ኢትዮጵያ ነገ ዜና | በአዲስ አበባ ዲጂታል የነዋሪዎች መታውቂያ በሚቀጥለው ሳምንት መሰጠት እንደሚጀመር ተገለጸ::
የከተማዋን ነዋሪዎች የመታወቂያ አጠቃቀም ዘዴ ያሻሽላል ተብሎ የታቀደውና በብዙዎች ዘንድ ሲጠበቅ የነበረው ይህ አዲስ የመታወቂያ ካርድ አሰጣጥ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚቀጥለው ሳምንት መሰጠት እንድሚጀምርና የአሰጣጡና ሁኔታ አዋጭነት እንዲሁም ድከመትና ጥንካሬ ታይቶ በቀጣይ በመላ አዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች መታደል እንደሚጀመር የከተማዋን ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።
ይህንን ወቅታዊና ዘመናዊ አሰራር አስፈላጊንት ያደንቁ አስተያየት ሰጭዎች የከተማዋ የአኗኗር እንዲሻሻል እገዛ ያደርጋል የአፍሪካ መቀመጫ እንደሚሆኗም ከስልጣኔ ጋር ከተማዋ የምታደርገው እንቅስቃሴ ከዚህ በተሻለ መልኩ መቀጠል አለበት ብለዋል።
በአንጻሩም ይህ የደም ዓይነት እንጂ የብሔር ማንነትና የትውልድ ቦታ የሚገልጽ ይዘት የሌለው መሆኑ የተገለጽው ይህ አዲስ የመታወቂያ ካርድ በቀጣይ የሀገር አቀፍ ሀዝብ ቆጠራ ላይ ሊያስከትል የሚችለው ውዝግብ በምን ምልኩ እንደሚፈታ ጥናት ስልመደረጉ ያሳሰባቸው መሆኑንና የካርዱ አሰጣጥ ብዙ ፈተናዎች ሊጥብቀው እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ስጋታቸውን ገልጽዋል::
ካርዱ በሚታደልበት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ እንከኖችን ለማስወገድ ሁኔታዎች የተመቻቹ ሲሆን በተለይ የኢንተርኔት መቆራረጥ እንዳያጋጥም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።