እስኪነጋ | መስፍን ማሞ ተሰማ

እስኪነጋ | መስፍን ማሞ ተሰማ

ሠላም ለናንተ ይሁን!

አዎን እናምናለንአዎን የነጋ ነውየህወሃትናህወሃታውያን ዘመነ ፅልመት እየተገፈፈ ነውበኢትዮጵያ ሠማይ ሥር የብሩህ ቀን አጥቢያ ፍካትይታያልያለጥርጥር ይነጋልአዲስም ቀን ይሆናልግን ገና አልነጋም መቼ ይነጋል? ብላችሁ አትቸኩሉንጋትም ተፈጥሯዊ ዑደቱን ያጠናቅቅ ዘንድ ግድአለውና ንጋቱ በህወሃትና ህወሃታውያን ፅልመትእንዳይጋረድ ግድ ነውና

ህወሃታውያን እነማን ናቸው? ህወሃታውያን ማለትእነ ጃዋራውያን እነ ፀጋዬ አራርሳውያንመሰሎቻቸውና ወዘተርፈዎች ሁሉ ናቸውየበቀልናየቂም በቀል የጥላቻና የጎጠኝነት ታንቡረኞችህወሃትና ህወሃታውያንም የኢትዮጵያን ዘመነፅልመት ናፋቂዎች ናቸውና

እንዲነጋየህወሃትና ህወሃታውያን መጋዝጥርሳቸው ሊረግፍ ግድ ነውእብሪተኛውጉልበታቸው ሊፈስ ግድ ነው ለ27 ዓመት እንደመንግሥት የረጩት መርዛቸው ሁሉ ሊመክን ግድነው የታበየ ልባቸው ሊሟሽሽ ግድ ነው በዝርፊየደለበው የባንክ ደብተራቸው ይቀደድ ዘንድ ግድነው

እንዲነጋ መከላከያ ፖሊስና ደህንነት በለውጡ ህግሊገዙና ሊደራጁ ግድ ነው የሀገር እንጂ የጎጥአገልጋይና ታዛዥ አይሆኑ ዘንድ ግድ ነውፍርድቤቶችና የህግ ተቌማት  በለውጡ ራዕይ በህግናፍትህ አርማታ ላይ ብቻ ይታነፁ ዘንድ ግድ ነው

እንዲነጋዴሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራረፉ በህግማዕቀፍ በዜጎችም ያለ ስጋት ይተገበሩ ዘንድግድ ነው እንዲነጋበኢትዮጵያ ሠማይ ሥርነፃነትና ፍትህ መብትና እኩልነት ጠያቂ ዜጎችመኖሪያቸው ጨለማ ቤቶች ምሳና ራታቸውሰቅጣጭ ቶርቸር ውርደትና ሞት መሆኑበርግጠኝነት ማብቃት አለበት

እንዲነጋየኢትዮጵያ ልጆች በኢትዮጵያ ምድር ሁሉየመኖር ተፈጥሯዊ መብታቸው በህግ ማዕቀፍሊረጋገጥ ያለ ሥጋትም በዜጎች ሊተገበር ግድ ይላልእንዲነጋኢትዮጵያ ልጆቿን የምታሳድድየምታባርር መሆኗ ቀርቶ የምታቅፍና የምታኖርመሆን መቻሏ ግድ ነው

አዎ! በኢትዮጵያ መንጋቱን አዲስም ቀን መጥባቱንለማብሰርበኢትዮጵያ ሠማይ ሥርኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ነፃ ፈቃድና ነፃምርጫ የተመረጠ መንግሥት ቤተ መንግሥቱንይረከብ ዘንድ ግድ ይላል እነሆም በዚያን ቀንየአዲሲቷ ኢትዮጵያ ንጋት ይፋ ይሆናል!!! እነሆ ያኔፅልመቱ ያለ ርዝራዥ ተገፎ ይነጋልናኢትዮጵያናህዝቧም አዲስ ዘመን ይጀምራሉና!

እንግዲህ ይህ እስኪሆን ኢትዮጵያውያን እንቅልፍአይኖረንምእረፍትም አንመኝምየጨለማውንዘመን ትብትብ የፖለቲካ ሠንሠለት እስክንጣጥስየተዘረፈውን ሀገራዊ ሀብት እስክናስመልስበየጎጣቸው ድንኴን ሥር የተደበቁትን ጥፍርነቃዮንና የተደራጁ ሌቦችን መንጥረን በአደባባይችሎት እስክናቆም እስክንፋረድ በየጎጡየታመሰውንና የታመመውን ማህበረሰብ እስክናክምከቶም ደከመን አንልም ጨለማው ዘመንእንዳይመለስ ከቶም እንቅልፍ አይኖረንም

አዎን እናውቃለንእስኪነጋ ሃሳዊ መሲሆችይበዛሉበኢትዮጵያ ስም እየተገዘቱ የአዞ እንባየሚያነቡ የአሳማ ጩኸት የሚጮሁም ይበረክታሉእንደ ልበ ሙቅ የጅብ መንጋ ከየጎሬያቸውተጠራርተው እየተፈራገጡ የሚያቅራሩእንደጃርትም በየጎጡና በየቀበሌው የሚርገፈገፉይነሳሉየጨለማውን ዘመን የደም ጥርሳቸውንእያፋጩና የደም ጥፍሮቻቸውን እያንጨፈረሩይወራጫሉ

አዎን እስኪነጋ ደናቁርትና ዘመን ያለፈባቸውፖለቲከኞች ይበዛሉ፤ <ትንቢተኞች> ይፈላሉጃኬትገልባጮች ቦታ ይይዛሉአብይንና መንግሥቱንተቺዎችና አቃቂረኞች የበዙበትን ያህል ጭፍንአምላኪዎችም እንደፈሉ እናውቃለን።  አዎእስኪነጋ ይህ ሁሉ በኢትዮጵያ ሠማይ ሥር ይሆንዘንድ እናውቃለን አስቀድሞ ጠቢቡ እንደተናገረውእነሆ ይህ ሁሉ ሲነጋ ከንቱ ነውአዎ መንጋቱከቶም አይቀሬ ነውና ይነጋል!!

እስከዛውበደማችንና በሞታችንበእስራችንናበስደታችን ባላባራውም ተጋድሏችን በአብይ ፆምመውጫ በአብያዊ በዓለ ሲመት በታወጀውኢትዮጵያዊነት ያገኘነውን አብይ ስጦታ እስኪነጋድረስ ይዘነው እንዘልቃለንየትግላችን ፍሬየሆነውን አብያዊውን መንግሥት የደገፍነውናየምንደግፈውሰውና ኢትዮጵያዊ ስለሆንን ብቻነው!! ለዚህም ነው እስኪነጋ ተደጋግፈን አብረነውየምንጔዘው

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ!

ህዳር 2011 ዓ/ም (ኖቬምበር 2018)

ሲድኒ አውስትራሊያ

LEAVE A REPLY