/ኢትዮጵያነገዜና/፡- የኢትዮጵያ መንግስት 20 በተለያዩ ሃገራት የሚሰሩ አምባሳደሮችን መሾማቸውን አስታወቀ። ኤምባሲዎችን ለማጠናከር እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንም በተገቢው መንገድ ሊያገለግል የሚችሉ አሰራሮች እንዲዘረጋ ሲወተውት እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በአንዳንድ ሃገራት የነበሩ አምባሳደሮችም ለቦታው የማይመጥኑና በስደት ከሚኖሩ ዜጎቻቸው ጋር ስምምነት እንዳልነበራቸው ይታወሳል።
አዳዲሶቹ ተሿሚዎች በሃላፊነት የሚሰሩ እና በተለይ ከኢትዮጵያውያን ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሊሰሩ የሚችሉ ይሆናሉ ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ያመላከቱ ሲሆን በሌላ በኩል ተሿሚዎቹ አሁንም ያለበቂ ችሎታ የገዢው ፓርቲ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸው ተሿሚዎች እንደተካተቱበት ጠቁመዋል።
በሹመት አሰጣጡ ደንብ መሰረት የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሣህለወርቅ በውጭ አገራት ኢትዮጵያን ለሚወክሉ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደሮች ሹመት መስጠታቸውን የሃገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ተሿሚዎችም የሚከተሉት መሆናቸው ተገልጿል።
1. አቶ ዘነበ ከበደ፣
2. አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣
3. ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን፣
4. አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድ፣
5. ወ/ሮ ናሲሴ ጫሊ፣
6. አቶ ሐሰን ታጁ፣
7. አቶ ረታ አለሙ፣
8. አቶ ሄኖክ ተፈራ፣
9. ወ/ሮ አለምፀሐይ መሠረት፣
10. ዶ/ር ትዝታ ሙሉጌታ፣
11. አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ፣
12. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣
13. አቶ ተፈሪ ታደሰ፣
14. አቶ ፍፁም አረጋ፣
15. ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር፣
16. አቶ ሚሊዮን ሳሙኤል፣
17. አቶ መለስ አለም፣
18. አቶ ብርሃኔ ፍስሐ፣
19. ዶ/ር አይሮራት መሐመድ እና
20. አምባሳደር ሳሚያ ዘካርያ በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ተሹመዋል፡፡
ምንጭ፡- የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት