የሶማሌ ክልል የ12 ምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ

የሶማሌ ክልል የ12 ምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ባሳለፈነው አመት ሐምሌ በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት እጃቸው አለበት ያላቸውን 12 የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት መነሳቱ ተገለጸ።

የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ውሳኔውን ያስተላለፈ ሲሆን መብታቸው ከተነሳባቸው የምክር ቤት አባላት ውስጥም ስድስት የሚሆኑት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
12ቱ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳባቸው የሶማሌ ክልል የምክር ቤት አባላትን ስም ዝርዝር ይፋ ያደረጉ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ እርከን የሃላፊነት ቦታ ላይ የሰሩ አመራር እንደሚገኙበት አመልክተዋል።
1. አቶ መሐመድ ረሺድ ኢሳቅ – የቀድሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ
2. አቶ ከደር አብዲ – የቀድሞ ንግድና ኢንዱስተሪ ቢሮ ኃላፊና የሶሕዴፖማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
3. አቶ አህመድ አብዲ – የክልሉ የቀድሞ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና የክልሉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከሥልጣናቸው ሲለቁ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩ
4. ወ/ሮ ፈርቱን አብዲ መህዲ – የውኃ ልማት ቢሮ ኃላፊ
5. ወ/ሮ ሱአድ አህመድ ፋራህ – የቀድሞ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
6. አቶ አብዲሀሊም መሐመድ – የውኃ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ
7. ወ/ሮ ማጅዳ መሐመድ – የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
8. ወ/ሮ አያን ጉላንዴ – የጎዴ ከተማ የፋይናንስና አስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
9. አቶ መሐሙድ ሔርዮ – የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
10. አቶ አብዲ መሐመድ አባስ – የአርብቶ አርደርና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ
11. አቶ መሐመድ ቢሌ (ሚግ) – የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
12. ወ/ሮ ነስራ ሐሰን – የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት አማካሪ የነበሩ ሙሉ በሙሉ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳባቸው መሆናቸው ታውቋል።

አባላቱ የሰብአዊ መብትን ከመጣስና በግጭቶች እስከማነሳሳት የሚዘልቅ ክስ እንደሚቀርብባቸው እና በሙስናና የወንጀል ክሶች ተጠያቂ እንደሚሆኑ ዘገባዎች አሰረድተዋል።

በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ኦማር እና በፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን በሆኑት አቶ አህመድ ሸዴ መካከል የነበረውን አለመግባባት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቢሯቸው ጠርተው በመነጋገር ማስማማታቸው ይፋ ተደርጎ እንደነበር አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY