የ2019 የአለም የፕሬስ ነጻነት ቀን በኢትዮጵያ እንደሚከበር ዩኔስኮ አስታወቀ

የ2019 የአለም የፕሬስ ነጻነት ቀን በኢትዮጵያ እንደሚከበር ዩኔስኮ አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የ2019 የአለም የፕሬስ ነጻነት ቀን በኢትዮጵያ እንዲከበር መወሰኑን ዩኔስኮ በይፋ አስታወቀ።

የመገናኛ ብዙሃን ሚና በዲሞክራሲና ምርጫ ላይ በሚል መሪ ቃል እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከግንቦት 2 እስከ 3 (በኢትዮጵያ ሚያዚያ 24 እና 25 ) ሲከበር ከመላው አለም አንድ ሺ የሚደርሱ እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ መንግስት ጠያቂነት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር እንደሚከበር የገለፁት የዩኔስኮ የኮሚኒኬሽን ረዳት ዳይሬክተር የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው ያላቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች በተለይ በሚዲያ ነፃነትና በሠብአዊ መብት አያያዝ ረገድ አድናቆት እንዳላቸው አክለው ገልፀዋል ።

ከሠሞኑ አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጄ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጠኞች ያልታሰሩባት ሃገር ሆናለች ሲል መግለፁ ይታወቃል ።

LEAVE A REPLY