አገራችን ኢትዮጲያና ህዝቧ ለ27 አመታት ነግሶባት የነበረውን የአገዛዝ ስርእት በሰላማዊ የ ህዝብ ትግል ለመጣል ከፍተኛ ትግል የተደርገ ቢሆንም በስተመጨረሻ ለውጡን በመንግስትነት የሚመሩት ግን ስርአቱን የሚወክሉ “የለውጥ ፈላጊ” ወገኖች እንጂ በስርአቱ ተገፍተው በይፋ ሲታግሉት የነበሩ ስዎች ወይም የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም የህዝብ ተውካዮች አይደሉም። ሆኖም ግን ለውጥ የሚፈልገው የተጨቆነው ህዝብ ከስርአቱ ከመጡ በመንግስት ዙፋን ላይ በተቀመጡ “የለውጥ ፈላጊ” ወገኖች የተሰጡትን የተስፋ ቃል በመስማት በጅምሩ ሙሉ ድጋፉን ሰጥቶቸዋል።
ይህንንም ተከትሎ በለውጥ ሂደት ውስጥ መድርግ ያለባቸውን የመጀምርያ እርምጃዎችን ( እስርኞችን መፍታት የመሳስሉትን የግድ መደርግ የነበርባቸውን ጉዳዮች) ፈጽመዋል። ይህ ግን መስርታዊ የአገሪቱንና የህዝቡን ዘላቂ ችግር የሚፈታ ሳይሆን የተቆጣ ህዝብን ስሜት የሚያበርድ ድርጊት ነው። የለውጥ መሪዎቹ የሽግግር ግዜውን ሁሉንም ወገን በሚወክል የህዝብና የፖለቲካ ስብስብ ከመምራት ይልቅ እራሳቸውን (ከአስከፊው ስርአት ገዥ ድርጅቶች በሚወከሉ “የለውጥ ፈላጊዎች”) የሽግግሩ መሪዎች በማድርጋቸው የሚፈለገውን ለውጥ በሙሉ ሃይልና ፍላጎት ለማምጣት እንዳይችሉ ተናንቇቸዋል። ። በዚህ የሽግግር ግዜ መሪዎች መካከል መልካም የሚመኙና አገሪቱን ለተሻለ የመንግስት ስርአት ሊያደርስ የሚያስችል ፍላጎትና ራእይ ያላቸው ወገኖችም ቢኖሩም ለብሰውት ያለው የቆሸሸና የተቀደደ ሸማ (የፖለቲካ ስብስብ) ሊያራምዳቸው የማይችልና የሚያደናቅፋቸው በመሆኑ ባሁኑ ሰአት አገራችንና ህዝቡ በመስቀለኛ መንግድ ላይ ይገኛሉ።
በተከፈተው የለውጥ ጅማሮን ተጠቅመው በተለያየ የአለም ሃገራት ተበትነው የነበሩ ወገኖች አቧራቸውን አራግፈው በ 60ና70ዎቹ ያራግቡት የነበርውን አንዱን ባንዱ የሚጫን ከፋፋይ፣ የአደፈ የፖለቲካ ድሪቶን የዘር ስብስብ ካባ አለብሰው የዘምኑንና የመጪውን ትውልድ (አብዝኛውን የህብረተስብ ክፍል) ያልተርዳ ወይም የሚጎዳ አመለካክት ይዘው በስብስባና በሚዲያ አገሪቱናና ህዝቡን ወጥርው ይዘውታል። እነሱን በሚከተል የተደራጀ ሃይል በማን አልበኝነት ተነስቶ ብዙ ጥፋት፣ ግድያ፣ ዝርፊያ እንዲሁም የህዝብ መፈናቀል አድርሷል። ከስልጣን መንበራቸው ከተነሱ የገዠው ድርጅት ሰዎችና ድርጅቶች ጋር በመተባበርም ትልቅ ጥፋት በአገራችን እያደርሱ ነው። በመንግስትንት የተቀመጡት “የለውጥ መሪዎች” በሚራገበው አዲስ ትርምስ ውስጥ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክር ውስጥ ገብተው መሰርታዊ የህዝቡን የሚፈልገው ለውጥን ከመመስረት ይልቅ በውዥንበሩ ተጠልፈው አገራችንን አሁን ባልችበት መስቀለኛ መንገድ ላይ አድርሰዋታል።
የመንግስት መሪዎች የሽግግሩን ግዜ የሚመሩብትና የሚከተሉት ግልፅ የሆነ ፍኖተ-ካርታ ባለማሳወቃቸው (ወይም ስለ ሌላቸው) ለውጡን በግልሰቦች ፍላጎትና ግዜ ወይም የወቀቱ ትኩሳት በሆነ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ እንዲሆን አድርገው የሚመሩት ሆነዋል። ይህን ፀሃፊ ጨምሮ ብዙ ሰዎች ለለውጡ የሚርዱ የሽግግር እይታዎችን በጽሁፍ ቢያቀርቡም፡ አሁን የምናየው እውነታ ግን ግብታዊ የሚመስሉና አደጋ ሊቀርፉ የሚችሉ እርምጃዎች አይደሉም። ካንድ ቦታ ተንስቶ ህዝብን ጭኖ የሚሄድ መሪ (ሹፌር) የሚሄድበት ጥርጊያ መንግድ ወይም ሃዲድ ሳይሰራ ወይም ሳይኖረው በፍላጐት ብቻ የአሰበው ቦታ እድርሳልው ማለት እጅግ አድካሚ፣ ጎጂ፣ ወይም መውደቅና መስብር ሊገጥመው ይችላል።
በመንግስት ዙፋን ላይ መቀምጥ ትልቅ ሃላፊነት ነው። ከባድ እንድሚሆንና እጅግ እርጋታ፣እውቀት፣ብልሃትና ዘዴ ያስፈልገዋል። የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም ለህዝብ መልካም ነገር አመጣለው ያለ አመራር በፍላጎት ብቻ ቦታው ላይ መቀመጥ የለብትም። ለሚሰጠው ተስፋ ተግባራዊነት መሆን የሚያስችል የመንግስት መዋቅርን አስትካክሎ ማስፍጽምና ህዝቡንም ማማከር ወይም የተስፋው ተግባራዊ አካል ማድርግ ያስፈልጋል። ብዙ ተስፋ ስጥቶ ትንሽ ተግባራዊ ከሚያደርግ አመራር ይልቅ ብዙ ተስፋ ስይሰጥ ትንሽ ተግባሪዊ የሚያድርግ ውጤታማ ነው።
የ 27 አመቱን የግፍ ስርአት በዋናነት የሚመሩትን ከቤት መንግስት መንበሩ ማራቅ ጀምሮ የሚፈጸሙ የለውጥ የመጀምርያ ጅምሮችን ተከትሎ መከተል የነበርበት ዋና ጉዳይ ለ45 አምታት አገራችንን ሲነውጣት የነበርውን የጥፋትና ሁከት መሰረቶች የሆኑትን የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲን ማስቀርትና በአገርችን ህዝብ መካከል በተለይም ለ45 አማታት በተፈፀሙ የጥፋት ድርጊቶች፣ ቁርሾዎችን ዘግቶ በአዲስ መንፈስ በኢትዮጲያዊነት ሰው የምንሆንበት የይቅርታ፣ የእርቅና የመግባቢያ እርምጃዎች መወስድ ነበርባቸው። ምንም እንኳ ተስፋው በንግግር ቢገለፅልንም እና ሁላችንም በደስታ የደግፍን ቢሆንም በሃላፊነት የተቀመጡት “የለውጡ መሪዎች” እንዚሁን ተቀዳሚ ተግባራት ሳይፈሙት እስካሁን ቀርትዋል። በዚህም መሰርት የበለጠ የዘር ክፍፍልና ጥፋት፤ ከመቀራረብና እርቅ ይልቅ መራራቅን ለሌላ ጸብ የሚፈጥርን እኩይ ድርጊቶች እንዲከናውኑ እድል ሰጠውታል። እየትንደረደሩ ላለው የሚቀጠለው ምርጫ አገር ሊያሳድግ በሚያስችል ፖሊሲ ሳይሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳድሩት ባለፈው ቁርሾና ቅሬታ ላይ በተመሰረተ ልዩነት፣ ቂም በቀል፣እንዲሁም የተጋነነ የቀድሞ ታሪክ ትንታኔና የሃስት የመሬት ይገባኛል የመሳሰሉትን አስፈሪ መፈክሮች የታጀበ የምርጫ ዘመቻ ይሆናል። ይህን የግዜ እድል ሳንጠቀመው በመቅረታችን የሚያስከፍለን የህይውት፣ የንብረት፣ የመፈናቀል፣ የሰላም እጦት እዳ ለሚቀጥሉት አመታት የሚገጥመን ይሆናል።
ለመሆኑ ለህዝባችንና ለአገራችን የሚበጀን ምን ይሆን?
ምንም እንኳ ከመልካም ሽግግር መንገድ የወጣን ቢሆንም መንግዱን ለማስትካክል እድሉ አሁንም አለን። በሽግግር ግዜ መሪነት ያሉ “የለዉጥ መሪዎች” እንድሁም የህዝብ ብሶት እንወክላለን የሚሉ የፖለቲካ ስብስቦች፣ ወጣቶች ፣ ሚዲያዎች እንዲሁም ህዝቡ ሊያስብባቸውና ሊያከናውኑት የሚገባ አንኳር ቁም-ነገሮች አሉ።
ዋናውና መሰረታዊው ቁም ነገር የኢትዮጲያውያን ዜጎችን ሰው መሆን መብት ማክበር ነው። የሰው ዋናው መግልጫው ሰውነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ፍላጎቱ፣ ኑሮው፣ ህልሙ፣ ተስፋው፤ የግለስብ መብቱ፣ ጤናው ባጠቃላይ የግለስብ ከሌሎች የሚለይበት ባህሪና አስትሳስብ ያለው መሆኑ ነው። አንድን ሰው በጎሳው ጨፍልቆ ማሰቡና ለሱ በዛ መልክ መስፈሩ የሰውነት ባህሪውን መድምሰስና እንድ መንጋ ከብት መቆጠሩ ነው። ይህን መስርታዊ ተግባር አብዛኛው ሰው የሚያውቀው ቢሆንም ያን የጎሳ ስብስብ ወይም አደርጃጅት ተጠቅመው መንግስት ስርአት የሚያራምዱ ስልጣን፣ ጉልበት አና ሃብት መስብሰብ ለሚፈልጉ ጥቂት ግለስቦች ወይም ስብስቦች የሚበጅ እንጂ ለህዝቡ የሚፈይደው ነገር አልመኖሩ ነው። ሰዎችን እንድ መንጋ መቁጠሩ ከሰወ የማህብረሰብ እድግት አቅጣጫ ሲመዝን የማያዋጣና ፈራሽ ነው። ይህን በማወቅ ስዎች በዋናኘነት በዜግነታቸው ላይ የተመሰረተ ስርአት-መንግስት በመግንባት ሌሎች ልዩነት ባህሪያትን በማያጋጭ መልክ የሚያድጉብትን ዘዴ መምስረት ወሳኝ መሆኑን ማውቅና ተግባራዊ ማድርጉ ነው።
አንዳንዶች በጎሳ ላይ የተመሰረተ የመንግስት ስርአት እንገንባ ይላሉ። ይህ ጸረ-ዲሞክራሳዊ እንጂ ፍትሃው ስር አት አይደለም። ላለፈው 27 አመታት ተሞክሮ የከሸፈ ድርጊት እንደገና መሞከር የለበትም። ሰዎች በጎሳ ብቻ አይለያዩም። በሃይምኖትም ይለያያሉ። በጎሳ ፖለቲካ የተለከፉ ወገኖች ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ ሰዎች በሃይማኖት ስለምንለያይ በሃይማኖት ላይ የተመሰረተ መንግስት-ስርአት በኢትዮጲያ እንገንባ ቢባሉ መልሳቸው ምን ይሆን? በጾታ ስንምንለያይ የጾታ ልዩንትን የሚይራምድ መንግስት ወይም ስርአትም ሊባል ነው። በመልካችን ቀለም፣ በቁመታችን፣በሰውነት ክብድታችን፣በእድሚያችን ፣በሃብታች በመሳስሉት ስለምንለያይ በነዚህ ላይ መሰረት ያደርገ መንግስተ-ስርአት እንምስርት ብንል የጥፋት እንጂ የሚበጀን አይሆንም።
አገራችን ኢትዮጲያ የብዙ ቛንቋ፣ ባህል፣ ወግ፣ ሃይማኖት ያላቸው ዜጎች (ህዝብ) ስብስብ እንድመሆኗ መጠን በዘላቂነት የሚያቆየን በልዩንትቻን ላይ የተመሰረተ ስርአት ሳይሆን ሰው መሆናቸንን (ዜግነት) የሚያከበርልን ስርአት ስንምሰርት ነው። በዚህ የዜግነት ስርአት ውስጥ ልዩንቶቻችን ጤናማ በሆነ መልክ፣ በሚጠቅመን እንጂ ማንንም በማይጎዳ መልክ ልንጠብቀው ወይም ልናሳድገው የምንችልበትን ዘዴ መፈየድ እንችላለን።
በዜግንት ላይ የተመሰርተ ስርአት መሰርታዊ የሰው ልጅ መብታችንን እንዲይሳከብርልን አድርገን ከመሰርትነው ለብዝበዛና ጭቆና የሚያጋልጠን አይሆንም። የሚመሰርተው መንግስታዊ መዋቅርም ይህን ሊፍታ በሚችል መልኩ ከተደራጀ ( ፍርድ ቤት/ዳኝንት ፣ ፖሊስ/ ህግ አስክባሪ፣ ሚዲያ፣ የመናገር፣ የመሰብሰብ ፣የመጻፍ፣ ሰብአዊ መብት ጠባቂ አካል፣ ነጻ የህዝብ ምርጫ እና አጣሪ ኮሚሽን የመሳስሉት ካሉ) ሰዎች የደርሳባቸውን ግፍ ወይም አድሎ በሰላማዊ መንገድ የሚያስቆሙብትና የሚለውጡብት ሂደት ይፈጠራል። በህግ ልኡላዊነት ላይ የተመሰረት መንግስተ-ስርአት ይሆናል።
ይህንን ማድርገ ስንችል፤ ወያኔው ወስኖ ለአገዛዙ እንዲያመቸው ብሎ ያስቀመጠውን የክልል ወስን በቀላሉ በማፈርስ፤ ለእድገት ሀዝብ-ለህዝብ ለማቀራረብ የሚያመችንን፣ ኑሮችንን በተሻለ ለሚለውጥልን አዲስ የፊዴራል ክልል (states) መንግስቶችን በመምስርት ስልጣን ህዝቡ አጠገብ ማድርግ አይሳነነም።
በዜግነት የተmeሰረተ ስርአተ-መንግስት ስንምስርት እንደ ኢትዮጲያ ላለ ታሪካዊ አገር በህዝብ የተመረጠ ፕሬዝዳንታዊ መንግስት ብንመርጥ በተሻለ ሁኔታ አገሩን የሚመራውን መሪ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ የመምርጥ እድል ስለሚኖርው ህዝቡ ለዲሞክራሲያዊ ሂደት ቀርቤታ እንዳላው በማመን መልካም ስሜት ይፈጥራል። አንድ የጎሳ ፖለቲካ መሪ እንዴት ተብሎ ለኢትዪጵያዋይን ሁሉ እኩል መሪ ሊሁን ይችላል? ማንም ኢትዮጲያዊ በችሎታውና በሚያቀርበው የተሻለ የሃገር አስተዳድር ፖሊሲና ዝግጅት ከየትም ጎሳ ቢመጣ በህዝብ ቀጠታ በመመርጥ አገር ሊያስተዳደር የሚያስችል እድል ይፈጠራል።
ምንም እንኳ ማእክላዊ (ፌድራል) መንግስት መቀምጫ ከተማ ቢኖረውም ወደፊት በምንምስረትው መንግስት ሌሎች ከተሞች እንዲምስረቱና፤ የተምሰርቱትም እንዲያድጉ ከፍተኛ ጥርት መደርገ ያልበት ሲሆን ሁሉም ነገር ወደ ዋና ከተማው መድርግ የለበትም። ይህ ሌሎችን ከተሞች እድገት ያቀጫጫል፣ ድግሞም እድገትን ወደ ሌሎች ያገርችን ክፍሎች አንዳናድርግ እንቅፋት ይሆናል። የተመጣጠን እድግት ሲኖር የህዝብ ፍልሰት ራሱ መልክ ይይዝና አላስፈላጊ ውጥርቶችን እጅጉ ይቀንሰዋል። የማእክላዊ (ፌድራሉ) መንግስት የተለያዩ የሚንስቴር መስሪያ ቤቶችን በተላያዩ ከተሞቻችን ማድርግ ይችላላል። ዘመናው ቴክኖሎጅ በመጠቀም ስራን በቀላሉ ማቀላጠፍ ስለሚቻል ሁሉን ነገር ባንድ ቦታ መከምር አያስፈለግም። ይህም የፌድራል መንግስቱን በሁሉም ኢትዮጲያን ሰፈር ቅርብ ያደገዋል።
እያንዳንዱ ያስተዳድር ክፍለ-ሃገር (Federal region) እና ትላልቅ ከተሞች በህዝብ በተመርጡ የአስተዳድሩ ነዋሪዎች እንዲመራ ማደርግ ተገቢ ይሆናል። የፌድራል መንግስቱ ( states) የሚመሩ መሪዊችን (Governor) አና ከተሞችን የሚያስተዳድሩ ከንቲባዎች (Mayor) በቀጥታ በህዝቡ ቢመርጥ የትሻለ ይሆናል። ይህም ህዝቡ በቀጥታ የፖለቲካ አስተዳድር ምርጫ ሂደት ላይ የተሳታፊነት (ዲሞክራሲይዊ ሂደት) ያደርገውል።
ይቀጥላል።