ባንድ አገር የሚኖር እጅግ ባለፀጋ፣ ትሁት፣ እግዚሓቤርን የሚፈራ ሰው ነበር። እጅግ ታታሪ በመሆኑ አባቶቹ ና እናቶቹ ባቆዩለት መሬት ላይ ጎብዞ ትልቅ ማሳ፣ የሚያስጎመጅ፣ ብዙ የእህል እንዲሁም ጥርጥሬ ምርት ነብረው። መልካም ምድርም ስለነብር ጥሩ ፍራፍሬም ያፈራ ነበር። ደግሞም የሚያማምሩ ቁጥርቸው የበዛ ከብቶች በጎች፣ ፍየሎች፣ ዶሮውች፣ ፈርሶች፣ በቅሎዎችእንዲሁም አህዮች ሁሉ ነበሩት።
የቤቱን ጎጆውች በሰፊው አሳምሮ ስለሰራቸው ያየው ሁሉ የሚቀናበት ነበር። ከአባቶቹም ከወርሰው፣ በሱም ጉብዝና ያገኘውን መልካም መሬት የውሃ ምንጭ ሁሉ ድህና አደርጎ አጥሮ ይጠብቀውም ስለነበር ማንም ደፍሮ እርሱ ማሳ አይገባም ነበር።
መልካምም ሰው ስለነበር እግዜሃቤር ባርኮት ከሚወዳት ሚስቱ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ነበሩት። ልጆቹንም አጎብዞ በላቡ ያገኘውን፣ እግዚሃቤርም የባረከለትን ሀብት እይተጠቀሙ ደስ ብሎቸው ብዙ ዘመን ይኖሩ ነበር።
ታድያ ሰነፍ የሆኑ ብዙ ምቀኞች ከቅርብም ጎርቤት ከሩቁም ነበርበት። በእሱ ዘንድ ያለውን እህል፣ ወተት፣ ማር፣ ከብቶች እያዩ አይናቸው ይቀላ ነበር። ሊሰርቁትና ሊዘርፉት ብዙ ግዜ ሞክረው እሱና ሚስቱ ልጆቹም ጎብዘው እየገርፉ ያባርሯቸው ነበር። የራሱ ድርሻ ከሆነው ውጪ ግን የነርሱን ሃብት ሳይነካ ብዙ ዘመን ይኖር ነበር።
እጅግም ደግ ስለ ነበር የተራቡና፣ የተጠሙ፣ እንዲሁም ሀይለኞⶭ የሚያሳድዷቸውን የሰው ዘር ሁሉ መጠለያ እየሰጠ፣ እየምገበ፣ የቆሰሉትን እያከመ ያኖርቸውም ነበር። አመስግነው ወደ አገርቸው የሚሄዱትንም ስንቅ ሰጥቶ ይሸኛቸውም ነበር።
እግዚሃቤርንም የሚፈራ የአባቶቹን ሃይማኖት ተከትሎ በጦም ና በጸሎትም ተግቶ የሚኖር መልክማ ሰው ነበር። መልካምም ሰው ስለ ነበር እግዚአቤር አብልጦ ባርኮት እጅግ ሃብታም ሆኖ ከነ ልጆቹ ብዙ ዘመን ኖረ።
ሰው ነውና እያረጀ እየደከመ መጣ። ያባቶቹን አገርና ሃብት ለልጅ ልጆቹና ለወደፊት ትውልድ ተጠብቆ ይኖር ዘንድ ልጆቹን የበለጠ ብልሃት፣ የዘመኑንም ስልጣኔ ይማሩለት ዘንድ የተወሰኑትን ባህር ማዶ ለቀለባቸው ፣ ለሚማሩበት፣ ለሚኖሩበት ገንዝብ አሲዞ ላካቸው። ከእነርሱም አንድ አንዶቹ መልካሙን ነገር ከመማር ይልቅ ሌላ ያልተግባ ባህልና ትምህርት፣ እግዚሃቤርንም የሚከደውን ሁሉ ተማሩ። አባታቸውም አረጀና ደክሞሞተ። ሚስቱም፣ ልጆቹም፣ የሚወዱት ወዳጆቹሁ ሁሉ አዘኑና ወደመጣበት ምድር አሳረፉት።
የሚመቀኙት ጠላቶቹ ግን እጅግ ደስ አላቸው። ደስም ብሏቸው ጮቤ ረገጡ። ያን ለዘመናት ይቋምጡለት የነበርውን የደጉን ሰው ለምለም መሬት ፣ የውሃ ምንጭ፣ ከብቶቹን ሁሉ ሃብቱን ለመቀራመት ቋመጡ። ጥፍራቸውንም አሾሉ፤ ጥርሳቸውንም አንግጫገጩ። እንዴት አድርገው ያን ሃብት በእጃቸው እንድሚያደርጉት አሰቡ መከሩ። እንደ ድሮው ልማዳቸው ጦር ሰብቀው ለመዘርፍ ሲሞከሩ ጎበዞቹ ልጆች ያባታቸው እልፈት ሃዘን ገና ባይወጣላቸውም፣ ጎብዘው ተከላክለው አባረሯቸው። እንዚም ምቀኞⶭ ሌላ ዘዴ ና ተንኮል መፈለግ ጀመሩ።
ምቀኞቹ መክረው፣ አጥነትው የደርሱበት ብልሃትና ተንኮል አስደሰታቸው። ለዚህም የሚረዳ ገንዝብ፣ ሃብት ሁሉ አዋጡ። የዛን መልካም ሰው ልጆች ወንዳማማቾቹን እህትማማቾቹን አንዱን የጠቀሙ እየመስሉ ክፉ ምክር እየመከሩ፣ እረስ በርስ እንዲጣሉና ህብረታቸው፣ ጥንካሬያቸው የሆነውን አንድነታቸውን እንዲፈርስ መከሩ።
በዚህም መሰርት ወዳጅ መስለው ባህር ማዶ ለትምህርት የሄዱትን የተወሰኑትን የደጉን ሰው ልጆች ቀርበው ‘እናንተ እኮ የሰለጠናችሁ፣ ብዙ ትምህርት የቀሰማቸሁ ስለሆነ ወደ አባታችሁ ቤት ስትሄዱ ዋና አስተዳዳሪ፤ ደግሞም ካባታችሁም የሃብት ድርሻ መልካም መልካሙን ለም የሆነውን የውሃ ምንጭ የሚፈስበት ቦታ ይገባችኋል። እዚያ አገር ቤት ያሉ ወንድሞቻችሁመሃይማን ስለሆኑ እናንተን ማገልገልገል አለባቸው’ እያሉ ልብን የሚያማልል ከፉ ምክር መከሯቸው። እነሱም እግዚሃቤርን መፍራት የባህር ማዶ ትምህርት አስቀርቶላቸው ስለነበር በዚህ ክፉ ምከር ልባቸው ተሞላ።
በዚያ ደጉ ሰው ቤት የሚኖሩ መልካም ልጆቹን ደግሞ ቀርበው ‘‘እንዚያ ባህር ማዶ የሄዱ ወንድምና እህቶቻችሁ የበላይ ሊሆንቧችሁ ነው። መልካሙን መሬት ከብቶች ሁሉ ሊወስዱባቸሁና ለናነት ደረቁን፣ ውሃ የሌለውን፣ የከሱትን፣ በሽተኞችን ከብቶች ሊያወርሷችሁ ነው” ብለው ክፉ ምክር መከሯቸው። ምንም እንኳ በዚህ ምክር ባይገዙም ወንድሞቻቸው ና እህቶቻቸው ከባህር ማዶ እስኪመጡ እንድነታቸውን ጠበቀው በሰላም ጠበቁ።
ከባህር ማዶ የተመለሱ አንዳንድ ወንድምናእህቶቻቸውን በደስታ ተቀበለው ቢያይዋቸው ገን እጅግ ተለወጡባቸው። እግዚሃቤርንም አየፈሩም። ሃይማኖታቸውንም ለውጠዋል ክደዋል። ”አለተማርችሁም፣ አልሰለጥናችሁም” እያሉ ‘‘እኛ የምንለውን ስሙ‘‘ ይሏቸውም ጀመሩ። በመካከላቸውም አለመግባበት ተፈጠረ። መልካሙንም መሬት ከብቶች በቶሎ ይቀራመቱ ጀምር።
እንዚያ ምቀኞች እጀግ ተደሰቱ። የዛን የደግ ሰው ሃብት በአጅ አዙር እጃቸው ላይ የሚገባበትን ቀናት በናፍቆትም ይጥብቁ ጀምር። ወንዳማምቾቹ ሲጣሉ የሚመክሩ እየምሰሉ እጅጉን ልይነቱን አሰፉባቸው። አንዳንዶቹን ወደቤታቸው እየወሰዱ ጦርና ጎራዴ እያስታተጠቁ መብትህን አስጠብቅ እያሉ ከፉ ምክር እየመከሩ በወንድማምቾቹ ዘነድ ደም እንዲፈስ አደረጕ።ባህሩንም፣ ውሃ ያለበትን በዚያም ያለውን ምድር ሁሉአስወሰዱ።
የልጆቹ እናት እያለቀሰች ‘‘ልጆቼ ሆይ ምነው ምነው’‘ብላ ብትማጸናቸው የሚሰማ ጠፉ። እሷም ”ልጆቼ. አባታችሁና እኔ ያፈራነው ሃብት፣ ከዘር ማንዘራችንም የወርስነው ሀገር ሁሉ ከበቂያቸን በላይ ነው። ለሁላቸሁም ይሆናል። ሁላቸንንም በእኩልነት ያኖራል‘ ብትላቸውም አለሰማ አሉ። ከባህር ማዶ የመጡ ልጆችዋ ‘‘ይህቺ ሗላ ቀር አሮጊት ደንዝዛለች አይገባትም’‘ እያሉ ተሳለቁባት። እንዳንድ ልጆቹዋ እናታⶨው እንዲህ በልጆችዋ ስትዋረድ አይተው አለቀሱ፤ በወንድሞቻቸውም ላይም አዘኑ።
ወንድማማቾቹና እህታማምቾቹ መነጋገር ተስኗቸው ከትውልድ ጀምሮ ሲወራርስ የመጣውን ሃብትና እናት አባቶቻቸው ጠብቀው፣ አሻሽለው ያቆዩትን መሬትና ሃብት ካልታካፈለነው፡ ካልሽነሽነው እያሉ የራሳቸውን ድርሻ እንዚያ ምቀኞች በሰበኳቸው መሰረት ድንበር እያሰመሩ ካልተከፋፍልን፣ አንተም ወንድሜ አንቺም እህቴ ከኔ ክልል እንድትወጡ እያሉ ዛቻና ማስፈራርትእንዲሁም ክፉ ድርጊት ማድርግ ጀምሩ።
ያቺ ደግ እናት ልጆቼ ሊተላለቁ ነው ብላ ለቀሶ ላይ ናት ። እነዛ ምቀኞችም አሰፈስፈው ወንድማማቾችና እህታማምቾቹ ሲተላልቁ የሚዘርፉት ምድርና ሃብት ለመከፋፈል ተዘጋጀተዋል።
ይህ ከላይ የተገለጸው ምሳሌ እውነታ ዛሬ በኢትዮጲያ እየተፈጸመ ነው። ልጆችዋ በታሪካዊ ጠልቶችዋ ሴራ ተጠልፈን፣ ባደርባን የስግብግብነት መንፈስ ህይወት ዘርቶ እየመራን አሁን አገራችን ኧፋፍ ፣ገደል ጫፍ አደርሰናታል። ሁላችንም የተደገሰውን ታላቅ የጥፋት ድግስ አውቀን፣ አባትና አናቶቻችን ጠብቀው ያወረሱንን ሀገር በእኩልነት፣ በወንድማማች እህማምችነት ተባብረን ይዘን፤ የምቀኛ ጠላትንም ሴራ አክሽፈን፣ የበለጠ አደገን ተመንድገን ፣ እግዚሃቤርን እያመስገንን፣ ደስ ብሎን እየኖርን አባቶቻችንና እናቶቻችን ለኛ በነፃነት እንዳሰርከቡን ሁሉ እኛም ለልጆቻችን እንድናስረከብ ሀላፊነትና ግዴታ አለብን።
እያንዳንድችን የኢትዪጲያ ልጆች አሁን በሃገራችን እይተፈፀመ ባለው ሴራ በየትኛው እንደ ተጠለፍን መርመርነ፣ አወቀን፣ ተለውጠን፣ ሴራውን በመተባበር በማክሸፍ ደስ ብሎን በእኩልነት ያባቶቻችንን ቤት አሙቀን እንዴት እንደምንኖር እንችል ዘንድ በማስተውል ራስችንን መርምረን ለተገባር እንብቃ።
ለዚህም ያባቶቻችንና የናቶቻችን አምላክ ይረዳን!
አሜን።