የነገሮች መመሳሰል እንደገረመኝ እኖራለሁ፡፡ “ታሪክ ራሱን ይደግማል” መባሉም ትክክል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ላስታውስ እፈልጋለሁ፡፡ የውጫሌ ስምምነት ለምን እንደሆነ አላውቅም አሁን ትዝ አለኝ፡፡ በተለይ አንቀጽ 17፡፡
አንቀጽ 17 የውጫሌ ስምምነት ብዙ መዘዝ ያመጣች ናት፡፡ የአማርኛና የጣሊያንኛ ይዘቷ መለያየቱ ነበር ኢትዮጵያንና ጣሊያንን ብዙ ዋጋ ልታስከፍል የቻለችው፡፡ ለምን ትዝ እንዳለኝ አሁን ገባኝ፡፡ የአማራው ክልል ፕሬዝደንት አሜሪካ ገብተዋል፡፡ የአቀባበሉን ሥነ ሥርዓት እየተመለከትኩ ሳለ ነው ያቺ ነገረኛ አንቀጽ ትዝ ያለችኝ – ነፃ መሆናቸው ገርሞኝ፤ ምልባትም ከወያኔ ፈቃድ ሳያስፈልጋቸውና መቀየጃ ገመድ ቢጤ እግራቸው ላይ ሳይታሰር መሄዳቸው አስደንቆኝ፡፡
ጣሊያንና ትግራይ በብዙ ነገር ይመሳሰሉብኛል፡፡ ነገር ግን የትግራይ ጭካኔና ዐረመኔነት ከጣሊያን ጋር በፍጹም አይወዳደርም፡፡ ጣሊያን በዘርም ሆነ በቀለም ከኢትዮጵያ ጋር ዝምድና እንደሌላት ይያዝልኝ፡፡ ትግራይ ግን በዘርም፣ በሃይማኖትም፣ በቋንቋም፣ በሥነ ልቦናም፣ በኢኮኖሚም፣ በባህልም፣ …. ከኢትዮጵያውያን ጋር እጅግ እንደሚመሳሰሉና በብዙ ነገሮች እንዲያውም አንድ እንደሆኑ አስቡልኝ፡፡ እናም ቢያንስ ጣሊያኖች በግብረ ሶዶማዊ የቆሸሸ “የወንጀል ምርመራ” በቁም የመግደያ ሥልትና አሰቃቂ የእስረኞች አያያዝ ሲታሙ አልሰማሁም፡፡ ቢያንስ ጣሊያኖች እስረኞችን በርሀብና በምድር ቤት ውስጥ ሊነገር የማይችል የስቃይ ዓይነት ሲያንገላቱ እንደነበር የሚገልጽ ነገር ተጽፎ አላነበብኩም፡፡ ጣሊያኖች ጨዋ ጠላቶች ነበሩ፡፡ ጭካኔያቸው ለከት ነበረው፡፡ ሲገድሉ እንኳን በርህራሄ ነው፡፡ ሰዎች ነበሩና!
አንቀጽ 17 ነገረኛ ነበረች፡፡
“ኢትዮጵያ ለውጭ ጉዳይ ዲፕሎማሲዋ ጣሊያንን ልታማክር ትችላለች፡፡” የአማርኛው ይዘት፡፡
“ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ግንኙነቷን በጣሊያን በኩል ታከናውናለች፡፡” የጣሊያኛው ይዘት፡፡
ወደኛው ጎዶች ላምጣው፡፡
በግልጽ ተጽፎ የማይነበበው የሕወሓት አንቀጽ እንዲህ ይላል – “ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች (ወያኔ የጠፈጠፋቸው ማለት ነው) የውስጥም ሆነ የውጭ ግንኙነታቸውን ለማከናወን ‹የትግራይ ሪፓፕሊክ›ን ዕውቅናና ፈቃድ ማግኘት አለባቸው፡፡” የወያኔ ህገ መንግሥት አንቀጽ 11 ፡፡
የሚገርም መመሳሰል፡፡
