… ድርጅቱ ለዓመታት የሰራቸው መልካም ስራዎች መኖራቸው እሙን ነው። …በገዥው ሃይል ተጠምዝዞም በግሉ ፕሬስ ላይ የሰራቸው ደባዎችና አኩይ ተግባራትም ይታወቃሉ፤ አይረሱም። ነጻው ፕሬስን የግዴታ ጠርናፊ አንቀፆችን የያዘ ውል እስከማስፈረም፣ ብሎም አላትምም እስከማለት የደረሰበት ጊዜያቶችን አይተናል – በተለይ ገዥውን ሃይል በሚሞግቱ የህትመት ውጤቶች ላይ።
በሃገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ የህትመት ውጤቶች እየበዙ ነው፣ እሰየው ነው። ነገ ከነገወዲያም ይብዙ እላለሁ። ነገር ግን ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ በአንድ በኩል አትራፊ መሆኑ ይገለጻል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ትናንት በሚሰራበት መንገድ እየተጓዘ ነው መሰል፣ የህትመት ውጤቶች በቀናቸው (መውጣት በሚገባቸው ዕለት) ለንባብ የማይደርሱበትን ሁነት እያስረዋልን ነው። ይሄ አግባብ አይደለም። የህትመት ውጤቶች ለአንባቢያን በተቻለ መጠን በሚወጡበት ዕለት መድረስ ይኖርባቸዋል። የአሳታሚዎች በተለያየ መንገድ ዘግይቶ ወደማተሚያ ቤት መግባትም አንድ ራሱን የቻል ችግር መሆኑ ሳይዘነጋ።
ለምሳሌ ባሳለፍነው ቅዳሜ፣ ኢትዮጲስ ጋዜጣ ቅዳሜ ዘግይታ ነበር ለንባብ የበቃችው። ቅዳሜ መውጣት የነበረበት አዲስ አድማስ ጋዜጣም ትናንት ሰኞ ዕለት ነው መውጣት የቻለው። ባለፏት ወራት ተደጋጋሚ ችግር አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ታይቷል። የዕለተ ዕሁዱ ሪፖርተር ጋዜጣንም ዛሬ ማክሰኞ ነው ልናገኘው የቻልነው። …የዕሁድ ሪፖርተር፣ ፎርቹን …ጋዜጦች፣ ሰኞና ማክሰኞ ሲወጡ ብዙ ጊዜ አይቻለሁ። ፍትህ መጽሄትም ቅዳሜ መውጣት ሲገባው እሁድ የወጣበት ቀን አለ። የት እንደሚታተም በእጄ ላይ በሚገኙ መጽሄቶች ላይ ተገልጾ አላየሁም።
ከመጡ ገዥዎች ጋር አክሮባት እየሰራ፣ በአድርባይነት በዋነኝነት ገዥዎችን የሚያገለግለው ዕድሜ ጠገቡ አዲስ ዘመን ጋዜጣም ዛሬ አልወጣም ብለውኛል – ጋዜጣ አዟሪዎች። እንደሚታተም በመጽሄቱ ላይ ተገልጾ ባላይም። ማሽን ተበላሽቶ የሚባል ችግሩ እንደምክንያት ይሰማል።ይሄ ሊያጋጥም ይችላል። ግን ተደጋጋሚ ብልሽት ከሆነም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጠንካራ መፍትሄ ያሻል። ትርፋማ የተባለው፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትም ከዘመኑ ጋር የሚሄድና የሚመጥን አሰራርን መከተል ይኖርበታል።
ዘግይቶ መውጣት አሳታሚዎችን፣ አንባቢዎች ይጎዳል!
#ኢትዮጵያ!
#ዓለም!