በአይጥ ወጥመድ የተያዝን ድመቶች ሆንኮ! | ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ

በአይጥ ወጥመድ የተያዝን ድመቶች ሆንኮ! | ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ

“ጋዜጠኛማ ይህን ታሪክ ማወቅ አለበት” እያሉ ነው መሰል፣ አንዳንድ ሰዎች የሚያካፍሉኝ ገጠመኞች ለታሪክ የሚበቁ ቁምነገሮች ሁነው አገኛቸዋለሁ።

አንድ ጊዜ ከወዳጄ ዶ/ር ፍስሃ አበበ ጋር ተገናኘተን ስንጫወት፣

“እኔና መለስ ዜናዊ በአንዲት ክፍል በጀኔራል ዊንጌት አብረን ተምረናል” አለኝ።

ታድያ በአመቱ የትምህርት ዘመን መጨረሻ ሁሌ እንደሚደረገው፣ ተማሪዎች የተለያዩ ባህላዊ ትርኢቶችን እናቀርባለን። የትግራይ ባህላዊ ጨዋታ ለማቅረብ፣ አንድ አበራ አብርሃ የሚባል ጎበዝ የክፍላችን ልጅ ተነስቶ ስም ሊመዘግብ፣ “ከትግራይ የመጣችሁ እጃችሁን አውጡ” ይላል።

ከትግራይ የመጡ እጃቸውን ሲያወጡ፣ ሁሌም ከፊት መደዳ የሚቀመጠው መለስ ዜናዊ (ያኔ ለገሰ ዜናዊ) እጁ ሳያወጣ ይቀራል። ረጅሙ አበራ ደግሞ ከሥሩ የተቀመጠውን ለገሰን ቁልቁል እያየ፣ “የትግራይ ልጅ አይደለህም እንዴ? ለምን እጅ አላወጣህም?” ይላል።

መለስ ደግሞ፣ “እኔ የትግራይ ልጅ አይደለምሁ፤ ኤርትራዊ ነኝ” ይለዋል።

ግራ የገባው አበራ አብርሃምም፣ “ከአድዋ አይደለህም እንዴ የመጣኸው?” ሲለው፣

“ከአድዋ ብመጣም፣ ትውልዴ ኤርትራዊ ነኝ አልኩህኮ” ሲል በክፉሉ የነበርን ተማሪዎች ታዝበናል።

ታድያ ብዙ አመት አለፈና፣ ደርግ ወድቆ ወያኔ አዲስ አበባ ገብቶ የወያኔ መሪ ተብሎ መለስ ዜናዊ በቴሌቭዥን ብቅ ሲል “በጣም ነበር የደነገጥኩት። የትግራይ ልጆች ተበሉ” ነበር ያልኩት።

ስልጣን እንደያዘ ወድያው “ባንዴራውኮ ጨርቅ ነው” ሲል፣ አልገረመኝም። በለስ ቀንቶት አገር የማፈራረስ ስራውን እንደጀመረ ገባኝ።” ብሎ ትዝታውን ደመደመ።

መለስ ያጠመደልንን የዘር ፖለቲካ ዛሬ የት እንደደረሰ እያየነው ነው። “አዲስ አበባ ባለቤትዋ የዚህ ዘር ነው” እስከማለት ተደርሷል። ይህ ፉጹም እብደት ነው። አብሮ የሚያኗኑር አይደለም። ጠላት የራሱን ወጥ እንዲጣፍጥ ብሎ ‘ኦሮሚያ’ የሚባል አገር ፈጥሮ ሄዷል። ይህ የጠላት ወጥመድ መሆኑን አውቀን በተለይ የኦሮሞ ልሂቃን ወጥመዱን ድምጥማጡ በማጥፋት ቀዳሚ ሚና መጫወት አለባቸው። እንኳን አዲስ አበባ፣ ደብረዘይት፣ ናዝሬት፣ ጅማ፣ ሀረር ድሬዳዋ ወዘተ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ከተሞች እንጂ የኦሮሞ ብቻ መባል እንደ ወንጀል መቆጠር አለበት። በየትም አገር በዘር ፖለቲካ መደራጀት በወንጀል ያስከስ ሳል። በኢትዮጵያም በዘር መደራጀት በህግ መከልከል አለበት። ኢትዮጵያችን እንደ ሀገር ልትቀጥል ከሆነች የኢትዮጵያ ጠላት የዘረጋው የዘር ፌዴራሊዝም መረብ ዶግ አመድ መሆን አለበት። ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ ኢትዮጵያ ወደ ቅድመ መለስ/ህወሃት ወደ ነበረችበት አስተዳደር ስትመለስ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች!

LEAVE A REPLY