/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ሞት ና መፈናቀል እንዲቆም የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተካሄዱ።
ሰልፎቹ በአምቦ፣ ጊምቢ፣ ሆለታ፣ ቡራዪ፣ ባኮ እና መቱን ጨምሮ ሌሎች ከተሞችም ተካሂደዋል። ሰልፈኞቹ በክልሉ በተለያዩ አዋሳኝ ቦታዎች እየደረሰ ያለውን ግድያና እንግልት ያወገዘ ሲሆን ይህንን ተግባር የፈፀሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ገልጾ ባወጣው መግለጫ የኦሮሚያ ክልል ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል። እስካሁን ከ200 በላይ ሰዎች ችግሩን በማስጀመርና በመባባስ ተይዘዋል።
የፀጥታ ችግር እየፈጠሩ ያሉ አካላት በተቀናጀ መንገድ በስልጠና እና በተለያየ ጦር መሳሪያ በመደገፍ በህዝቡ ላይ ጦርነት የከፈቱ በመሆኑ ችግሩን በአጭር አልቆመም ያለው የክልሉ መግለጫ ችግሩን ለመፍታት መቸገሩን ገለጾ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር መቅረፍ እንዲቻል የኦሮሚያ እና የቤንሻንጉል ክልሎች ስምምነት ምክንያት የብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት ህዳር 21 ቀን 2011 ዓ.ም ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የፌደራል የፀጥታ አካላት ችግር ባጋጠማቸው አካባቢዎች በመግባት እርምጃ መውሰድ ጀምሯል።