በትግራይ ወደ ኤርትራ የሚያስገባው የዛላምበሳ ድንበር ተዘጋ

በትግራይ ወደ ኤርትራ የሚያስገባው የዛላምበሳ ድንበር ተዘጋ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ዶክተር አባይ ከተመረጡ እስር ወራቶች ውስጥ ከስራቸው ታላላቅ ስራዎች ውስጥ በአለምአቀፍ እና በኢትዮጵያውያን ጉልህ ሰፈራ የያዘው የኢትዮጵያ እና የኤርትራው 20 አመት የዘለቀ ጦርነት ከፍጻሜ መድረስ ሲሆን በዚህም ምክንያት ተከፍቶ የነበረው የዛላምበሳ ድንበር ዛሬ መዘጋቱ  ተገልጿል።

በድንበሩ አካባቢ ከፍተኛ የንግድና የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ሲከናወን ለአስር ወራት ዘልቆ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ በኤርትራ መንግስት ትዕዛዝ ድንበሩ አካባቢ ለማለፍ የመንግስት የይለፍ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ብቻ መሆኑ ይፋ ሆኗል።

በኤርትራ አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ ወዲህ መንግስት ይህንን እርምጃ እንዲወስድ መገደዱን ዘገባዎች የጠቆሙ ከመሆኑም በላይ ዛሬ በተዘጋው የዛላንበሳ ድንበር አካባቢ ለገበያ የተዘጋጁ አትክልትና ፍራፍሬዎች ለኪሳራ ማድረጋቸው ታውቋል።

የኤርትራው የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ኤፍሬም ይስሃቅ ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራ ክፉኛ ተደብድበው በአሁኑ ሰዓት በአረብ ሀገር ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ድምጸ አልባ መስሪያ ይዞ በመኖሪያ ቤታቸው የመግደል ሙከራ አደረገ የተባለ ግለሰብ በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ  በውጭ የሚገኙ የኤርትራ ድረገጾች ዘግበዋል።

ይህ ሂደት በማናቸውም መልኩ የትግራይ ህዝብ በህወሓት ላይ እጁን እንዲያነሳ ያስገድደዋል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች የትግራይ ህዝብ በየትኛውም አቅጣጫ የሚያደርጋቸው የንግድም ሆነ የማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እየተገቱ የሚገኙት ህወሓት ከማእከላዊ መንግስት ጋር በሚያራምደው ያልተገቡ ፍጥጫዎች ስለሆነ ወደከፋ ደረጃ ሳይደርስ የትግራይ ምሁራን ህውሀታዊ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ምልከታ ያለው ሰፊ ውይይት ማድረግ እና ህዝቡን ከህወሃት የመነጠል እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ ያስገነዝባሉ።

LEAVE A REPLY