ሠላም ለናንተ ይሁን!
የትግላችንና የመሥዋዕትነታችን የመታሰራችንና የመሰደዳችን ውጤት የሆነው አብያዊው መንግሥት በኢትዮጵያ መንበር ላይ ሲቀመጥ ለ27 ዓመት በምድሪቱ ላይየሰቆቃና የርኩሰት የጥፋትና የዝርፊያ ሁሉ ቁንጮ የሆነውአሸባሪውና ዘረኛው ህወሃት ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይያለጥርጥር ተመንጭቆ ወርዷል።
የወረደውና የተዋረደው ህወሃት መቀሌ ትግራይ መሽጎ ይንደፋደፋል። በወላለቀ ጥርሱ እየገለፈጠ፤ በተሸበሸበ እጁእያጨበጨበ በስታዲየምና በአዳራሽ እየተሰበሰበ የቁምተዝካሩን ያወጣል። ማጋነን የመሰለው በቅርቡ መቀሌዩኒቨርሲቲ የተካሄደውን ስብሰባ ይመልከት።
በዚያ አዳራሽ የክፉ ሰዎች ስብስብ የሆነው ህወሃት ጣዕረሞት ላይ ስለመሆኑ ስብሃት ነጋ በአስረጅነት የቀረበ«አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም» የሚለው ብሂል ማሳያ ነው። 27 ዓመት ዲሞክራሲን ቤተ መንግሥት ሆኖ ሲሰይፍ የኖረውህወሃት መቀሌ ላይ መሰየፍ ባቃታቸው የጃጁ እጆቹእያጨበጨበ የፀረ ዲሞክራሲነቱን ተዝካር አውጥቷል።
አሸባሪው ህወሃትና በኢትዮጵያ ምድር በአምሳያው ፈጥሮየዘራቸው አሜኬላዎች ሁሉ በለውጡ ማዕበል ተጠራርገውየኢትዮጵያ ትንሣዔ ዕውን እንደሚሆን ከቶም አንጠራጠርም። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ህወሃት ከነርኩሰቱናከነግብረ በላዎቹ መቀመቅ ይወርዳል።
ከህወሃት በተጔዳኝ የኢትዮጵያን ትንሣኤ እያወከ ያለው ኦነግነው። ህወሃት እንደ ድርጅት ከፅንሱ እስከ ውልደቱ፤ ከውልደቱ እስከ ጣዕረ ሞቱ ለኢትዮጵያ ጠንቅ እንደሆነ ሁሉኦነግም እንዲሁ ነው። ኦነግ ስለ ኢትዮጵያ መጥፋት እንጂስለ ኢትዮጵያ መኖር አልሞም ሆነ ሰርቶ አያውቅም።ኢትዮጵያውያንን ለመሰየፍና ኢትዮጵያን ለመበተንየሜንጨኛውን ጃዋር እና የለንደኑን የኦነጋውያንን ስብሰባፉከራ ዋቢ ማቅረብ ይበቃል። ኢትዮጵያን ማፍረስ እንጂማዳን አላማችን አይደለም ያሉትን።
ኢዮባዊ ትዕግሥት የሰፈነበት አብያዊው መንግሥት የኦነግንእኩይነትና በቀል በይቅርታና በንስሃ ለማስተሰረይ በዘረጋለትየሠላም እጅ «ተቀብሎ» ከአስመራ አዲስ አበባ ሲገባ ለኦነግየተደረገውንና ኦነግ በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ያደረገውንኢትዮጵያ መቼም አትረሳም። ቡራዩ ይመሰክራልና።
ይህም ሁሉ ሆኖ ለኦነግ «የሳሳ ልብ» የነበረው አብያዊውመንግሥት ባልዋለበት ገድል ጩኸት ያበዛውን ኦነግበአንቀልባ አዝሎ ሲያባብለው ወራትን አስቆጥሯል። ኦነግታዝሎም መዝለሉንና ጀርባ መንከሱን አላቆመም። ኦነግንያዘለው አብያዊው መንግሥት ኢትዮጵያዊ ነው። እናም ኦነግጀርባዋን እየነከሰ የሚያደማው ሠላም ፈላጊዋን ኢትዮጵያንነው። ኦነግ ዕብደት ላይ ነው። አብይንና ለማን ወለጋ ላይአጥምዶ በጥይት ለመጣል ማሴሩን ሰምተናል። አብይ ራሱበአደባባይ ነግሮናልና። አብይንና ለማን ለመግደል ማቀድየለየለት ፀረ ኢትዮጵያዊነት ነው። ኦነግ ታድሶም ሆነ ተሞርዶከዕብደቱ ሊድን ከቶም አይችልም።
ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ኦነግንና ኦነጋውያንን አዝላየምታባብልበት ጀርባ የላትም። መቀሌ ትግራይ እንደመሸገው አምሳያው ህወሃት ነቀምትና ቄለም ወለጋ ውስጥየከተመውና በየጉድባው አድፍጦ ህዝብንና ሀገርንየሚያሸብረው ኦነጋዊ ሁሉ ከኢትዮጵያ ጋር «መደመር» ከቶምቢሆን አይችልምና መቀነስ አለበት።
ኦነግን ከታዘለበት አንቀልባ ያወረደውና ክንዱን ሊያነሳየወሰነው አብያዊው መንግሥት እርምጃው ቢዘገይምሀገርንና ህዝብን ከኦነግና ኦነጋውያን ጥፋት ለመታደግአልረፈደምና «ቅነሳው» ይበልጥ ተጠናክሮና ፈርጥሞይቀጥል ዘንድ እንጠይቃለን።
ከእንግዲህ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ኦነግንና ኦነጋውያንን፤ ህወሃትንና ህወሃታውያንን እና መሰል ወዘተርፈዎችንማዘልም ሆነ መሸከም አንችልም፤ አንገፍግፈውናልና – በቃንበቃን በቃን!!!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ!
ታህሳስ 2011 ዓ/ም (ዲሴምበር 2018)
ሲድኒ አውስትራሊያ
mmtessema@gmail.com