28 ህገ ወጥ የተባሉ ታላላቅ የሪል እስቴት ኩባንያዎች ታገዱ

28 ህገ ወጥ የተባሉ ታላላቅ የሪል እስቴት ኩባንያዎች ታገዱ

/ኢትዮጵያነገዜና/፡- 28 ታላላቅ የሪል እስቴት ኩባንያዎች በህገወጥነት ተጠርጥረው መታገዳቸው ተገለፀ ። ጉዳዩን እንዲከታተል በም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የተቋቋመው ኮሚቴ በኩባንያዎቹ ላይ ያካሄደውን የዳሠሣ ጥናት ተከትሎ ከአገልግሉት ታግደው እንዲቆዩ ተወስኗል።

ዕግዱ በግልባጭ የተላከላቸው እንደ መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ እንዲሁም የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ፅ/ቤት ያሉት ተቋማት ከታህሳስ 18/2011 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ለተጠረጠሩት ኩባንያዎች አገልግሎት እንደማይሠጡ ታውቋል።

ኩባንያዎቹ በወንጀል የተጠረጠሩት፦ መሬት በሚያገኙባቸው መንገዶችና ግንባታ በሚያከናውኑባቸው ሁኔታዎች ቢሆኑም ጥርጣሬውን ይበልጥ ያጠናከረው ደግሞ ከኩባንያዎቹ ባለቤቶች የተወሠኑት ንብረት ወደ ሶስተኛ ወገን ስም በማዛወር ሀብት ለማሸሽ የሚያደርጉት ጥረት እና ከፍተኛ ሩጫ መሆኑ ተመልክቷል።

ጉዳዩን ለመመርመር የተቋቋመው ኮሚቴ ከመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጋር በመጣመር ጥናቱን ካጠናቀቀ በኋላ ህጋዊዎቹን ወደ አገልግሎት፤ ህገወጦቹን ደግሞ ወደ ዕርምት ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል ።

በህገወጥነት ተጠርጥረው የታገዱት ኩባንያዎች የሚከተሉት ናቸው፦

ኖህ ሪል ስቴት
ሰንሻይን
አያት
ሳትኮን ኮንስትራክሽን
ሴንቸሪ 21 ኮንስትራክሽን
ሙለር
ሳንታ ማርያ
ዋይቲዋይ ኮንስትራክሽን
ኃይሌና ዓለም ሪል ስቴት
ሰዒድ መሐመድ
ማኅተባይ ሪል ስቴት
አደይ አበባ ፍሰሐ ሴት
ናታን
ጌታቸው ወልዴ
ወልመስ ኮንስትራክሽን
ሐውስ ዊዝደም የጋራ መኖሪያ ቤቶች
ዮሐንስ ካሳዬ
የማናት
ዛምራ ትሬዲንግ
ማክሮ
ሮማናት
ፀሐይ ሪል ስቴት
መክሊት ሪል ስቴት
ጎላጉል ሪል ስቴት
ካሩቱሪ ሪል ስቴት
ባታ ሪል ስቴትና
ፈቃዱና ጓደኞቹ ሪል ስቴት

LEAVE A REPLY