በቀደመው የወያኔ ዘመን ትግራይ የፈለጋትን ዕቃና ገንዘብ ሁሉ ከክልሎች ስታፍስ ቆየች፡፡ የክልል መሪዎችን ልክ እንደቤት አሽከርና ገረድ በመቁጠር ስትፈልግም አስራ እየገረፈችና በሌሎች እስረኞች ላይ የምትፈጽመውን ብልግና ሁሉ ሳይቀር እየፈጸመችባው ሚስቶቻቸውንም ጭምር እየደፈረች ስትጫወትባቸው ኖረች፡፡ መሪዎቹ በቀን ስንቴ መብላት እንዳለባቸው፣ የትኅትናን ድምበር ለጣሰው የቃላት አጠቃቀሜ ይቅርታ ይደረግልኝና ስንቴ መሽናትና መፍሳትም እንዳለባቸው ስንቴ መተንፈስ እንዳለባቸው… ከትግራይ በቀጥታ በስልክና ሊቆጣጠራቸው አጠገባቸው ከተቀመጠ ትግሬ ወያኔ ትዕዛዝ እየተቀበሉ ራሳቸውን አዋርደው ሕዝባቸውንም አዋረዱ፡፡ ትግሬዎች አማራ ሆነው፣ ትግሬዎች ኦሮሞ ሆነው፣ ትግሬዎች ሃዲያ ሆነው፣ ትግሬዎች ወላይታ ሆነው፣ ትግሬዎች ጉራጌ ሆነው …. አማረ፣ ደቻሳ፣ ዋንታሞ፣ ሻመና፣ ዘበርጋ…. በሚሉ ስሞች ኢትዮጵያን ዳር እስከዳር ጋጧት – እንደጅብ ሠፍረውባት አመሸኳት፡፡
ጅብ እምብርት ያለው መሆኑን በነሱ እምብርት-አልባነት እስክናረጋገጥ ድረስ ሀገሪቱን በርሀብ አንጀታቸው ወረዱባት፡፡ የፈለጉትን መሬትና ንብረት ወደ ትግራይ አሸጋገሩ፡፡ ማይማኑ ወያኔዎችና ጀሌያቸው የቁጥርን ምንነት አለማወቃቸውን እስክናረጋግጥ ድረስ በቁጥር ማይምነታቸው ላይ እንኳን ሣቅንባቸው፡፡ ሚሊዮንንና ቢሊዮንን እንደ አምስትና አሥር ቁጥሮች አውርደው ተራ ሲያደርጓቸው “ወይ ማይምነት!” ብለን ተሣለቅንባቸው፡፡ “እገሌ የተባለው ወዲ ሐጎስ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ዘረፈ፤ እገሌ የተባለው ወዲ አህፈሮም 10 ቢሊዮን ብር ሠረቀ…” መባልን ስንሰማ እኛ ራሳችንም የቁጥር ማይማን መሆናችንን እስክንጠራጠር ገረመን፡፡ ይሄ ይሄኛው ሆዳምነት እንኳን ምንም ማለት አይደለም – ደንቆሮ ጆሮ ብቻ ሣይሆን የጥጋብና እርካታ መለኪያም ስለሌለው የነሱ ለየት ቢልም ግዴለም ይሁን፡፡ ሕዝቧን ሰማይና ምድር ሊሰሙት በሚሰቀጥጣቸው ስቃይ ፍዳውን ማብላታቸው ግን ከይቅርታም በላይ ነው – ይህ ነው አብሮ የማያኗኑረው፡፡ አሁን ያ ሂደት እየቀረ ይመስላል፡፡ ስንት የሚያስቅና የሚያስገርም፣ ደም የሚያስለቅስና በትውልዶች መሀል
ግርዶሽ ሆኖ እስከወዲያኛው የሚዘልቅ ነገር ስንታዘብ ቆየን፤ ወይ ጊዜ ደጉ! ይህን ሁሉ ያደረጉት ግና እነሱ ብቻቸውን እንዳይመስልህ፡፡ የኛ ኃጢኣት፣ የውጭ ጠላቶቻችን ቁሣዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የመረጃ እገዛ፣ የኛ አለመተባበርና እንዲያውም መገፈታተር፣ ሌላም ሌላም… ተደምሮበት የነሱን ወንጀልና ብልጣብልጥነት አገዘፈው፡፡ በዚያም ምክንያት ክፉኛ ተጎዳን፡፡
… እስካሁን እንዲህ ነበርን፡፡ የወደፊቱን ደግሞ ልናይ ነው፡፡ ግን ግን ሁሉም ይህን እውነት ይገንዘብ – እግዚአብሔር በመንበሩ አለ!! ብዙ ያሳየናል ገና – በቃ፡፡ “ለለአሃዱ በበምግባሩ” እንዲል መጽሐፉ፡፡ yiheyisaemro@gmail.com