የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ (ቲም ለማ) ለውጥ ከዩጎዝላቪያና ራሽያ ለውጥ ጋር ይመሳሰላል |

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ (ቲም ለማ) ለውጥ ከዩጎዝላቪያና ራሽያ ለውጥ ጋር ይመሳሰላል |

| ብርሃነመሰቀል አበበ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ (ቲም ለማ) በኢትዮጵያ እያመጡት ያለው ለውጥ በምስራቅ አውሮፖ እና በሶቬት ህብረት ከ1989 ጀምሮ ከተካሄደው liberalization ጋር በብዙ መልኩ ይመሳሰል። ስር ነቀል ነው። ነፃነት አይቶ ለማያውቅ ህዝብ ነፃነትን ፈንጥቋል።

እየገጠመን ያለው አደጋም ተመሳሳይ ነው። ለምሳሌ ያህል በሶቬት ህብረት እና በዮጎስላቪያ የሆነውን እንመልከት።

1ኛ) በሶቬት ህብረት ሚካኤል ጎርቫቾቭ ወደ ሰባ ዓመታት ስልጥን ላይ ከነበረው እና ከበሰበሰው የሶቬት ኮሚንስት ፖርቲ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ፖርቲው እና አፋኝ ስረዓቱ አገርቱን በዚያ መንገድ ማስቀጠል እንደማይችል በመገንዘብ ሁለት ስር ነቀል የለውጥ ፖሊሲ liberalization (glasnost) እና የመዋቅር ለውጥ(perestroika) አደረገ። አዲሱ ለውጥ ስር ሳይሰድ ከሶቬት ኮሚንስት ፖርቲ(ኢህዲግን የሚመስለው) የተረከበው አሮጌው ስረዓት ፈረሰ። በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ሶቬት ህብረት በእጁ ፈረሰች። የሚካኤል ጎርቫቾቭ የለውጥ ሂደት በመንገድ ላይ ቀረ። አሁንም ያ ጠባሳ በራሺያ እና የአከባቢው አገሮች ላይ እንዳጠላ ነው።

2ኛ) ሁለተኛው ምሳሌ የዩጎዝላቪያ ጉዳይ ነው። ዩጎዝላቨያም ልክ እንደ ምስራቅ አውሮፓ አገሮች ሁሉ liberalize እና democratiz ለማድረግ ጉዞ ጀመረች። ዩጎዝላቪያ በወቅቱ ስድስት በፌዴራል መዋቅር የሚተዳደሩ ክልሎች ነበሯት። ክልሎቹ ልክ እንደ ኢትዮጵያ በብሄር ላይ የተመሰረቱ ነበሩ። ለውጡ ሲመጣ በስድስቱም ክልሎች ብሄርተኞች ምርጫ ምርጫ አሉ። አገራዊ ይዘት የነበረው እና በስልጣን ላይ የነበረው የዩጎዝላቪያ ሶሻልስት ፖርቲ ለክልል ብሄርተኞ አጎብዲዶ ምርጫ አደረገ። ብሄርተኞቹ በየክልሉ አሸነፉ። ኢህዴግን የሚመስለው የዩጎዝላቪያው ሶሻልስት ፖርቲ በምርጫው ተሸነፈ፣ የዩጎዝላቪያው መዕከላዊ መንግስት ፈረሰ። በየክልሉ ያሸነፉት ብሄርተኞቹ መቷኳስ ጀመሩ። ዩጎዝላቪያ ፈረሰች። በዚያ አገር ላይ የደረሰው እልቂት ከሁለተኛ አለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፖ ከተፈፀሙ እልቂቶች ከፍተኛው ነው።

ከነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ኢትዮጵያ ቢያንስ አራት ትምህርቶችን መውሰድ ትችላለች።

1ኛ) ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ማመንዥግ የተሳነው አሮጌው ኢህዲግ በእጃቸው ሳይፈርስ፣ የለውጥ ኃይሎችን በፍጥነት አደራጅተው ለውጡን መሬት በማስያዝ፣ አሁን ያላቸውን የህዝብ ድጋፍ ይዘው እና አጠናክረው የጀመሩትን ለውጥ ማስቀጠል።

2ኛ) አሁን ያለገደብ የተለቀቀው ጥግ የደረሰ liberalization በኣናርክቶች እና በፅንፈኞች abuse ተደረጎ የተገኘው ነፃነት እና የመጣው ለውጥ ተጨናግፎ እንደ ሶቬቶቹ መረን ሳይወጣ ሉጓም ቢበጅለት እና የ Liberalization ኑ ሂደት ተጠያቂነት እና ኃላፊነት የተሞላበት እንዲሆን ህጋዊ እና ተቋማዊ እንዲሆን ማድረግ።

3ኛ) በለውጡ የተፈጠረውን መዕበል ተሳፍሮ ስልጣን ለመያዝ በመቋመጥ ሌት ተቀን ለምርጫ እንደ ዩጎዝላቪያው ብሄርተኞች የሚያቃስቱት ራሳቸውንም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ ለአደጋ እንዳያጋልጡ አገሩን ከምርጫ ፖላቲካ ወደ አገር ግንባታ ፖላቲካ በማሻገር ማስከን እና ህዝብ ምክንያታዊ ምርጫ እንዲያደርግ በቂ ጊዜ መስጠት። እስከዚያ ድረስ ህዝባዊ መንግስት ለማቋቋም የሚያስችል የህዝቡን የኢኮኖሚ፣ የፖላቲካ እና የማህበራዊ ችግሮች በዘላቂነት በሚፈቱ የተቋም ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረግ እና ኢትዮጵያን ከሶቬት እና ዩጎዝላቪያ አደጋ አይነት መታደግ። የኢትዮጵያ ችግሮች በምርጫ እንዳልተፈጠሩ ሁሉ በምርጫ እንደማይፈቱ ተገዝቦ፣ የምርጫ ማግስት ግጭት ውስጥ ገብተን በምርጫ የማንፈታቸው ችግሮችን ይበልጥ ከማወሳሰብ ተቆጠበን ሌሎች የኢትዮጵያ ችግሮችን መፍቻ መንገዶችን በማፈላለግ ለዘላቂ ህዝባዊ አንድነት፣ሰላም እና እድገት መስራት ።

4ኛ) በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄዎችን ሙሉ በሙሉ በሽግግሩ ወቅት በመመለስ ህዝቡን እና አገሩን ወደ ኢትዮጵያ አቀፍ civic(national) identity በማሸጋገር constitutionally patriotic የሆነች ህዝባዊና ዲሞክራሳዊ ስረዓት በመገንባት ኢትዮጵያን በፀና መሰረት ላይ ማቆም።

LEAVE A REPLY