ፊንፌኔ/አዲስ አበባ | አምዶም ገብረስላሴ

ፊንፌኔ/አዲስ አበባ | አምዶም ገብረስላሴ

ለኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦችን እና የኢትዮጵያ አንዱ ብሄር የሆነውን ሆደ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ ግጭት ውስጥ ለማስገባት አጎቶቸ ያዘጋጁት የግጭት ድግስ “ፊንፌኔ የኛ አዲስ አበባ የኛ”!!!!!!

እንደሚታወቀው አጎቶቸ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እና የስልጣናቸውን ጊዜ ለማራዘም ሲባል የኢትዮጵያን ህዝብ ከነደፋበት መርዛማ ስትራቴጅወች መካከል የአጭር እና የረጅም ልብወለዶችን በመፃፍ አንዱ ብሄር ከአንዱ ብሄር እንዲጋጭ ማድረግ፣የአንዱን ክልል መሬት ቆርሶ ለአንዱ መወሰን እና የመሳሰሉት ሲሆኑ የብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ እና የአፍሪካ አንድነት መቀመጫ የሆነችው ፊንፌኔ ወይም አዲስ አበባም ከላይ ከጠቀስኳቸው መርዛማ ስትራቴጅወች መካከል የሆነች ሴራ ሴራ ስትሆን ሆደ ሰፊውን እና በተለያዩ አካባቢወች የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን አቅፎ በፍቅር የሚኖረውን የኦሮሞ ህዝብ ለማጋጨት የተዘጋጀች የህወሀት እና በህወሀት ደጋፊነት ኤርትራ በርሀ ከአርባ አመታት በላይ ከርሞ በእነስበሀት ነጋ ከፍተኛ አቀባበል የተፈጠረውን ለውጥ ተጠቅሞ አንድም ጥይት ሳይተኩስ ወደ ኢትዮጵያ በገባው የዳውድ ኢብሳ ኦነግ የተደገሰች የጥፋት ሴራ እንደሆነች የአደባባይ ሚስጥር ነው!!!!!

dawed ibsa n sebhatበነገራችን ላይ አዲስ አበባ/ፊንፌኔ አይበለው እና የኦሮሞ ህዝብ የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሳ እና የወሰን አከላል በታሪክም ይሁን አሁን ባለው ወሰን ፊንፌኔ/አዲስ አበባ ኦሮሚያ ክልል ወሰን ውስጥ ሆና ከተገኘች ፊንፌኔ/አዲስ አበባ ደሴት ስላልሆነች ወደኦሮሚያ መካለሏን ማንም ይቃወማል የሚል ሀሳብ በጤኛ አእምሮ ባለቤቶች ይታሰባል ብየ አላስብም።ነገር ግን ወዳጀ ኦሮምያ ትገነጠላለች ብለክ የምታስብና ኦሮምያን ለመገንጠል ቀን ከሌት የምትሰራ ከሆነ የአለማችን ምርጡ ዘገምተኛ ነክ ብየ አስባለው።ምክንያቱም በውስጧ በሚሊየን ከሚቆጠሩ ብሄር ብሄረሰቦችን ይዛ ተጋብታና ተዋልዳ በፍቅር ከእግዚአብሄር የሰጣትን የተፈጥሮ ሀብት አካፍላ የምትኖርና ሰፊውን የኢትዮጵያ ምድር የያዘች ክልል ስለሆነች አንተ ቤተስብክን ይዘክ በራስክ አለም ትገነጠል ይሆናል እንጅ ኦሮምያን ወዴትም ልትገነጥላት አትችልም!!!!

ስለዚህ በአማራ ስም እና በኦሮሞ ስም የፌስ ቡክ አካውንት እየፈጠርክ ፊንፌኔ የኛ አዲስ አበባ የኛ በሚል ጊዜክን በከንቱ ከምታባክን ያገኘከውን ለውጥ ተጠቅመክ ለራስክም ለቤተሰብክም ብሎም ለሀገርህ በሚጠቅም ስራ ላይ ብታሳልፍ ለራስክም፣ለቤተሰብህም እንዲሁም ለሀገርህ ጠቃሚ ሰው ትሆናለህ!!!!አንተም ወዳጀ በማይረባ የግጭት ፖስት ላይ ኮሜንት ስትሰጥ ጊዜህን ከምታባክን ግጭት ፀሀፌውን ሰይጣን እና ግጭት ተቀባዩን ግሩፕ ብሎክ በማድረግ ፌስ ቡክ ላይ ጠቃሚ መረጃወችን ብቻ ብትከታተል ብዙ ታተርፋለክ!!!

ፈጣሪ ሆይ ግጭት ፈጣሪወች የሚሰሩትን እና የሚያተርፉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው!!!!

LEAVE A REPLY