/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በአፋር ክልል ኣዳር ወረዳ ሦስት ኩንታል ዶላር መያዙን ምንጮች ከቦታው አስታውቀዋል ።
ከሰሜን ወደ መሀል አገር በመጓዝ ላይ ባለ አንድ ቶዮታ መኪና ውስጥ የተጫነ ገንዘብ በህብረተሰቡ ጥርጣሬ እንዲቆም ተገዶ ሲፈተሽ በሶስት ማዳበሪያዎች የታጨቀ ዶላር መገኘቱን የተለያዩ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ተከትሎ ለማጣራት በቦታው የተገኘው ምንጮችን አረጋግጧል።
ገንዘቡ ወደ ባንክ በአደራ ገቢ ተደርጎ መኪናዋና ተሳፋሪዎቿ በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ክልሉ መዲና ሠመራ ተወስደዋል።
አሁን ከተያዘችዉ መኪና ጎን ቆማ የምትታየው በሮቿ የታሸጉት ጥቁር መኪና ከዚህ በፊት በተመሣሣይ መልኩ ገንዘብ የማሸሽ ተግባር ላይ ተሰማርታ በቁጥጥር ስር ተይዛ የታሠረች ነች መሆኗን ለመረዳት ተችሏል።