ሁለት እውነታዎች ስለ አማርኛ ቋንቋ || አቤል ዋበላ

ሁለት እውነታዎች ስለ አማርኛ ቋንቋ || አቤል ዋበላ

አማርኛ ማለት፣ ፕሪሞርዲያል የሆነ ማኀበረሰብ( በአጎት ልጅ፣ በአክስት ልጅ የሚዛመድ፣ በአጥንት ቆጠራ የሚለካ) ህዝብ የሚናገረው ቋንቋ አይደለም። በርከታ ሰዎች ያበለፀጉት እንደ ትላልቅ ቋንቋዎች ሁሉ የሌሎች ቋንቋዎችን ሀብት ገንዘብ ያደረገ ያደገ ትልቅ ቋንቋ ነው።

አማርኛ ማለት፣ የራሱ አልፋቤት ያለው እና በርካታ መፅሕፍት ያሉት የግዕዝ ሲቪላይዜሽን አካል ነው። በአለም የራሳቸው አልፋቤት ያላቸው ቋንቋዎች እፍኝ የማይሞሉት በአጋጣሚ አይደለም። የሰው ልጅ በመሉ ታሪኩ ደክሞ፣ አሰላስሎ፣ አዳብሮ ያቆያቸው እነዚህን ብቻ ስለሆነ ነው። ይህ ፋክት ነው። ከዚህ ጋር መጋጨት ወደኋላ መቶ አመት ወርደህ አንደምትጋጨው ሚኒልክ አይምሰለህ። ይህ የሰው ልጆች ታሪክ ነው። ምንም ማድረግ አይቻልም።

ይልቅ አፋን ኦሮሞን ለማሳደግ ብለህ ልጅህን እንግሊዘኛ እንዳይናገር እንደማትከለክለው አማርኛ አትናገር አትበለው። እንግሊዘኛም ይናገር፣ አማርኛም ይናገር፣ አረብኛም ይናገር፣ አፋን ኦሮሞም ይናገር። አፋን ኦሮሞ አንተ አንደምታስበው ልፍስፍስ ሽባ ቋንቋ አይደለም። በርካታ ፎርኮሎሮች፣ ዜማዎች እና ሌሎች ሀብቶች ያሉት ትልቅ ቋንቋ ነው። ይህ ሀብቱ እንኳን ኦሮሞውን እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ አይደለም የሌላ ሀገር ዜጋ የሚያማልል ነው።

LEAVE A REPLY