/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በስመ ኢንቨስትመንት ስራ ላይ ባልዋሉ መሬቶች ከሁለት ነጥብ አራት ቢሊየን ብር በላይ ያለአግባብ ከባንክ ብድር መወሠዱ ተጋለጠ ።
የጋምቤላን መሬት በኢንቨስትመንት ስም ግለሰቦች ተቀራምተውታል፤ ነገር ግን መሬቱ ለታሰበለት ልማት ሳይዉል በሌጣው ብድር ከባንክ ተወስዶባቸዋል ሲል ልማት ባንክን ዋቢ ያደረገ መረጃ አጋለጠ ።
ከ2005-2009 ዓም በኢንቨትመንት ስም 160 ግለሰቦች የጋምቤላ ክልል መሬትን በመቀራመት ከኢትዩጵያ ልማት ባንክ 2,460,457,327.15 (ሁለት ቢልዩን አራት መቶ ስልሳ ሚልዩን አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሀያ ሳባት ብር ከ15 ሳንቲም) በብድር ስም የወሰዱ ሲሆን ፤
“ከብድሩ ውስጥ 99% አልተመለሰም፤ መሬቱም ለታሰበለት አላማ አልዋለም ” ይላል ልማት ባንክን መሰረት አድርጎ የወጣዉ ይኸው መረጃ።
መረጃው ይፋ ያደረገውን ዝርዝር ከምስሎቹ ይታዘቡ።