ዛሬ በሰላማዊና ህጋዊ ትግል እንቅስቃሴ፣ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) እጅግ በጣም የተሳካ ጋዜጣዊ መግለጫ ማድረግ ችሏል፣ በጽናት እና በብርቱ ትግል የተደረገም ነውና ደስ ብሎናል።
ከም/ቤቱ መግለጫ በኋላም፣ በርካታ ጥያቄዎች ከጋዜጠኞች ተነስተውም ከሁለት ሰዓታት በላይ በቂ ምላሽ ከም/ቤቱ ተሰጥቷል።
በዚህ አጋጣሚ፣ በስፍራው የተገኛችሁ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን እና ባለሞያዎችን ከልብ ከልብ እናመሰግናለን።
እንዲሁም ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመታደም የመጣችሁ በርካታ ግለሰቦች፣ መርሃ ግብሩ እንዲሳካ ደፋ ቀና ላላችሁና ሀሳቦቻችንን በመደገፍ ከጎናችሁ መሆናችሁን ገልጻችሁ በአጋርነት ለቆማችሁ በሙሉ [በሀገር ውስጥና ወጪ ሀገራት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን] በሙሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። በቅንም ሆነ በክፋት እሳቤ ተነሳስታችሁ የነቀፋችሁን ዜጎችም፣ ተጨማሪ ጉልበት ሆናችሁናል!
ሁሉንም ማድረግ የሚችል ፈጣሪም ይመስገን!
መብትህን ደፍረህና ታግለህ እንጂ ቁጭ ብለህና ፈርተህ አታስከብረውም! ሰላማዊና ህጋዊ የመብት ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ዴል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ!
#በኢትዮጵያ!
#ዓለም!