የባላደራ ምክር ቤት ጉዳይ || አክሊሉ ወንድአፈረው

የባላደራ ምክር ቤት ጉዳይ || አክሊሉ ወንድአፈረው

በዴሞክራሲያዊ ግንባ ውስጥ የሞጋችና ነ ተቋማት ሚና

ባለፉት  ጥቂት ወራት ዲስ አበባበአካባቢዋ በተቀሰቀሰው የ”ባለቤትነት ጥያቄ “ የተነሳ  አዳዲስ ተጫዋቾችን ያካተቱ የፖለቲካ ክስተቶች በመታይት ላ ናቸውከነዚህ ውስጥ  “አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ነዋሪራሷንም ችላ መተዳደር የሚገባት ከተማ ነች “ በሚል አመለካከት ር የተሰባሰበውና በታዋቂው ዜጠኛ ስክንድር ነጋና ጋሮቹ የሚመራው “ባለደራ ምክር ቤት ወይም ባልደራስ ” የተሰኘው የህዝብ ስብሰብ (ሲቪክ ማህበር) አንዱ ነው። በዚህ ጽሁፍ ይህ የሲቪክ ድርጅት የተመሰረተበትን አግባብና እያካሄደ የሚገኘውን ትግልእንዲሁም እየደረሰበት ያለውን ፈታኝ ተግዳሮት በተመለከተ፤ ሀገራችን የፖለቲካ ሽግግርዴሞክራያዊ ስርአት ለመመመስረት ከሚደረገው ጎዞ አኳይ የሚኖረውን እንደምታ በጨረፍታ አሳያለሁ።

የሲቪክ ድርጅቶች ወይም ማህበራት ሚያስገኙዋቸው ጠቀሜታእጅግ ሰፊ ሲሆኑ ነዚህም በሁለት ዋና ዋና ጉዳዩች ዙሪያ ሊመደቡ ይችላሉ። አንዱ ማህበረሰብአዊ ጠቀሜታቸው (ሶሻል ካፒታል) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የፖለቲካ ጠቀሜታቸው (ፖለቲካል  ካፒታል ) ናቸው

የሲቪክ ድርጅቶች  ማህበራዊ እሴት (ሶሻል ካፒታል)

የሲቪክ ድርጅቶች  ማህበራዊ እሴት (ሶሻል ካፒታል) የሚባለየስቪክ ድርጅቶች በሚበት ዋና ሀሳብ ዙሪያ ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦችና ማህበረሰቦች ማሰባሰብ እርስ በርስ እንዲተዋወቁ በአላማና በግብ ዙሪያም እንዲቀራረቡ የማድረግ ጠቀሜታቸውን ያመለክታል። በዚህ አይነት ተግባር ተጨበጭ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ይበልጥ እንዲቀራረቡአንዳቸው ከሌላው ድጋፍ እንዲያገኙ ብቸኝነትና የተገላይነት ስሜት እንዳያጠቃቸው ያግዛል።

የሰው ልጅ ኑሮ እየተወሳሰበ ብዛኛው ህይወቱም በግል ስራ ላይ አተኩሮ በሚኖርበት ጊዜ እነዚህ ማህበራዊ እሴቶች ላይ ያተኮሩ ድርጅቶች አስፈላጊነት ታላቅ ቦታ አላቸው። ቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችንም ይህንኑ በመገንዘብ ይመስላል ድርቁብ፣ ጅጌ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ማህበራዊ ድርጅቶችን መስርተው ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ እንዲቀጥሉ ያደረጉት

የዚህ አይነት አደረጃጀትና ስብስብ ውስጥ የሚታዩ ማህበራዊ ድርጅቶች አገልግሎታቸው ሰፊ ቢሆንም በፖለቲካ ድርጅቶች ፖሊሲና አስተሳሰብ ላይ ተጽእኖ ለማድረስ የሚኖራቸው ክህሎትግን ዝቅተኛ ነው። የምስረታቸው አላማም ሆነ አደረጃጀታቸው ፖለቲካ ተጽእኖ መፍጠርን ወይም ፖሊሲን ማስፈምን በእሳቤ ውስጥ አሰገብቶ ስላልሆነ በዚህ ረገድ የሚያደርገው ተጽእኖም ዝቅተኛ ነው

ይህ ማለት ግን በሶሻል ካፒታል ዙሪያ የተሰባሰቡ ሲቪክ ድርጅቶች ውሎ አድሮ በዙሪያቸው ያሰባሰቡትን እምቅ ሀይል ወደ ፖለቲካ ካፒታልነት ሊቀይሩት አይችሉም ማለት አይደለም።

የሲቪክ ድርጅቶች ፖለቲካዊ እሴት (ፖለቲካል ካፒታል)

ፖለቲካ እሴት (ፖለቲካል ካፒታል) ተብሎ የሚጠራው ደግሞ የሲቪክ ድርጅቶች የተወሰነ የማህበረሰብ ክፍልን የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ በተለይም በመንግስት፣ በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ጽእኖን ለማሳደር የሚያሰትለውን ከመደራጀትና የህዝብን እምቅ ሀይል ለፖለቲካ ግፊት ከማዋል ጋር የተያያዘ ችሎታን የሚመለከት ነው።

ይህን ተባር መሰረታዊ ስራቸድርገው ሚንቀሳቀሱ ሲቪክ (ማሀበራዊ) ድርጅች የመብት መረጥን ለማስቆም፣ ህዝብ ላይ ከፍተ ተጽእኖ ሚኖራቸው መንግስትና ፖለቲካ ድርጅቶች ላ ተጽእኖ ለማሳደርወዘተ የሚቻለው በዋናት በተደራጀና ተቀነባበረ መንገድ ነው ብለው የሚያምኑ፣ የግለሰብ ጥረቶች በድርት መልክ ካልተሰባሰበ መንግስትም ሆነ ፖለቲካ ፓርቲች በቀላሉ እደማያዳምጡ ግንዛቤን የወሰዱ አካሎች ናቸው

በተለይ ደግሞ ብዙሀዊነት በሚታይበትና የተለያዩ ክፍሎች ፖለቲካዊም ሆነ ማህበራዊ ፍላጎታቸውን (አጀንዳችን) የመግስት ፖሊሲ ለማድረግ ፊት በሚያደርጉበት ህብረተሰብ ውስጥ የዜጎች ጥቅም የሚጠበቀው በተናጠል ሳይሆን ተሰባስቦ በሚደረግ ተጽእኖ  ፈጣሪነት ነው። በዚህ አውድ ውስጥ ያልተደራጁ የህብረተሰብ ክፍሎች ብዛኛው ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል ሀይል እንደማይኖራቸው ገንዘብ ዜጎች የተደራጀ ሀይላቸውን የጋራ ጥቅማቸው ለማስጠበቅ የሚያስችላቸው ስብስብ አስፈላጊ ይሆናል። ይህ እውን የሚሆነውም የመደራጀትንና በጋራ ተጽእኖ የመፍጠርን የፖለቲካ እሴት (ካፒታል ) በተገነዘበ ሲቪህ ድርጅት አማካኛነት ነው።

የፖለቲካ መሪች ውሳኔ ዜጎች ህይወት ላይ እጅግ መሰረታዊ የሆነ በጎም ሆነ መጥፎ ተጽእኖ የማሳደር ችሎታ አለው። አንድ መንግስት አንድን በረሰብ መሰረታዊ በሆነ መልክ ለዘመናት እንዲለወጥ የሚያደርገው ውሳኔ ሊሰተላልፍ ይችላልይህን የመንግስት ተጽእኖ ለማስቀየርም ሆነ  ለመቋቋም  ተጽእኖ  ፈጣሪ ሲቪክ ህበራት መደራጀት እጅግ አሰፈላጊ ይሆና ይህ በህብረተሰብ ላይ የሚደርስ ተጽእኖን የማስቆምና የማስቀየር እምቅ ሀይል ነው ፖለቲካዊ እሴት የሚባለው።

የፖለቲካ ብዙሀዊነት አውን በሆነበትና የፖለቲካ ስልጣን ህዝብ ድምጽ ብቻ በሚያዝበት ህብረተሰብ ውስጥ ፖለቲከኞየህዝብን ድምጽ እንዲያዳምጡ ሚደረበት መንገዶች ውስጥ አንዱ በድም አሰጣጥ ላይ ድጋፍን በመንፈግና በመስጠት የሚገለ ነው። በዚህ መልክ ድምጽን በተደራጀ መልክ  ለመንፈግም ሆነ ለመስጠት ሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ ህዝብን የማደራጀት፣ ማስተማርና በድምጽ አሰጣጡ  የሚፈልገውን ውጤት ለማምጣት የሚያስችለውን  ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችለውን  ክህሎት (ፖለቲካል ካፒታል)እውን ለማድረግ ሲቪክ ድርጅቶች ሚና ከፍተ ነው።

በአጠቃላይ የሲቪክ ድርጅቶች የፖለቲካ ካፒታላቸውን በተለያዩ ጥያቄች ዙሪያ ህዝብን በማሰባሰብ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የፖለቲካ ሀይሎች ለህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ ትኩረት እንዲሰጡ ተጽእኖ ለማድረስ የሚደርጉትን የዜጎች እንቅስቃሴ ያሳያልበፖለቲካ ሽግግር ወቅት ይህን ተግባር ትኩረት ሰጥተው የሚንቀሳቀሱ ማህበራዊ ድርጀቶቸ ዴሞከረሰዊ ለውጥ ማሳካትና ዴሞከራሲያዊ ስርአት ግንባታን በጠንካ መሰረት ላይ ለማስቀመጥ በሚደረግ ጥረት ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ ይታያል፡

ሽግግርና ሲቪክ ድርጅቶች

ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር በሁሉም ገጽታው ፈላጭ ቆራ እኔ የምለውን ብቻ  ስማ ከሚል አገዛዝ ወደ የህዝብ መብየተከበረበት የህዝብ ድምጽ ወደሚደመጥበትና ሰብአዊ መብትና የህግ የበላይነት ወደተረጋገጠበት ስርአት የሚደረግ የለውጥ ሂደት ነው።  

በዚህ ይነት የግግር ደት ውስጥ የሲቪክ ማህበራት ዋነኛው ተግባር ባንድ ሀገር ውስጥ የሚገኝ መንግስት ስልን እንዳይባልግና በሚያሰተዳድረው ህዝብ ህይወት ላይ ተገቢነት የሌለው ተጽእኖ እንዳያደርግ የሽግግሩ ሂደትም ፈሩን ስቶ እንዳይሄድ መንግስት ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የሚያከብር እንዲሆን አበክሮ መስራት ነው።

ከአምባገነን ስርአት ተላቆ ወደ ዴሞክራሲ በሚያመራሽግግር ሂደት ውስጥ መንግስት እንዳለፉት አምባገነኖች ሁሉ መብት መርገጥ እንዳያገረሽበት፣ ከሚገባው በላይ በመሄድ የህዝብን መሰረታዊ መብት እንዳያኮላሽ፣ የህዝብን ፍላጎትና መብት ወደጎን ገፍቶ የራሱን እና የደጋፊቹን ጠባብ ፍላጎት ብቻ በህዝብ ላይ እንዳይጭን፣ ለሰላምና ለዴሞክራሲ ግንባታ ታማኝ ሆኖ እንዲቀጥል በስልጣን መባለግ አድል ወዘተ የመሳሰሉት አስከፊ ክስተቶች እንዳይከሰቱ ቢከሰቱም በጊዜ እንዲጋለጡ ታላቅ ሚናን የሚጫወቱት የሲቪክ ድርጅቶች ናቸው።

የሲክ ድርጅቶች የህዝብ ይናና ጆሮ በመሆን ህዝብን ለመብቱ እንቆም በማስተማርና በማደራጀት በለውጡ ሂደት  ንቁና ቆራጥ ተሳታፊ  እንዲሆኑ የለውጡ ሂደት በአስተማማኝ መልክ አንዲቀጥል የለውጥ ሀይሎች እንዲጠናከሩ ለውጡም ተቋማዊ እየሆነ ስር እየሰደደ እን ያግዛሉ።

ይህ ሲሆን ደግሞ ህዝብ በለውጡ ሂደትና በመንግስት ላይ እምነቱ እንዲጠናከር ለመንግስት ያለው ከበሬታና እምነትም ከፍ እንዲል ታላቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ነው ዴሞክራሲያዊ ስርአት የህብረተሰቡን ታላቅ አመኔታና ድጋፍ የሚጎናጸፈው። የዚህ አይነቱን  ስርአት ነው ህብረተሰቡም የኔ ነው ብሎ እንደ ይኑ ብሌን የሚንከባከበው።

ባጭሩ ከአምባገነን ስርአት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር ህዝብን ከል ያደረገ (ህዝብን ያሳተፈ) መሆን ይገባዋል። ይህ ደግሞ በዋናነት የሚገለጥበት አንዱ መንገድ ህዝብ በራሱ ፍላጎት በሲቪክ ማህበራት አማካኝነት በንቃትና በድፍረት መሳተፍ ሲችል በመሆኑ እነዚህ ድርጅቶች ሊበረታቱሊደገፊም ይገባቸዋል።

የሀገራችን ፖለቲካዊ ምህዳር መስፋትና ባለአደራ ምክር ቤት መወለድ

በኢትዮጵያ ህዝብ ትግል የህወሀት የበላይነት ከተወገደና ዶክተር አብይ አህመድም የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን ስልጣን ከያዙ ወዲህ የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍል። ከዚህም ጋር ተያይዞ  የህብረተሰቡን ጥቅም ለማስጠበቅም የተለያዩ ድርጅቶች ብቅ ብቅ ማለት ምረዋል። ከነዚህ ውስጥ አንዱና በቅርቡ ተመስርቶ ትልረትን የሳበው ባልደራስ ወይም ባለአደራ ምክር ቤት የተሰኘው ድርጅት ነው።

ለ አደራ ምክር ቤት መነሻው አዲስ አባባ በማን ትተዳደር በሚለው ጥያቄ ዙሪያ የተነሳውን ሀሳብ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከሰተውን ከፍተኛ ውጥረትና አለመረጋጋት ተከትሎ ነው፡

ኢህአዴግ ለ27 መታት እንዳደረገው ሁሉ አዲስ በባን በተመለከተም ህዝቡን ሳያሳትፍ “መሪው ድርጅት” በፈለገው መልክ ሲፈልግ ላንዱ ክልል ሲሰጥ ሌለ ጊዜ ደግሞ ሲነጥቅ፣ እንደቆየ ይታወቃል። በዚህም ተግባሩ ፖሊሲ አሁን ለምንለከተው በአዲስ አባባ ላይ ለተቀሰቀሰው የይገባኛል ጥያቄ ተጨማሪ የግትና የጭንቅ ድባብፈጠረበትን ሁኔታ እንዳመቻ እናያለን።

ይህ ሁሉ ሲሆን ኢህአዴግ የአዲስ አባበን ነዋሪፍላጎትና ስሜት ምን እደሆነ አንድም ጊዜ ጠይቆ እንደማያውቅ ታሪክመዝግቦታል።

ደራስ ወይም ባላደራ ምክር ቤት የተሰኘው ንቅ በዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ ኢህአዴግም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ከተማችንንና ህዝቧን ወዲያ ወዲህ ሊያደርአይገባም፣ በስጦታም፣ በፖለቲካ ዳረጎትም ይሁን በሌላም ምክንያት ፈለገው አካል ያለፍላጎታችን አሳልፎ ሊሰን አይገባም በሚል እሳቤ የተነሳየሚንቀሳቀስም ነው።

ለአደራ ና ከጅምሩ የቆለት ላማ የአዲስ አባባን ነዋሪወችን አስተባብሮ መንግስትንም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ አዲስ አበባን በተመለከተ ባላቸው አመለካከት አኳያ እኖ ማሳደር እና መሞገት መሆኑን በግልጽ አስፍሯል። ይህ ሁኔታ ላለፉት 27 መታት ባልተለመደ መልክ ደሲቪክ ድርጅት የፖለቲካ ካፒታሉን ባግባቡ ገምግሞና አውቆ የተደራጀ መሆኑን ያሳያል።

ይህ ሞጋች ህብረተሰብና ህዝብ የሚጠበቅ የዴሞክራሲዊ ህብረተሰብ መሰረት ግንባታውንም እጅግ የሚያጠናክ፣ ፖለቲከኞችንም ከራሳቸው ፍላጎት ባለፈ በህዝብ ፍላጎት እዲገዙ የሚደርግ አበረታች ተግባር ነው፡’ይህ መንግስም ሆነ ሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ተጠያቂነትን እንዲያውቁ፣ የሚያግዝ የዴሞክራሲያዊ ሂደት መሰረት  ነው።

ዴሞክራሲያዊ ስርአትን እውን መሆን ለምንናፍቅ ጠያቂ ነጻና ደራጀ ህብረተሰብን ለምንፈልግ ሁ ይህ አስደሳች እንጂ አስጊ ክስተት አይደለም። ባላአደራወች (ባልደራሶች) ለማድረግ የሚፈልጉት በማንኛውም ዴሞክራሲን አከብራለሁ በሚል ሀገር ማህበራዊ ድርጅቶች ሚያደርጉትን የተለየ አይደለም

ለዚህ ነው ይህ ሲቪክ ድርጅት ሊበረታታና አይዞህ ሊባል እንጂ እዲሸማቀቅ እዲዳከም ወይም እንዲጠፋ መደረግ የለበትም የምለው። በርግጥ እንደጀማሪ ድርጅት ባላደራ ምክር ቤትም ስህተት ሊሰራ ድክመትንም ሊያሳይ ይችላል። ይህ የሚጠበቅ ነው።

ሀገራችን ዴሞክራሲእንድትሆን ከፈለግን ረግ ሚገባን ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ፍላጎታችንን እውን ሊያደርጉ የሚችሉ ተቋማትን (ሲቪክ ድርጅቶችን ጨምሮ) ድክመታቸውን እንዲያሰተካክሉ እያገዙ አቅማቸውን መገንባትና ማጠናከር ነው። በእነዚህ ይነት ድርጅቶች ላይ የሚደረግ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽእኖን መቃወም ደግሞ ለመሰረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር መቆም ነው።

ሲቪክ ማህበራት ለማበብ አበረታች ድባብ ይሻ

 የሲቪክ ማህበራት በተዛዋሪም ሆነ በቀጥታ በጥቃት ስር ሲሆኑ (በፖሊስ  ሲሳደዱ መሪቻቸው  ሲወገዙ፣ የሚታሰሩ ስብሰባ ሲከለከሉወዘተ) ህብረተሰቡ እንደልቡ ተንቀሳቅሶየሲቪል ግዴታውን ለመወጣት አስቸጋሪ ይሆንበታል በዚህ ላማ ስር የሚቋቋሙ ሲቪክ ድርጅቶችም ብቡምአይጎለብቱም

ህወሀት መራሹ ኢህአዴግ የ27 ት አገዛዝ የተመለከትነውም ይኽንኑ እውነታ ነው ከተነሳሽነት ማነስ ይሆን መንግስት ተጽእኖ የተነሳ ሲቪክ ማህበራት በተለይም የፖለቲካ ጥያቄ የዜጎች መብት ላይ ያተኮሩት ሁሉ ድምማጣቸው እንዲጠፋ ተደርጓልየኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ሴት ጠበቆች ማህበር፣ የሰብአዊ መብት ጉባ፣ የመምህራን ማህበርሰራተኞች ማህበርወዘተ ከሚጠቀሱት ሰለባወች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡

አሁን ባለው የሀገራችን ሁኔታም ደራ ምክር ቤት የተሰኘው ሲቪኽ ማህበር ገና ብቅ ከማለቱ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት መሪችና የፖለተካ ድርጅት ተወካዮች ውገዝና መኮነን መጀመራቸው፤ ስብሰባ እንዳያደርጉ የተለያየ ተጽእኖ ማሳደራቸውወዘተ፣ በለውጡ ማግስት የተከፈተውየፖለቲካ ምህዳር መልሶ እንዲጠብ የሚያደርግ እንጂ የሚያዳብረው አይደለም።

አንዳንዶች ባልደራስ ወይም ባለአደራ ቆሜለታለሁ ከሚለው ላማ ውጭ የራሳቸውን ትርጉም በመስጠትዲስ አባባ ከተማን ምክር ቤት ተክ መስራት ያለብ እኔ ነ “ ብሏል በማለት ሊፈርጁትና የህዝብ ድፍን ሊያሰነፍጉት፣ የሚጥሩበት ሁኔታ ይታያል።  አንዳንዶች ደግሞ “የአዲስ አባበን ዝብ እወክላለሁ እንዴት ይላል” እኔም የአዲስ አባባ ነዋሪ ነ ሆኖም ለስበሰባ እኳ አልተጠራሁምይላሉ። ይህን የሚሉ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ለመሆኑ እናንተ እንወክለዋለን እያችሁ በስሙ የምትናገሩት ህዝብ መ ተሰብስቦ ነው ናንተ ውክልና የሰጣችሁ ቢባሉ ምን እንደሚሉ ይገርመኛል።

ሕወሀት መራሹ ኢህአዴግ የሲቪክ ማህበራትን በተመለከተ ይከተለው የነበረው አንዱ ፖሊሲ እነዚህን ድርጅቶች ከፖለቲካ ድርሻቸው ለመነጠልና በእርዳታና ሌሎች በማህበራዊ ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮ በማድረግ ላይ ያጠነጠነ ነበር። ባጭሩ ነጻ ሞጋችና ፖለቲካዊ ተጽእኖ ፈጣሪ ሲቪክ ድርጅቶችህወሀትን አይመቹትም ነበር።

ለዚህ  ማሳያ ሀገር በቀል የሆኑትንም ሆነ በውጭ የሚገኙ ሲቪክ ድርጅተች ከፖለቲካ ተግባር ተገልለው እርዳታ የማደል ወይም መንግስት በሚያጸድቀው ተግባር ላይ ብቻ እንዲሳተፉ ሲፈቅድ መቆየቱ ፣ በመብት ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ድርጅቶች (ሰብአዊ መብት፣ የሰራተኞች መብት፣ የመናገርና መፍ፣ የሴቶች መብትወዘተ) ደግሞ በሀገር ውስጥ ያሉት እንዲቀጭጩና እንዲጠፉ በውጭ ያሉት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ድርሽ እንዳይሉ አድርጎ መቆየቱ ነው።

አሁን ደግሞ ያን ጨቋኝ ስርአት አስወግደን ራያችን ዴሞክራሲያዊ ስርአትን መገንባት ነው በሚባልበት ይህንኑ ሀላፊነት ተሸካሚ የሆኑ ጅምሮችን ማጥላላትና እንቅስቃሴያቸውንም  በተለያየ ሁኔታ ማደናቀፍ እጅግ ተገቢ ያልሆነ ተግባር ነው። ይህ ደግሞ የሆነው ሀገራችን በለውጥ ውስጥ ነች ሲቪክ ማህበራትም የለውጡ የጀር አጥንት ስለሆኑ ይህንን ለማገዝ የሚሆን አዲስ የማህበራት አዋጅ ተዘጋጅቷል ተብሎ በተገለጸ ማግስት መሆኑ እጅግ ግራ የሚያጋባና እጅግ አሳሳቢም ያደርገዋል።

በርግጥ ባደራ የተሰኘው ስብስብ እጅግ ሞጋችና ያነሳቸውም ጥያቄለፖለቲከኞች እጅግ ፈታኝ እንደሆኑመረዳት ይቻላል ያም ሆኖ ግን ያቄው ገና ለገና ፈታኝና አከራካሪ (ሴንሲቲቭ) ነው በማለት የህዝብን የመደራጀትና ሀሳቡን በነጻ የመግለጽ መብት ማፈን አግባብ አይደለምየዚህ አይነቱ ተግባር የመንግስትና ህዝብ ቅራኔ ያካርረዋል እንጂ አያረግበውም እንደ ባላደራ የመሰሉ ሲቪክ ድርጅቶችን አግልሎና ድምጻቸውን አፍኖ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላይ ውሳኔ ማስተላለፍ ቢቻል እ የውሳኔው ቅቡልነቱ እጅግ ዝቅተኛ ነው የሚሆነው። ለዴሞክራሲ ግንባታ ደግሞ እጅግ አፈላጊው ነገር የለውጡ ሀይልና የለውጡን ሂደት ቅቡልነት (ሌጅትመሲ) ማዳበር እንጂ የዜጎችን ድምጽ ማዳመጥን ወደጎን ትቶ የፈለጉትን ውሳኔ ማስተላላፍ አይደለም

በዚህ አኳይ ከፖለቲካም አንጻር ይሁን ዜጎች በፖለቲካ ምህዳሩ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ከማበተረታታት  ወይም ዜጎች በሽግግሩ ትክክለኛነት ለይ ያላቸውን እምት ከማዳበር አኳያ መደረግ የሚገባው ምክር ቤትንና መሰል ድርጅቶች ማበረታታትና መደገፍ እንጂ እንቅፋት መሆንከቶውንም አይደለም

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ እዳሉትም ማሰታወስ የሚገባው ለዴሞክራሲ ግባታ በዋናነት የሚያሰፈልገው ጠንካራ ሰ ሳይሆን ጠንካራ ተቋማትን መገንባት ነው (Africa does not need strong men. It needs strong institutions ። እነዚህ ነጻና ሞጋች ተቋእንዲያብቡ የሚያበረታታ ድባብ ከሌለ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር እንዘጭ እንጭ ማለ የማይቀር ነው፡ይህ ደግሞ ለማንም የሚጠቅም አይደለም።

ስለዚህ ምን ይደረግ

ይህን ፈተና በበጎ መንገድ በመፍታት ታላቁ ድርሻ የመንግስት ሲሆን ሌሎችም ቢሆኑ ሊጫወቱት የሚገባው ሚና ከፍተኛ ነው። በዚህ አኳያ

መንግስት ነጻና ሞጋች ሲቪክ ድርጅቶችን በመገንባት አኳያየማያመነታና የማያወላውል ሙሉ የድጋፍ አቋም ሊያሳይ ምህዳሩንም ሊያመቻች ይገባዋል። አሁን በተፈጠረው ግራ አጋቢ ሁኔታ አንጻር ሲታይ ይህ ድጋፍ በዋናነት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቢገለጽ ታላቅ ተጽእኖ ይኖረዋል።
ህዝብ በዚህ መልክ ሲሰባሰብ ለመንግስትም ሆነ ለተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶች የማይመቹ ጉዳዮችን ሊያነሳ እንደሚችል ከወዲሁ በመገንዘብ መንግስት ይህንንም ተቃርኖ ለማስተናገድ ዝግጁ ሊሆን ይገባዋል።
ለአደራ ምክር ቤት ላይ የተጣለው እገዳና ተከታታይ ተጽእኖ ባስቸኳይ መቆም ይኖርበታል
የተለያዩ ነጻ መገናኛ ብዙሃንም ይህንን እና ተመሳሳይ ጉዳዮችን በቅርበት በመከታተል በማንኛውም አካል የሚደረጉ የመብት ረገጣችንና አፈናችን በወቅቱ በሰፊው ለህዝብ ማሳወቅ ይገባቸዋል;
የፖለቲካ ድርጅቶችም የመደራጀት መብትን ማክበርና ነጻ ሲቪክ ድርጅቶች እንዲመሰረቱና  እንዲጠነከሩ የማድረግ ተግባር የመንግስት ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን የእነርሱም ድርሻ እንደሆነ ግንዛቤ ሊወስዱና በረግባርም ሊያሳዩ ይገባል።
ባለአደራ ምክር ቤትም ራሱን በየጊዜው በመገምገም አስፈላጊ የሆኑ ማስተካከያወችን በማድረግ የዴሞክራሲያዊ ስርአት አጋርነቱን ይበልጥ ሊያሰመሰክር ይገባዋል።

ሚያዝያ 25፣ 2011  (ሜይ 3፣ 2019)

ethioandenet@bell.net

LEAVE A REPLY