/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/:- በመጥፎንቱ በሚታውቀው ማእከላዊ እና አዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የንበሩ ምረማሪ ፖሊሶች ወስጥ አስሩ በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንድተመሰረተባችው የጠቅላይ አቃቢ ህግ ጽህፈት ቤት ይፋ አደረገ::
እንደ ጽህፈት ቤቱ ገለጻ ተከሳሾች ወንጀል መርማሪ ሆነው በሰሩበት ወቅት ታሳሪ የግል ተበዳዮችን
– በኤሌክትሪክ ገመድ በመግረፍ
– በብረት ጉጠት የጣት ጥፍራቸውን በመንቀል
– በሽብርተኝነት ተፈረጀው ከነበሩ የአርበኞች ግንቦት ሰባት እና የኦነግ የፖለቲካ ድርጅቶች አባል ናችሁ በማለት ሽጉጥ አፉቸው ውስጥ በመክተት
– በግንብ ላይ በተሰካ ብረት ላይ ለረጅም ጊዜ እጃቸውን በካቴና በማሰርና በማንጠልጠል
– ከግድግዳ ጋር በማጋጨት
– ፊታቸውን በጥፊ በመምታት
– የፊትንና የጺም ጸጉር ፒንሳ በሚመስል ነገር በመንጨት እንዲሁም ራሳቸውን በሚስትቱበት ወቅት ውሃ በመድፋት በግድ የአሸባሪ ድርጅቶች አባል መሆናቸውን እንዲያምኑ በማድረግ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመፈጸማቸው ለፍርድ መቅረባቸውን አቃቢ ህግ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል::
አስሩ ተልከሳሾች
1 – ኮማንደር አለማየሁ ሐይሉ
2 – ዋ/ሳጅን እቴነሽ አረፋይኔ ወልደ ሚካኤል
3 – ዋ/ሳጅን ኪዳኔ አሰፋ ሸማ
4 – ዋ/ሳጅን ርእሶም ክህሽን
5 – ኢ/ር ፈይሳ ደሜ በዳዳ
6 – ም/ኢ/ር የሱፍ ሃሰን መኮንን
7 -ም/ኢ/ር ምንላርግልህ ጥላሁን
8 – ረ/ኢ/ር መንግስቱ ታደሰ አየለ
9 – ረ/ኢ/ር አለማየሁ ኃይሉ ሁንዴ
10 – ኢ/ር ስንታየሁ ፈጠነ ለገሰ መሆናችውን የግለጸው ጠቅላይ አቃቢ ህግ ላልፉት ስምንት አመታት በሰሩበት የምርመራ ስራ አስቃቂ የሆኑ የምርመራ ስልቶችን በመጠቀም የፍጸሙትን ድርጊት ገልጿል::
በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ አሰቃቂ ምርመራዎች ስለመፈጸማችው በተለይ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጦች እና አለም አቀፍ ተቋማት ለረጅም አመታት ሲወተውቱ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት የፈጠራ ወሬዎች ናቸው በማለት ሲያስተባብል እንደነበር አይዘነጋም:: ዛሬ ለረጅም አመታት ሲፈጽሙ እንደነበር በማመን የፌደራል አቃቢ ህግ በተከሳሶች ላይ 78 ክሶችን የያዘ መዝገብ መክፈቱንና በግል ተበዳዮች ላይ ምርመራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ተበዳዮች ላይ የተፈጸሙ መከራዎችን አስታውቋል::
– እጃቸውን በካቴና በማሰር
– በምርመራ ክፍል ውስጥ በተዘጋጀ ሚስማር ላይ በማጠልጠል
– በጣት እንዲቆሙ በማድረግ
– በኤሌትሪክ ገመድ በመግረፍና በግንባር ግድግዳ በማስገፋት
– በብልታቸው ላይ ከ2 እስከ 4 ሊትር ሃይላንድ ውሀ በማንጠልጠል ከ2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት እንዲቆዩ በማስደረግ
– በኤሌክትሪክ በማስነዘር
– ብልታቸውን በፒንሳ በመሳብ የጭንቀት ህመም እና ተያያዥ ድብርት እንዲደርስባቸው አድርገዋል
በማለት ክሶቹን የዘረዘረው አቃቢ ህግ ከዚህም በተጨማሪ:-
– በቀዝቃዛና ጨለማ እስርቤት ውስጥ በማሰር
– በእግራቸው መሀል እንጨት አስገብቶ በመገልበጥ የውስጥ እግራቸውን በኤሌትሪክ ገመድ በመግረፍ
– በምርመራ ክፍሉ በተዘጋጀ ሚስማር ላይ በማንጠልጠል ለረዥም ሰዓት እንዲቆዩ በማድረግ
– አድካሚ እና ከባድ ስፖርት በማሰራት
– አፍንጫው ውስጥ እስክሪብቶ በመክተት
– መቀመጫቸውን እና ጀርባቸውን ውሃ እየደፋ በኤሌክትሪክ ሽቦ በመግረፍ
– ጺማቸውን በመንጨት
– ብልታቸውን በቀጭን ሲባጎ በማሰር በግል ተበዳዮች ላይ ሞራላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት አስከትለዋል በሚል ክስ የተመሰረተባችው መሆኑን ለመረዳት ተችሏል::
አቃቢ ህግ በርካታ ምስክሮችን በይፋ እና ይፋዊ ባልሆነ መልኩ እንደሚያቀርብ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን በእስር ከተሰቃዩት ወጣቶች መካከል አሸናፊ አካሉ የደረሰበትን በደል በይፋ ለመመስከር ዝግጁ መሆኑን ገልጾልናል::