ሮማን ፕሮቻዝካ || መስፍን አረጋ ዘነገደ ኩሽ

ሮማን ፕሮቻዝካ || መስፍን አረጋ ዘነገደ ኩሽ

The numerous tribes who inhabit the Ethiopian state are being forcibly kept from European colonialism by Abyssinian rulers whose aim is to act as champions of all black people so as to attack and destroy Western culture

የጦቢያ አያሌ ብሔረሰቦች የነጭ ባርያ የመሆን ምርጫቸውን የነፈጓቸው መሠረታዊ ዓላማቸውበነጭ ተጽእኖ መቃብር ላይ የጥቁርን ልዕልና መገንባት የሆነው የሐበሻ መሪወች ናቸው፡፡

Roman Prochazka (Abyssinia: The Powder Barrel, Vienna, 1935)

ሮማን ፕሮቻዝካ (Roman Prochazka) ፣ በጀርመንኛ ጥቁሩ አደጋ (die Schwarze Gefahr) የሚል ርዕስ የሰጠውንናበጣልያንኛ ተተርጉሞ አደገኛዋ ጥቁር ጦቢያ (Abissinia pericolo nero)፣ በእንግሊዘኛ ተተርጉሞ ደግሞ ጦቢያ፣ በርሜል ባሩድ (Abissinia: The Powder Barrel) የተሰኘውን መጽሐፍ ከዘጠና አመታት በፊት (1929 ዓ. ም) የጻፈ፣ ጦቢያውያን ባንድነታቸው በተጎናጸፉት በታላቁ ያድዋ ድል አንጀቱ የቆሰለ ነምሳዊ (Austro-Hungarian Empire) የናዚ ባላባት (baron) ነበር፡፡  የመጽሐፉ ፍሬ ሐሳብ ደግሞ በጥቁርነታቸው የሚኮሩት የጥቁሮች አገር ጦቢያ፣ ለነጭ ዘር መቅሰፍት ስለሆነች፣ ባገር በቀል ጎጠኞች ተጎጥጉጣ መገነጣጠል አለባት የሚለው ነው፡፡  

ምዕራባውያን ዘረኞች በተለይም ደግሞ ለጥቁር ሕዝብ የጋቱትን እንቆቆ ወር ተራቸው ደርሶ እንዳይጋቱ እጅጉን የሚሰጉት ሜሪቃኖችና እንግሊዞች ጦቢያን በተመለከተ ማናቸውንም ፖሊሲ (policy) ሚቀርጹት የፕሮቻዝካን መሠረታዊ ሐሳብ በመንተራስ ነው፡፡  በሌላ አባባል እነዚህ ዘረኞች ጦቢያን በተመለከተ ማናቸውንም ድርጊት የሚያደርጉት ድርጊቱ ከፕሮቻዝካ ሐሳብ ጋር የሚጣጣም ከሆነብቻ ነው፡፡  ምዕራባውያን ለጦቢያ የሚያደርጓቸው ድጋፍ፣ እርዳታ፣ ብድር ወዘተ. መታየት ያለባቸውም በዚህና በዚህ መነጽር ብቻ ነው፡፡  በምዕራባውያን ባህል ነጻ ምሳ (free lunch) የለም፣ በተለይም ደግሞ ለጥቁሮች፡፡  

የመላው ዓለም ጥቁሮች ነጭን ድል ባደረገችው በጦቢያ ከመኩራት ይልቅ እንዲያፍሩባትና የነጭን የበላይነት በጸጋ እንዲቀበሉ፣ ጦቢያን አሳፋሪ ለማድረግ ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡  በጥቁርነታቸው እየኮሩ የጦቢያን ጥቅም የሚያስቀድሙ አገር ወዳድ ጦቢያውያን ስልጣን እንዳይዙ፣ ከያዙም እንዳይቆዩ፣ ከቆዩም ሰላም አግኝተው ዓላማቸውን እንዳያሳኩ \መጋረጥ\ የሚችሉትን ጋሬጣ ሁሉ ይጋርጣሉ፡፡  መለስ ዜናዊን የመሰለ የነጭ ቡችላ ሲያገኙ ደግሞ ቡችላውንባስፈላጊው ዘዴ የይስሙላ ስልጣን አስጨብጠው፣ ቡችላነቱን እስከቀጠለ ወይም ደግሞ ከሱ የተሻለ ቡችላ እስከተገኘ ድረስ ስልጣኑ እንዲቀጥል የቻሉትን ሁሉ ይፈጽማሉ፡፡    

ባፍ መፍቻ ቋንቋው ባማረኛ መናገር እስከሚያሸማቅቀው ድረስ የዝቅተኝነት ስሜት ክፉኛ የተጫወተበት ዋለልኝ መኮንን‹‹በእንተ ብሔራተሰብ ጦቢያ›› (On the question of ethopian nationalities) የተሰኘውን ጦማር በ 1962 ዓ.ም የጦመረው የፕሮቻዝካን ሐሳብ በመኮረጅ ነበር እስከሚያስብል ድረስ በማንጸባረቅ ነበር፡፡  ወያኔ የገበረተው (apply)፣ ኦነግም ሊገበርተው የተነሳው ይህንኑ የፕሮቻዝካን ሐሳብ ነው፡፡  በሌላ አባባል፣ ዋለልኝ፣ ወያኔ፣ ኦነግ፣ ሻቢያና ሌሎቹም የጎጠኛ አስተሳሰብ አራማጆችሁሉም የፕሮቻዝካን ህልም እውን ለማድረግ የተኸለቁ የፕሮቻዝካ የሐሳብ ልጆች ናቸው ማለት ነው፡፡

የኦነጉ ሌንጮ ለታ በሰፊው ያማራ ሕዝብ ላይ ያሾፈ መስሎት ‹‹በቅርቡ ብሔርተኛ የሆኑት አማሮቸ ብሔርተኝነት ጥሟቸዋል›› ሲል፣ የራሱን አላዋቂነት ራሱ መመስከሩ እንደሆነ አልገባውም፡፡  አማራ ማለት በኦሮሞ፣ በትግሬና በሌሎች ታፔላወች ራሱን በራሱ ሳይወስን በጦቢያዊነቱ ብቻ የሚያምን አማረኛ ተናጋሪ ማለት ነው፡፡  የዚህ ሕዘብ ብሔርተኝነት ደግሞእንደ ወያኔና እንደ ኦነግ ብሔርተኝነት ትናንት የተፈጠረ ፕሮቻዝካ ዓላማ ውጤት ሳይሆን፣ ዘመናትን የተሻገረ ነው፡፡ ብሔርተኝነቱ ደግሞ ከወያኔና ከኦነግ ብሔርተኝነት እጅግ የጠነከረ ነው፡፡  በሌላ አባባል በብሔርተኝነት ደረጃ ያማራን ሕዝብ የሚበልጥ ማንም – እደግመዋለሁ – ማንም የለም፡፡  ያማራ ብሔርተኝነት ግን እንደ ወያኔ ኦነግ የቀበሌ ብሔርተኝነት ሳይሆንመላውን ጥቁር ሕዝብ የሚያጠቃልልየጥቁር አንበሶች ጥቁር ብሔርተኝነት (black nationalism of black lions) ነው፡፡  ይህን ሐቅ ደግሞ የወያኔና የኦነግ የሐሳብ አባት የሆነው ራሱ ፕሮቻዝካ በግልጽ ገልጾታል፡፡  

ወያኔና ኦነግ ያሜሪቃ ጌቶወች (ghettos) ጋንጎች ጦቢያዊ አምሳሎች ናቸው፡፡  የጦቢያወቹ ወያኔና ኦነግ የጦቢያ ሕዝብ ልእልና ፀሮች ሲሆኑ፣ ያሜሪቃወቹ ጋንጎች ደግሞ ያሜሪቃዊ ጥቁር ልዕልና ፀሮች ናቸው፡፡  ያሜሪቃወቹን ጋንጎች የፈጠራቸው ወይም እንዲፈጠሩ ሁኔታወችን ያመቻቸላቸው፣ የሕዝብ፣ በሕዝብ፣ ለሕዝብ የሚባለውን ያሜሪቃን መንግሥትእንዳሻው ወዳሻው የሚዘውረው ቀላይ መንግሥት (deep state) በመባል የሚታወቀው የነጭ ዘረኞች ሕቡዕ ድርጅት ሲሆን፣ የጦቢያወቹን ጎጠኞች የፈጠሯቸው ወይም እንዲፈጠሩ ሁኔታወችን ያመቻቹላቸው ደግሞ የፕሮቻዝካሐሳብ አቀንቃኝ የሆኑት የምዕራባውያን (በተለይም ደግሞ ያሜሪቃና የእንግሊዝ) ቀላይ መንግሥታት ናቸው፡፡

ያሜሪቃወቹም፣ የጦቢያወቹየፈጠሯቸው ደግሞ ያሜሪቃንና የጦቢያን ጥቁር አንበሳ በመረዙት ጥቁር ውሻአስነክሰው፣ አንበሳው ሲሞት፣ ውሻውንም ገድለው ሁለቱንም /ለመገላገል/ ነው፡፡  ይህን ዘዴ ምን እንበለው?  እሾህን በሾህ እንዳንለው፣ ነጭ ዘረኞች እሾህ የሆነባቸው አንበሳው እንጅ ውሻው አይደለም፡፡

ያሜሪቃ ጋንጎች ዋናውን ጉዳይ እንዳያዩ ተደርገው መናኛው ላይ እየተወዛገቡ፣ ያሜሪቃ ቀላይ መንግሥት በሕቡዕ በሚነዛላቸው እጽ ደንዝዘው፣ በሚስጥር በሚያስታጥቃቸው መሣርያ ርስበራሳቸው እየተጨፋጨፉ ጥቁርን በጥቁይጨፈጭፋሉ፡፡  አልፈው ተርፈው ደግሞ ለጥቁር ልዕልና ሲሉ የጥቁር ፀር ከሆነው ያሜሪቃ ቀላይ መንግሥት ጋር ግብግብ የገጠሙትን ማልኮልም ኤክስን የመሠሉትን ድንቅ ታጋዮቻቸውን ከቀላዩ መንግሥት በተሰጣቸው ቀጭን ትእዛዝ መሠረት በጠራራ ፀሐይ እየረሸኑ፣ ቀኝ እጃቸውን በግራ እጃቸው ቆርጠው ምንም መተከር የማይችሉ ዱሾች ይሆናሉ፡

በጥቅማጥቅሞች በተቀመመ ሰበካ ተሰብከው በጥቅማጥቅሞቹ ታውረው በሰበካው የደነዘዙት የጦቢያወቹ ጎጠኞች ደግሞ፣ የጦቢያ ችግር ሊፈታ የሚችለው በፕሮቻዝካ የሽንሸና ዘዴ ብቻና ብቻ ነው በማለት፣ ራሳቸውን አሳንሰው ጦቢያን በማሳነስ ራሳቸውንም ጦቢያንም ምዕራባውያን ፕሮቻዝካዊ አውሬወች የፋሲካ ቅርጫ ለማድረግ ይናውዛሉ፡፡ ራሱ ፕሮቻዝካ በግልጽ እንደመሰከረው፣ የቅኝ ገዥወች መቅሰፍት የነበሩትን ታላቁን የጦር አበጋዝ አባ ዳኘውን በተስፋፊነት እያወገዙ፣ የታላቂቱን ተስፋፊ የንግሥት ቪክቶርያን ልደት በያመቱ ያከብራሉ (በተለይም ደግሞ በካናዳና በአውስትራሊያ)፡፡  ራስ ሚካኤል ስሑል አድያም ሰገደን በመገልበጥ በመሳፍንት እንድትከፋፈል ያደረጋትን ጦቢያን የተቀራመቱትን የአንድነት ፀሮች ጠራርገው በማጽዳት፣ የልዕልናውን መንገድ ላባ ዳኘው ያደላደሉትን አባ ታጠቅን እየኮነኑ፣ የጀርመኑን ቢስማርክ (Otto von Bismarck)፣ እና የጣልየኑን ጋሪቫልዲ (Guiseppe Garibaldi) ያደንቃሉ፡፡

ውስጣዊ ችግር የሌለው አገር የለም፡፡  ዲሞክራሲ ከኔ ወዲያ ላሳር የምትለውን አሜሪቃን ብንወስድ ባያሌ ውስጣዊ ችግሮች የተሰነገች፣ በኃይል የተሳሰረች፣ አስተሳሳሪው ኃይል ቢወገድ ባጭር ጊዜ ውስጥ የምትበታተን ስንጥቅጥቅ አገር ናት፡፡  ያሜሪቃን ስንጥቅጥቅነት በደንብ የሚያውቁት፣ ሌሎች አገሮችን ለመሰነጣጠቅ የማይተኙት ያሜሪቃ መሪወችም፣ ያገራቸው ስንጥቅጥቆች በጊዜ ሂደት እየሰፉ ሂደው ሸለቆወች እንዳይሆኑ በመስጋት ‹ባብሔር አንድ የሆነች የማትከፋፈል አገር›› (One nation under god, indivisible) የሚል የታማኝነት ቃልግባት (pledge of allegiance) አዘጋጅተው፣ ታማኝነት ርቶ ቃል መግባት ምን እንደሆነ የማያውቁ እንቃቅላወች በየቀኑ ያስነበንባሉ፡፡  የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል፡፡  

ከካህኑ ዳቆኑ፣ ከጳጳሱ ቄሱ እንዲሉ፣ የኛወቹ ወያኔና ኦነግ ደግሞ ካሜሪቃ በላይ ዲሞክራት ነን አሉና ባረቀቁት የጫካ ሰነድ ላይ አንቀጽ ሠላሳ ዘጠኝን አሰፈሩ፡፡  ይህን ያደረጉት ግን ዲሞክራቶች በመሆናቸው ሳይሆን የጦቢያን ውስጣዊ ችግሮች በፕሮቻዝካ ዘዴ በመፍታት የራሳቸውንም የምዕራባውያንንም ዓላማ በማሳካት ባንድ ዲንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት ሲሉ ብቻና ብቻ ነው፡፡  የጦቢያ ውስጣዊ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት ግን በጦቢያ ጥላ ሥር በጦቢያዊ ዘዴ ብቻና ብቻ ነው፡፡  

የጦቢያን ችግሮች በፕሮቻዝካ ዘዴ ለመፍታት የሚታትሩት ገጠኛ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆኑ፣ በድርጅቶች ያልታቀፉ (ቢያንስ በይፋ) ግለሰቦችም ጭምር ናቸው፡፡  የሚቀጥለው ጦማር የሚያተኩረው ከነዚህ ፕሮቻዝካዊ ግለሰቦች ውስጥ አንዱ በሆነው በተስፋየ ገብረአብ ላይ ነው፡፡  እስከዚያው ድረስ የጦቢያ አምላክ አብሔር ይጠብቀወ፣ ይጠብቀን፡፡

መስፍን አረጋ ዘነገደ ኩሽ

የትብቱ ቀብር ደሴ ሳላይሽ፡፡

mesfin.arega@gmail.com

www.amaromiffa.com

LEAVE A REPLY