/ኢትዮጵያነገዜና/፡- አቶ ላለፉት ሶስት አመታት ከአማራ ክልል ቁጥጥር ውጭ ነበሩ የተባሉ ሶስት ቀበሌዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው እንዳስታወቀው የአማራ ክልል ከህዝቡ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሰሞኑን በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ ከክልሉ ቁጥጥር ውጭ ነበሩ የተባሉ ሦስት ቀበሌዎች አንድም ጥይት ሳይተኮስ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው የተመራ የአመራር ቡድንም በሦስቱም ቀበሌዎች በመግባት ከህዝቡ ጋር የተሳካ ውይይት አድርጓል ተብሏል።
ጉባይ ጀጀቢት፣ ሌንጫ እና መቃ የተባሉ ቀበሌዎች ከሶስት አመት በላይ ከክልሉ መንግስት እጅ ውጭ እንደነበሩ ከዚህ በፊት በአማራ ክልል የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ብርጋዴል ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ተገልፆ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በአማራ ክልል የቅማንት የማንነት ጥያቄ በተመለከተ ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካን ሀገር በተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባ ሲያደርጉ የነበሩት በክልሉ ርእሰ መስተዳድር በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልኡካን ቡድን በተደጋጋሚ የተጠየቁ ሲሆን ሁኔታውን ለማረጋጋት ስብሰባ አቋርጠው ሊመለሱ እንደነበር ያወሱት አቶ ገዱ በሁለቱ ወንድማማች አርሶ አደሮች መካከል ጣልቃ በመግባት መሳሪያና በርካታ ገንዘብ የሚያፈስ ሃይል መኖሩን ጠቁመዋል።