የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተከስክሶ የ33 ሃገራት ዜጎች አልቀዋል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተከስክሶ የ33 ሃገራት ዜጎች አልቀዋል

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የበረራ ቁጥር ET302 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ባጋጠው የመከስከስ አደጋ ተሳፋሪዎቹ ሙሉ በሙሉ ህይወታቸውን ያጡ መሆኑ ተዘገበ።

አሳዛኙ አደጋ የተከሰተው አውሮፕላኑ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ኬንያ በመምራት ላይ እያለ ነው።

ምድርን ከለቀቀ በስምንተኛው ደቂቃ የተከሰከሰው አሜሪካን ሰራሽ ቦይንግ 737 የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 157 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረ ሲሆን  የ33 ሃገራት ዜግነት ያላቸው እንደነበር ዘገባዎች አስረድተዋል።

አውሮፕላኑ ከደቡብ አፍሪካ ጀዋንስበረግ አዲስ አበባ በሰላም ገብቶ ለመልስ በረራ ወደናይሮቢ ጉዞ በማድረግ ላይ እንደነበር ታውቋል። የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን እንዳልታወቀና በማጣራት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ተወልደ ተናግረዋል።

አውሮፕላኑ በተከሰሱበት ስፍራ ተገኝተው ሃዘናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሞቱት ወዳጅ ዘመዶች ሁሉ መጽናናትን በመመኘት ለሟች ቤተሰቦች ማናቸውም ተገቢ ነገሮች እንዲደረግ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ታውቋል።

ህይወታቸው ያለፉት ተሳፋሪዎች የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸው ሲሆን ዜግነታቸውም
32 ኬንያውያን
18 ካናዳውያን
17 ኢትዮጵያውያን
8 ጣሊያናውያን
8 ቻይናውያን
8 አሜሪካውያን
7 ብሪታኒያውያን
7 ፈረንሳውያን
6 ገብፃውያን
5 ሆላንዳውያን
4 የመንግስታቱን ድርጅት ፓስፖርት የያዙ
4 ህንዳውያን
4 ስሎቫኪያውያን
3 ኦስትሪያዊያን
3 ስዊድናውያን
3 ራሻውያን
2 ሞሮኳውያን
2 ስፔናውያን
2 ፖላንዳውያን
2 እስራኤላውያን
1 ቤልጂዬም
1 ኢንዶኔዠያ
1 ኡጋንዳ
1 የመን
1 ሱዳን
1 ሰርቢያ
1 ቶጎ
1 ሞዛምቢክ
1 ሩዋንዳ
1 ሶማሊያ
1 ኖርዌይ
1 አየርላንድ
1 ሳዑዲ አረቢያ

መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY