ቦሌ ሚካኤል ትንሿ ኢትዮጵያ የሚያስብል የብሔር ስብጥር ይኖርባታል፡፡ ቦሌ ሚካኤል ላይ የኢትዮጵያ/የጅግጅጋ ሶማሌ፣ የሀርጌሳ ሱማሌ፣ የሀረር ኦሮሞ፣ የሸዋ ኦሮሞ፣ የአፋር የግመል ወተት ነጋዴ ምን አለፋችሁ ከእነዚህ አልፎ የሌላ ሀገር ዜጎችም ያለማዳላት ቻይኖችን ሁሉ አቅፋ ይዛለች፡፡ ቦሌ ሚካኤል ከለውጡ ወዲህ በተለይ የአንደኛው ኦነግ አመራር የሆነው ዳውድ ኢብሳ መግባት ጋር ተያይዞ ሥራቸው ላይ ሲያተኩሩ የነበሩ የሀረር ቄሮ ጫት ነጋዴዎች ቀንና ጊዜ ጠብቀው ከሚሸጡት ጫት ሥር ደብቀውት የነበረውን ሜንጫ ማውለብለብ ጀመረው ዛሬ ላይ የመጀመሪያ ፍላጎታቸውን በተግባር አሳይተዋል፡፡
የዛሬው የፀብ መነሻ ምክንያት፡- ቦሌ ሚካኤል ተወልዶ ያደገን ልጅ መኪና እንዲያሳልፉት ሲጠይቅ “አናሳልፍም!” በሚል ምክንያት #የቦሌ_ቄሮ ነን! የሚሉ ከ30 በላይ የሚበልጡ ልጆች ተረባርበው ደብድበውታል፡፡ (ከዚህ በፊት አስፖልት መንገድ ላይ የኦነግ ባንዲራን ቀለም ቀብተው ባንዲራችንን አትርገጡ! በማለት ፀብ ሊያስነሱ እንደነበር አይዘነጋም!)
ዛሬ በጠዋት የአካባቢው ወጣቶች ጋር እልክ የተያያዙት “የቦሌ ቄሮ ነን!” ባዮች የፀብ መሳሪያዎችን ገጀራም ጭምር ይዘው ከጠዋቱ ጀምሮ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ፖሊስ ዝምታን መርጦ ውሏል፡፡ የአካባቢው ፖሊስ ቀድሞም ነባራዊውን ሁኔታ ቢሰማም ምንም አይነት እርምጃ ሊወስድና ችግሩ ከመፈጠሩ በፊት ለመቆጣጠር ጥረት አላደረገም፡፡ (ይፈልገው ይኾን) በአጋጣሚ የተነሳው ፀብ ከየትመጡ በማይባሉ ሰዎች አካባቢው የተወረረ ሲሆን ከአካባቢውን ወጣት በቁጥር የሚልቅ ህዝብ ነዋሪዎች ላይ የድንጋይ ውርጅብኝ አውርዶባቸዋል፡፡
ቄሮ ነን ባዮች ሱማሌዎችን እንዲተባበሩ ሲያስገድዱና ሲያስፈራሩ ነበር፡፡ እነሱ አላረጉትም እንጂ ለፀብ ሲወጡ በሰፈሩ ውስጥ ይሄን ያህል ቄሮ አለ ወይ? እስኪባል ድረስ አጣና ላይ ምሲማር ሰክተው፣ ድንጋይ አንግበው፣ የተወሰነ ገጀራ ይዘው የወጡ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስም ፀቡን በአግራሞት ከመታደም በቀር የተሻለ ጥበቃና መከላከል ማድረግ አልቻለም፡፡ “ቄሮ ቄሮ ቄሮ ቄሮ…” እያሉ በህብረት እየጮሁ መድኃኒት ቤት፣ ህክምና ማዕከል፣ የሰው መኖሪያ ቤት እየሰበሩ “የተደበቀ ወጣት አስወጡ!” በማለት እየገነጠሉ ነበር፡፡ በፀቡ ላይ ሴቶች ሳይቀር ዘነዘና ይዘው ወጥተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ መቋቋም አቅቶት ፌዴራል ፖሊስ በመምጣት በብዙ ሃይል ለመቆጣጠር ችሏል፡፡ ፌዴራል ፖሊስ ባይመጣ የከፋ ጉዳት እንደሚደርስና ለመብረድም ይከብድ ነበር፡፡
የገረመኝ ነገርም ፌዴራል ፖሊስ ከአካባቢው ህዝብ ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ደግሞ ነዋሪ ወጣቶችን ማደን መጀመሩ ነገሩን ግራ ያረገዋል፡፡ እስካሁን በሰው ላይ ምን ያህል ሰው ጉዳት እንደደረሰ ግን ሊታወቅ አልቻለም፡፡
ባንኮች እና የተለያዩ ተቋማት በአሁኑ ሰዓት ዘግተዋል፡፡
በነገራች ላይ ባለፈው ሰናይት የምትባል የቀበሌ ሰራተኛ በሸገር ራዲዮ “መታወቂያ እየታደለ ነው!” ብላ ድምፅ ስታሰማ የነበረችው በዚሁ ወረዳ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የአካባቢው ወጣት አሁንም ከስሜት በዘለለ ከዚህ በፊት ጀምረኸው የነበረውን መደራጀት መቀጠል አለበት፡፡
የአካባቢው ህብረተሰብ ቤቱን ለገዳዩ ማከራየቱን አውቆ ከመሞት መሰንበት ቢል የተሻለ ነው፡፡
የቦሌ አየር መንገድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በፍፁም እምነት መጣል የለባችሁም፡፡ ተዋውቀናል፡፡