አዲስ አበባ – ኤፍ.ቢ.ሲ || የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ሰብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን የፓርቲው ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዩሃንስ ቧያሌው ገለፁ።
ሀላፊው ማዕከላዊ ኮሚቴው ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ባካሄደው ውይይት የተመለከታቸውን አጀንዳዎች እና ያስቀመጣቸውን የውሳኔ ሀሳቦች አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው ላይ እንዳመለከቱትም ኮሚቴው በስብሰባው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎችን ገምግማል።
ይህንንም መሰረት በማድረግ በቀጣይ በሚከናወኑ ስራዎች ዙሪያ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን ነው ያመለከቱት።
በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የፀጥታ ችግሮች እንደነበሩ በመመልከትም አሁን ላይ መሻሻሎች መኖራቸውን ገምግሟል።
ኮሚቴው አመራሩን ለማጠናከር የሚያስችሉ ሁኔታዎችንም በመገምገምም የፓርቲውን የተወሰነ አመራር በአዲስ የመተካት ስራ ማከናወኑም ተገልጿል።
የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶክተር አምባቸው መኮንንን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ይታወሳል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ምክትል ሊቀ መንበሩን እና አዳዲስ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚዎችን መርጧል። በዚህ መሰረት
1.አቶ ደመቀ መኮንን የአዴፓ ሊቀመንበር
2.ዶ/ር አምባቸው መኮንን ምክትል ሊቀመንበር
3.አቶ ላቀ አያሌው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ( አዲስ)
4.አቶ መላኩ አለበል የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ
5.አቶ ምግባሩ ከበደ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ
6.አቶ ዮሀንስ ቧያለው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ( አዲስ)
7.ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ
8.አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ
9.አቶ ብናልፍ አንዱአለም የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ
10.አቶ ተፈራ ደርበው የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
11.ዶክተር ይናገር ደሴ የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
12. አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
13. አቶ ፀጋ አራጌ የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው መመረጣቸውን ከአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
|| ዘገባው የፋና ነው ||