ይኸ እስልምናን የሚያሰድብ ሰው ነው | ሞሐመድ አሊ ሞሐመድ

ይኸ እስልምናን የሚያሰድብ ሰው ነው | ሞሐመድ አሊ ሞሐመድ

ይኸ እስልምናን የሚያሰድብ ሰው ነው። ይኸ ሰው ሙስሊም መስሎ መታዬት የለበትም። እስልምና የእሱ መቀለጃም መሆን የለበትም። በእስልምና የምትጠየቀው ስለሰው ሐቅ እንጅ ስለብሔርህ አይደለም። ለወንድምህ/በወንድምህ ላይ ምን አደረግህ? እንጅ ለብሔርህ ምን አደረግህ? ተብለህ አትጠየቅም። ይኸ ሰው ግን ጨርቁን የጣለ ብሔርተኛ/ዘረኛ ነው። ታላቁ ነብያችን መሐመድ (ሰዐወ) “ዘረኝነት ጥንብ ናት – አትቅረቧት” ያሉት ለእሱ ምኑም አይደለም። ደግሞም ብሔሬ/ዘሬ ለሚለው አይጠቅመውም። የያዘው አቅጣጫ አደገኛ ነው። እሱ በእሳት ነው የሚጫወተው።

በእስልምና የሰውን ሐቅ መንካት/መውሰድ አይፈቀድም። ኮንዶሚኔም ቤት የተገነባው ድሆች ከልጆቻቸው ጉሮሮ ላይ ነጥቀው በቆጠቡት ገንዘብ ነው። ይኸ ቤት የነሱ ሐቅ ነው። ቤቱ የተሠራው በእኛ መሬት ላይ ነው የሚል ክርክር ታቀርብ ይሆናል። ግን መሬቱን ላንተ ማን ሰጠህ? ወይስ ዛሬ ባለጊዜ ስለሆንክ በጉልበት ያሻህን ታደርጋለህ? ነገ ግን ሌላ ቀን ነው።

ሰው እንኳን ባገሩ አውሮፓ አሜሪካ ሂዶ መሬት ገዝቶ ቤት ይሠራል። መጤ/ሰፋሪ ተብሎ አገሩን ለቅቀህ ውጣ አይባልም። ይህች ምድር/ኢትዮጵያ ግን አያት ቅድመ-አያቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው ያቆዩዋት የጋራ ቤታችን ናት። ማንም ወደኋላ ሂዶ ታሪክ ጠቅሶ አገሩ የኔ ብቻ ነው ማለት አደጋ አለው። ልንገርህ አደጋ አለው!!!

ይህ ማለት ግን ገበሬው ተፈናቅሎ የትም ይውደቅ ማለት አይደለም። ለገበሬዎች ተገቢው ካሳና መቋቋሚያ መከፈል አለበት። እኔ ከዚህም በፊት ብያለሁ። በከተማ መስፋፋት ሳቢያ ገበሬዎች የተፈናቀሉት በአዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ አይደለም። ችግሩ አገራዊ ነው። ስለሆነም አገራዊ መፍትሔ ይፈልጋል። አንተ ግን መንግሥትንና ሌላውን ህዝብ አስገድደህ ከሌላው ሁሉ የተለዬ ነገር እንዲደረግልህ ትፈልጋለህ። ከጀርባ ሆነህ የሌሎችን ቤት እያስፈረስክ ህፃናትና አቅመ ደካሞች ያለመጠለያ ሜዳ ላይ እንዲወድቁ; መጠጊያ አጥተው እንዲንከራተቱ ታስደርጋለህ። ግን የነሱ እንባ ይፋረድሃል። እንባቸው ጎርፍ ሆኖ ይወስድሃል።

የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ የእጅህን ማግኘትህ አይቀርም!!!

LEAVE A REPLY