ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ያልተዘመረላት ጀግና | ኃይለ ገብርኤል

ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ያልተዘመረላት ጀግና | ኃይለ ገብርኤል

ከኤልያስ ገብሩ ገፅ የተወሰደ

አመታዊው የሴቶች ቀን ሲታሰብ ልትወሳ ሊነገርላት የሚገባ ጀግኖች እንስቶቻችን መካከል አንዷ፣ ያልተዘመረላት ጀግና ሰርካለም ፋሲል ናት።

ሰርኬ ጋዜጠኛ፣ ታጋይ፣ የጀግና ታጋይ ሚስት፣ የልጅ እናት፣ በአሰቃቂው የወያኔ ማጎሪ ከነእርጉዝነቷ በግፍ ታስራ በመከራ እስር ቤት ውስጥ የወለደች ስለሃገርና ሕዝብ መብት ስትል ከፍ ያለ መስዋዕትነት የከፈለች የማትሰበር ጀግና ኢትዮጵያዊት እህታችን ነች። የሴቶች ቀን ሲታሰብ በብሄራዊ ደረጃ ሊንገርላት የሚገባ የሰብዓዊ መብት ታጋይ ነች።

ብዙዎች ሰርኬን የሚያውቋት የጀግናው እስክንድር ሚስት በመሆኗ ነው። ሰርኬ ግን ከባሏም በላይ ጽናትና ቁርጠኝነት የነበራት ደፋርና ኩሩ ጋዜጠኛና ታጋይ ነበረች።

ሰርኬ የልጅ እናት ሆና ከትግሉ ግንባር ዘወር ብላ በስደት ላይ ብትሆንም፣ ስለሃገር ስለወገን ያላት ቁጭት በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ውድ ባለቤቷን በግፍ አስረውት የነበሩት ወያኔዎች በተለያየ ግዜ ባሏ ይቅርታ ጠይቆ እንዲፈታ ሊያግቧቧት የጠየቁ ቢሆንም፤ ብርቱዋ ሰርኬ ፍክንች ሳትል ባሏ እስክንድር በጀመረው ጽኑነት እስከ መጨረሻው እንዲገፉበት የመከረች ደፉር ጽኑና የመርህ ሰው ነች።

ሰርኬ እስክንድር ከተፈታም በኋላ በትግሉ ለመቀጠል ሲወስን ጎበዝ ብላ ያበረታች፣ ልጅ የማሳደግ ሃላፊነት ለብቻ ቢከብድም የዴሞክራሲ መብት እስኪረጋገጥ ያለውን ቤተሰባዊ ሸክም ለብቻዋ ይዛ ውድ ባለቤቷን መርቃ ወደ ትግሉ ግንባር የሸኘች አምሳያ የለሽ የሴት ጀግናችን ናት።

ሰርኬ፡- የጽናት፣ የቁርጠኝነት፣ ያልሰበር ባይነት፣ የመርህ ሰውነት ኩሩና ደፋር እህታችን የሴቶች ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ ሁሉ ተምሳሌት ነሽና እንኮራብሻለን እንወድሽለን።

እግዚአብሄር አምላክ ያንችንና የባለቤትሽ እስክንድርን ቅንና በጎ መንፈስ ሃገር መውደድና ሕዝባዊነት ለሁላችን ያድለን!

መልካም የሴቶች ቀን!
ሜይ ደይ!

የወንድ የበላይነት በናኘበት ባህላችን!

ግለኝነት በነገሰበት

የሴቶች ቀን!
Haile Gabriel (ሃይለ – ገብርኤል)
#ኢትዮጵያ!
#ዓለም!

LEAVE A REPLY