ዛሬ የትግራይ ቴሌቪዥን ጄኔራል ተክለብርሃንና ታሪክ አዋቂ ብሎ የጠራቸዉ ግለሰቦች የሸዋ ታሪክ ፀሀፊዎች ታሪካችንን አኮሰሱ ዶጋሊ እንዳይከበር አደረጉ ሲል ወርዶ ወርዶ ሸዋን መዝለፍ ጀምሯል። ሸዋ ታጋሽና ጨዋ ሕዝብ ነዉ። የትግራይ ህዝብ ወንድሙ ነዉ። የኤርትራ ህዝብ ወንድሙ ነዉ። ፖለቲካ መጪና ሂያጅ ነዉ።ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ስም መያዝ አይፈልግም። በዚያ ሁሉ ግርግር እንኳን ጨዋነቱን ያሳየ ህዝብ ነዉ።
ደግሞም ሸዋ ዶጋሊ ዘምቷል ድሉም በሸዋ ታላቅ ፌስታ ተደርጎበታል። እናም ጄኔራል ተክለብርሃን እና ጓደኞቹ ኤርትራ ሄደዉ መታረቅ ከፈለጉ ዶ/ር አብይ በሩን ከፍቶላቸዋል። ተዋህደዉ እንዳሰቡት አግአዚያን የሚባል አገር መመስረት ፈልገዉ ከሆነም መብታቸዉ ነዉ። ነገር ግን የትግራይን ህዝብ የውሸት ታሪክ መግቦ የተለያየ አወደ ግንባር በመፍጠር አጀንዳ ለማሳትና ከወንድሞቹ ለማጋጨት መሞከር አደጋዉ ከባድ ነዉ። የትግራይ ህዝብ ከአማራም ሆነ ከኤርትራ ወንድሙ የሚለየዉ ምንም የለም። ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጋር ተዋዶና ተስማምቶ የሚኖር ህዝብ ነዉ።
ለግንዛቤ
ራስ አሉላን ከፍ አድርጎ ያመሰገነ በየዓመቱም የዶጋሊን ድል ይዘክር የነበረዉ የመሃል አገር ህዝብ ነዉ። በ1979 የዶጋሊ ድል 100ኛ ዓመት ታላቅ ፖስተር ተሰቅሎ በኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ታላላቅ የጥናት ፅሁፎች ቀርበዉ አሉላ ተወድሰዋል። በአዲስ አበባ ስቴድየም ታላቅ የሙዚቃ ዝግጅት ተዘጋጅቷል።
1.የዶጋሊ ድል እንኳን ሊነገር በሬዲዮ ስሙ እንዳይነሳ የተደረገዉ በህወሀት ነዉ። ህወሀት ከ1983 አስከ አሁን አሉላን የሚወድ ቢሆን ኑሮ ለምን ዶጋሊን አላከበረም?
2.ህወሀት ዶጋሊ ላይ ደርግ ያቆመዉን የአሉላ አባነጋ ሐዉልት የዛሬ 27 ዓመት በሻዕቢያ ሲፈርስ በደሰታ ያጨበጨበና የአሉላን ታሪክ ያኮሰሰ ደማቸዉ ላይ ቆሞ የተሳደበ ደርጅት ነዉ። ለማስታወስ ደራሲ ፀጋዬ ገብረመድኅን የሐዉልቱ ምረቃ ቀን ታላቅ ግጥም አቅርበዋል። ህወሐት ኤርትራ እና ትግራይ ይመሳሰላሉ እንጂ አንድ አይደሉም የሚል ትርክት ያስተማረ ነዉ። አሁን ደግሞ ሸዋ ለያየን የሚል ትርክት ተጀምሯል። 27 ዓመት ሙሉ ከሻዕብያ ጋር እንዳትሰሩ ማን ከለከላችሁ። ምኒልክ?ሸዋ?
3.ዮሐንስ 4ኛ አይሮፕላን ማረፊያ ሻዕቢያ ሲቀይር ድጋፉን የሰጠ ድርጅት ህወሐት ነዉ።
እና አሁን ምን ይጠበስ ነዉ? ለምን ኢትዮጵያና ኤርትራ ታረቁ ነዉ? ምፅዋ መሄድ ናፈቃችሁ? አሉላ እኮ ኢትዮጵያዊ እንጂ የሰፈር ታጋይ የጎጥ ፖለቲከኛ አይደሉም። አሉላ ከፍታ ላይ ለመድረስ ብዙ ይቀራችኋል። አሉላ ሌላ ህወሐት ሌላ