ምን ይሰማህ ይሆን – What’s on your mind? | በማህሙድ እንድሪስ

ምን ይሰማህ ይሆን – What’s on your mind? | በማህሙድ እንድሪስ

ራስህ ጠቋሚ
ራስህ ገምጋሚ
ራስህ አራሚ
ራስህ ፈራሚ
ራስህ አርቃቂ
ራስህ አፅዳቂ
ነኝ ብለህ ደምድመህ ለኛ ከኛ በላይ “ሁሉንም አዋቂ”
እኔ ብቻ እንዳላልክ ዘመንህን ሁሉ
ዛሬ ሰው ፈልገህ ተጣርተሀል አሉ
ይገርማል ይደንቃል
ያን ያህል አቃለህ ሰውነቱን ክደህ እንዳላረከስከው
ምን ጉድ አጋጥሞህ ነው የሰው ያለህ ያልከው?
ያንን ሁሉ ክፋት
ያንን ሁሉ ንቀት
ያንን ሁሉ ዕብሪት
ያንን ሁሉ ትዕቢት
ወዴት አደረስከው?
ያኔ ስማኝ ሲልህ
ስትገፋው ኑረህ መላ ስታሳጣው
አሁን ና ስትለው ማነው የሚመጣው?
ስለዚህ ወዳጀ
ያው እንዳመጣብህ የራስህን እዳ ራስህ ተወጣው።

LEAVE A REPLY