ክፍል ፪ …
የምኒልክ ጦር ጣልያን ከምሽጉ እንዲወጣ የተዘየደው ነገር በኢጣሊያኖች የሚታመን የኢትዮጵያ ሰው በኩል የተሳሳተ መረጃ በማቀበል ከምሽጋቸው ወጥተው ውጊያውን እንዲጀምሩ ማድረግ ነበር። ይህንንም ለጀግናው የጦር አለቃ ራስ አሉላ አባነጋ አማከሩና ራስ አሉላ ቀድሞ ለራሳቸው እና በኋላም ለጣሊያን ስለላ ይሰሩ የነበሩ አውአሎም የተባሉ ነጋዴ ጣልያንን መረጃ እንዲያስቱ በእርቅ ከአፄ ምኒልክ ጋር እንዲገቡ ተደረገ።
አፄ ምኒልክም ይቅርታ አድርገውላቸው እቴጌ ጣይቱም በእህል ውሀ ሰበብ “አውአሎም ይህ የምትበላው እንጀራ ቁርባን ነው” ብለው በአፄ ምኒልክና በመኳንንቱ የተዘጋጀውን ወጥመድ እንዲፈጽሙ አስማሏቸው። ለጣሊያኑ ጄነራል ‘ኢትዮጵያኖች በእለተ እሁድ ቤተክርስቲያን የመሳለም ልማድ ስላላቸው፤ የካቲት 23 ሰንበትም ብዙው ወታደር አክሱም ፅዮን ለመሳለም ስለሚያቀና የቀረውም ምግብ ፍለጋ በመበተኑ ንጉሠ ነገሥቱ ብቻቸውን ይሆናሉ በጠዋት ማጥቃቱ ቢጀመር ድሉ ያለምንም ጥርጣሬ የጣሊያን ይሆናል” ብሎ አሳመነ።
በዚህም የጠላት ጦር ንጉሠ ነገሥቱን ብቻቸውን ሊወጋ ቋምጦ ሲገሰግስ ከዐድዋ ሠፈር ተቃረበና ጧት በዐሥራ አንድ ሰዓት ርችት አሰማ። የምኒልክም ሠራዊት አድፍጦ ሲጠባበቅ አድሯልና አፀፋውን መለሰ። በዚህ ጊዜ አፄ ምኒልክ የዐድዋን ጦርነት ከፈቱ።
ጦርነቱ ሲፋፋም አውአሎምና ጓደኛው ወደ ወገናቸው ጦር ሲቀላቀሉ ያየና ነገሩ የገባው ጄነራል “አውዓሎም አውዓሎም” እያለ ሲጣራ አውዓሎም ሰምተው “ዘወአልካዩ እያውዕለኒ” ብለው አፌዙበት። (በዋልክበት አያውለኝ እንደማለት ነው) ዉጊያም በግማሽ ቀን ተጠናቆ ቀኑን ሙሉ ምርኮና አስክሬን ሲሰበሰብ ውሎ ከምሽቱ በዐሥራ ሁለት ሰዓት ድሉ የኢትዮጵያ መሆኑ ታወቀ።
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia