ተስፋየ ገብረአብ፡ የወያኔው ኦቶ ዲትሪኽ || መስፍን አረጋ ዘነገደ ኩሽ

ተስፋየ ገብረአብ፡ የወያኔው ኦቶ ዲትሪኽ || መስፍን አረጋ ዘነገደ ኩሽ

ወያኔ፡ የጦቢያው  ናዚ

በፀረ አማራነት ላይ የተመሠረተው ዘረኛው ወያኔበፀይሁዳነት ላይ ከተመሠረተው ዘረኛው ናዚ ጋር በብዙ ረገዶች ይመሰሰላል፡፡

ወያኔ አፍሪቃዊ ናዚ ነው፡፡
መለስ ዜናዊ አፍሪቃዊ ሂትለር ነው፡፡
ስብሐት ነጋ አፍሪቃዊ ዲትሪኽ ኤካርት ነው፡፡  የሂትለርን ዘረኛ አስተሳሰብ የቀረጸው፣ የናዚ ርእዮተ ዓለም የመንፈስ አባት የነበረው፣ የሞርፊን ሱሰኛው፣ ሰካራሙሴሰኛው ዮሐንስ ኤካርት (Johann Dietrich Eckart)
በረከት ስምዖን አፍሪቃዊ ዮሴፍ ጌቤልስ ነው፡፡  የናዚ ማስታወቂያ ሚንስቴር የነበረው ዮሴፍ ጎቤልስ (Joseph Goebbels)
ተስፋየ ገብረአብ ደግሞ አፍሪቃዊ ኦቶ ዲትሪኽ ነው፡፡  የናዚ ፕሬስ መምርያ ኃላፊ የነበረው ያቆብ ዲትሪኽ(Jacob Otto Dietrich)፡፡

መለስ ሙቶ ተቀብሯል፣ ስብሐት ነጋ አንድ እግሩ መቃብር ገብቷል፣ በረከት ታስሯል፣ ተስፋየ ግን አሁንም መርዙን ይነዛል፡፡ የወያኔው ጎቤልስ በረከት ስምዖን፣ ወያኔ በጦቢያውያን ላይ (በተለይም ደግሞ በጠላትነት በፈረጃቸው ባማሮች ላይ) ለፈጸመው ሂትለራዊ ጭፍጨፋ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ተጠያቂ ነው፡፡  ስለዚህም የፈጠራቸውን ወያኔን እንደ ፈጣሪየሚፈሩት ብአዴኖችወያኔ ፍራቻቸው ለቋቸው ቢሆን ኖሮ በረከት መከሰስ የነበረበት በከፍተኛው ወንጀሉ በዘር ማጥፋት እንጅ፣ በንዑስ ወንጀሉ በገንዘብ ማጥፋት አልነበረም፡፡ ለማንኛውም የበረከት ጉዳይ የሌላ ጦማር ርዕስ ስለሆነ፣ የዚህ ጦማር ርዕስ ወደ ሆነው ወደ ወዲ ገብረአብ እንመለስ፡፡

ወዲ ገብረአብ

ልክ እንደ ናዚው የፕሬስ መምርያ ሃላፊ ኦቶ ዲትሪኽ፣ የወያኔው የፕሬስ መምርያ ሃላፊ የወዲ ገብረአብ ዋና ተልዕኮወያኔያዊ ሕትመቶችን (ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችን፣ መጽሐፎችን፣ ወዘተ.) በበላይነት በመቆጣጠር፣ ጦቢያዊነትን አመንምኖ ጎጠኝነትን በማግነን በካፍለህ ግዛው ዘዴ የወያኔንአገዛዝ በማይናወጽ መሠረት ላይ ማቆም ነበር፡፡  በተለይም ደግሞ የወያኔን ጥንካሬ እጅግ አግንኖ የማይጋፉት ባላጋራማስመሰል ይጠበቅበታል፡፡  ወያኔ በተቃዋሚወቹ ውስጥ ለሚያሰማራቸው አፈ ጮሌ ሠርጎ ገቦች ደግሞ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ተቃዋሚወችን የማተራመስ ተልዕኳቸውን እንዲያሳኩ ከፍተኛውን እገዛ ይደርጋል፡፡ በተለይም ደግሞ የጦበያውያንን ጥቃቅን ልዩነቶች አግዝፎ ርስበርስ በማናቆር፣ ሙሉ ትኩረታቸውን ርስበራሳቸው ላይ አድርገው ርስበራሳቸው እንዲጠባበቁ ማድረግ አለበት፡፡

ልክ እንደ ዲትሪኽወዲ ገብረአብም ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት የበቃው፣ አስቀድመው የተሰጡትን ሃላፊነቶች ሁሉንም በሚገባ ተወጥቶ ከወያኔው መሪ ከመለስ ዜናዊ ከፍተኛ አድናቆት፣ ከበሬታና፣ መታመን በማግኘቱ ነው፡፡  ልክ እንደ ዲትሪኽ፣ ተስፋየም አዲሱን ሃላፊነቱን ከተጠበቀው በላይ አሳክቶ የወያኔውን መሪ ይበልጥ በማስደሰቱ፣ ቅናት ቢጤ የለመጠጣቸው ባልደረባወቹ ከመሪው ጋር ሊያቃቅሩት ጥርሳቸውን ነክሰውበት ነበር፡፡

የወያኔን ጥንካሬ አጉኖ ሰማይ እንዲያደርስ በተሰጠው ልዩ ተልዕኮ መሠረት፣ ወያኔ ሰውን ይቅርና ተራሮችን የሚያንቀጠቅጥ የማይጋፉት ባላጋራ ነው ለማለት ‹‹ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ›› የተሰኘውን ልብወለድ ጽፏል፣ አስጽፏል፡፡   ላንድ ቀን ቢተባበሩ ወያኔን ባንድ ቀን የሚጥሉትን አማራንና ኦሮሞን ለማፋጀት ደግሞ ‹‹የቡርቃ ዝምታ›› የተሰኘውን አደገኛ መርዝ ከበረከት ስምዖን ጋር በመተጋገዝ ቀምሟል፡፡

ዲትሪኽ በመጀመርያ ደረጃ የወንጀለኛው የናዚ ድርጅት አባል በመሆኑ ብቻ፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በወንጀለኛው ድርጅት ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነቶች ላይ በነበረበት ወቅት በነዛቸው እኩይ ትርክቶች (narration) ሳቢያ በኒዩርምቤርግ ችሎት (Nuermberg trials) ቁሞ (tried) በፀረሰብ ወንጀል(crime against humanity) ተወንጅሎ፣ ሰባት ዓመት ተፈርዶበት ዘብጥያ ወርዷል፡፡

ፀረሰብ ወንጀል (crime against humanity) ማለት ሰላማዊ ሰወችን ለመፍጀት ወይም ለማፋጀት ሲባል ሥራየ ብሎ የተፈጸመ ማናቸውም ዓይነት እኩይ ድርጊት ማለት ነው፡፡  ፀረሰበ ወንጀል እንደ ጦርነት ወንጀል (war crime) በጦርነት ወቅት ብቻ የሚፈጸም ወንጀል ሳይሆን፣ በጦርነትም፣ በሰላምም፣ በማናቸውም ጊዜ ሊፈጸም ይችላል፡፡  ፀረሰብ ወንጀልን ከሌላ ዓይነት ወንጀል ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ወንጀሉ በስልጣን ላይ ባለው ድርጅት ፖሊሲ ውስጥ በይፋ ወይም በሕቡዕ የተካከተ በመሆኑ፣ ድርጅቱ ወንጀሉን በይፋ ወይም በሕቡዕ የሚደግፈው ወይም ደግሞ የሚቸልለው(condone) (ማለትም ቸል የሚለው ወይም አይቶ እንዳላየ የሚያልፈው) መሆኑ ነው፡፡

ወዲ ገብረአብ ደግሞ በወያኔ ፖሊሲ መሠረት ጠላት ተብሎ የተፈረጀውን አማራን ከኦሮሞ ጋር ለማፋጀት፣ ሥራየ ብሎ እኩይ መጽሐፍ በመጻፍ፣ ለእልፍ አእላፍ አማሮች መገደል፣ መጎሳቆልና መፈናቀል፣ በቀጥታና በተዛዋሪ ተጠያቂ በመሆኑ፣ በፀረሰብ ወንጀል ተከሶ፣ በኢንተርፖል ታድኖ፣ ወደ ጦቢያ መጥቶ፣ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለበት፡፡

ጦቢያን በመሰለች ሮማን ፕሮቻዝካን (Roman Prochazka) መሠረታዊ ሐሳብ በሚያቀነቅኑ ምዕራባውያን ያላሰለሰ ጥረት ጎጠኝነት እንደ ወረርሽኝ በተስፋፋባት አገር ይቅርና፣ ጎጠኝነት በጽኑ ስለሚያስቀጣ ጎጠኝነትና ጎጠኞችከሞላ ጎደል በከሰሙባቸው በምዕራባውያን አገሮች እንኳንሐሳብን የመግለጽ ነጻነት የሚሄደው እስከተወሰነ ደረጃ ብቻ ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል ታዳሚ በታደመበት ቲያትር ቤት፣ በውሸት እሳት ተነሳ ብሎ ኡኡ በማለት ግርግር ፈጥሮ ታዳሚውን ለጉዳት ይልቁንም ደግሞ ለሞት መዳረግ፣ በሞት የሚያስቀጣ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡

ወዲ ገብረአብ ደግሞ በወያኔ ፀራማራ ፖሊሲ መሠረት አማራን ጡት የሚሸልት፣ ፣ ማሕፀን የሚዘረክት፣ አጥንት የሚከተክት፣ በደም የሚፈትት ያረመኔወች አረመኔበሚያስመስል ጽሑፍ የኦሮሞ ጎጠኞችን በተለይም ደግሞ ቄሮወችን መርዞ፣ እልፍ እእላፍ አማሮችን ለመፈናቀል፣ ለመጎሳቆልና ለእልቂት ዳርጓል፡፡  ወዲ ገብረአብን በፀረሰብ ወንጀል ለመክሰስ፣ አንገቶች የተመተሩበት፣ ጦቶች የተቆረጡበት፣ ሆድ እቃወች የተዘረገፉበት የቡራዩ ጭፍጨፋ የቡርቃ ዝምታ መስታዋታዊ ነጸብራቅ (mirror image) መሆኑን መጥቀስ ብቻ ይበቃል፡፡  

የፀረሰብ ወንጀል ሕግ የሚያገለግለው በነጮች ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ብቻ ካልሆነ በስተቀር፣  የናዚ ፕሬስ መምርያ ሃላፊ ኦቶ ዲትሪኽ በእኩይ ሕትመቶቹ ተወንጅሎ ሰባት ዓመት ከጠጣ፣ ከዲትሪኽ ወንጀል ሰባት ጊዜ ሰባ በላይ የከፋ ወንጀል የፈጸመው የወያኔው ፕሬስ መምሪያ ሃላፊ ወደ ገብረአብ ደግሞ ቢያንስ ቢያንስ ሰባት ጊዜ ሰባ መጠጣት አለበት፡፡

ባርባጉጉ፣ በጉራፋርዳ፣ በቡራዩና በመሳሰሉት የሰቆቃ ቦታወች በግፍ በገፍ የፈሰሰው ያማሮች ደም፣ ወደ ገብረአብን በፀረሰብ ወንጀል ተፋረዱልኝ እያለ በጦቢያውያን ሕጋቶወች(lawyers) ጆሮ ላይ ያለማቋረጥ ይደውላል፡፡  የዚህ ጦማር ዓላማ ደግሞ የወዲ ገብረአብ ወንጀል አንዱን ጦቢያዊ ሕጋቶ ወይም ሕጋቲት አነሳስቶ ዶሴ እንዲከፍትበትና፣ ሌሎቻችን ደግሞ ለዶሴ ከፋቹ አቅማችን የሚፈቅደውን አስፈላጊውን እገዛ እንድናደርግ ነው፡፡  እኔ እራሴ መስፍን አረጋ ደግሞ ወዲ ገብረአብ በፀረሰብ ወንጀል ተወንጅሎ ቢያንስ ቢያንስ ወህኒ እንዲወረወር፣ መወርወር የምችለውን ሁሉ እንደምወረውር፣ ገደል በተወረወሩት ጦቢያዊ ሕፃናት ስም በጦቢያ አምላክ ፊት ቃል እገባለሁ፡፡

የወያኔው ዲትሪኽ የወዲ ገብረአብ ወንጀል ግልጽ ስለሆነ፣ ዶሴው ይከፈት እንጅ ለመዝጋት ጊዜ አይፈጅም፡፡  ወንጀለኛው ደብቁኝ፣ ደብቁኝ ሳይል፣ እዩኝ፣ እዩኝ እያለ ዶሴውን መክፈት ደግሞ የጁን የሚያገኝበትን ጊዜ ይበልጥ ያፋጥነዋል፡፡  የጦቢያ ሕጋቶወች ማሕበር፣ አለህ (Ethiopian lawyers association, are you there)?  ጦቢያውያን ፈላሸር (diaspora) ሕጋቶወችስ?

 ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ?

የቡርቃ ዝምታን መጻፍ፣ የመጻፍ ነጸነት ገደብን በከፍተኛ ደረጃ የጣሰ፣ ከፍተኛ ቅጣት የሚያስቀጣ ከፍተኛ ወንጀል ነው፡፡  በሌላ በኩል ግን ተራራን ያንቀጠቀጠ ትውልድ፣ ምንትሴን የገረሰሰ ምንትሴ እያሉ ቱልቱላ መንፋት ውሸትነቱ ቢያጸይፍም ዋና ዓላማው ግን ዝቅተኝነት ስሜት ተጸንሶ፣ ደቁኖ የቀሰሰውን የወያኔን በራስ መተማመን መገንባት ስለሆነ፣ የተስፋየና የበረከት ሙሉ መብት ነው፡፡  በዚህ ቱልቱላ የሚተለተለው ግን በራስ መተማመኑን በውሸት ላይ በመገንባትማንነቱን በድቡሽት ላይ ያነጸው ራሱ ወያኔ ነው፡፡  ይህ በድቡሽት ላይ የተገነባ ማንነት በትንሽ ጩኸት እንደሚፈራርስ በግልጽ የሚያሳይ ዋቢ (reference) ለመፈለግ ደግሞ አንድ ጋዜጠኛ ሶሰት ጊዜ ቢጮኽበት ክፉኛ ደንግጦ በሶስት ቀኑ ከሞተው ከወያኔው መሪ ከለገሰ ዜናዊ መራቅ አያስፈልግም፡፡ ባህያ ቁርበት የተሠራ ቤት ብትነትን ይላል ጅብ የጮኸ ለት፡፡

ተራሮችን እያንቀጠቀጥኩ ባፍሪቃ ተወዳዳሪ ያልነበረውን ታላቅ ጦር ድባቅ መታሁት፣ ሊሞክረኝ የሚፈልግ ደግሞ መንገዱን ጨርቅ ያርግለት እያለ በማንገራበድ ደረቱን የሚነፋውን፣ ‹‹ጎራ ብቻ›› የሆነውን ጉረኛ ድርጅት ላያሌ ዓመታት በመምራት የድርጅቱ መለያ ዓርማ የሆነው ግለሰብ በሶስት ቃሎች ብቻ አንገቱን ደፋ፡፡

ወያኔ ቆራረጥኩት እያለ ጉራ የሚነፋው ለነሱ ለራሳቸው እኩይ ስለሆነባቸው አገር ወዳድ ጦቢያውያን ገዝግዘው የጣሉትን የወደቀ ግንድ እንጅ የጦቢያውያንን ዋርካ አይደለም፡፡  ለዚያውም ደግሞ የወደቀውን ግን የቆራረጠው ሻቢያ እንጅ ወያኔ አልነበረም፡፡  የወያኔ ተግባር ቁርጥራጩን መፈላለጥ ብቻ ነበር፡፡  ለዚያውም ደግሞ አብዛኞቹን ቁርጥራጦቹ የፈላለጡት ፈንጅ ረጋጮቹ ተለጣፊወች፣ በተለይም ደግሞ በወያኔ ቀጭን ትእዛዝ ስሙን ወደ ብኣዴን የለወጠው አዲሱ ለገሰንና ታምራት ላይኔን የመሳሰሉ የለየላቸው ፀራማሮች በማሾ ተፈልገው የተሰበሰቡበት ቅጥረኛ ቡድን ነበር፡፡  

ስለዚህም ወያኔ በሻቢያ አንቀልባ ታዝሎ በተለጣፊወች እየተመራ ሸገር የገባው በእድል እንጅ በድል አልነበረም፡፡  ሸገር እገባለሁ ብሎ ማሰብ ይቅርና ዓልሞ የማያውቀው ወያኔ፣ ሸገር ያስገባውን ዕድል ማመን ስላቃተው የውሸት የጀግንነት ትርክት (narration) ተርክቶ (narrate)፣ ትርክቱን ጦቢያውያን እንዲያምኑለት ይልቁንም ደግሞ እሱ ራሱ እንዲያምንበት ብዙ ደክሟል፡፡  ለዚህ አብነት ደግሞ (ያድዋን ባዕል ላንድ ቀን ለማክበር የሚታክተው ወያኔ) ከሚያዚያ መባቻ እስከ ሰኔ ፍጻሜ ድረስ ሦስት ወራት ሙሉ በግንቦት ሃያ ስም የሚደክመውን ድካም መጥቀስ ይበቃል፡፡  

የወያኔ ድካም በአልትግሬ (non-tigre) ጦቢያውያን ዘንድ መና ቢቀርም፣ ወርቅ ዘር ናችሁ እያለ በሚደልላቸው ትግሬወች ዘንድ ግን የማይናቅ ፍሬ አፍርቶለታል፡፡  ወያኔ ያለመታከት የደጋገመው ውሸት ውነት የመሰላቸው እነዚህ የዋሆች፣ ወያኔ በቅጡ ሳይዋጋ ሰተት ብሎ ሸገር እንደገባ፣ አንድ ጥይት ሳይተኩስ ሰተት ብሎ ከሸገር ሲወጣ ማመን ስላቃታቸው፣ ራሳቸውን ለማሳመን ሌላ የውሸት ትርክት (narration) መተርከት(narrate) ግድ ሆኖባቸዋል፡፡  በስህተት ላይ ስህተት፣ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፡፡  ጉድጓድ የገባ የጨነቀው አውሬ፣ ጉድጓዱን በጥፍሩ እየቆፈረ የበለጠ ያርቀዋል፡፡

በተለይም ደግሞ ከሌላው ጦቢያዊ የተለያችሁ ወርቅ ጀግኖች ናችሁ በማለት ወያኔ የዋሻቸውን ንጹሕ ውሸት በሙሉ ልባቸው ስላመኑ፣ ካማራ ጋር ጦርነት ገጥመን ‹‹የቀሩትን መሬቶቻችንን›› በቀናት ውስጥ እናስመልስ እያሉ በእሳት ለመጫወት ይቋምጣሉ፡፡

 አይበጅም ሲሉት ይበጃል ብሎ

በጫረው እሳት ሞተ ተቃጥሎ፡፡

እርግጥ ነው፣ ወያኔ በዕድል ሸገር ገብቶ የመንግሥት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረ በኋላ፣ በዋና ጠላትነት የፈረጀውን ራሱን ከውጭ ጠላት እንጅ ካገር በቀል አረመኔ ለመከላከል ያልተደራጀውን አማራ የሚባለውን ሕዝብ እንደ ቅጠል አርግፎታል፡፡  የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር ነውና፣ ወያኔ በማራ ላይ ያወረደው መከራ፣ ግራኝናጣልያን በድምር ካወረዱበት መከራ እጅግ ይከፋል፡፡  ግን ለምን?

አማራ መኻል ያደገው ተስፈየ ገብረአብ ባማራ ላይ በዚህ ደረጃ ቂም የያዘበት ምክኒያት ምንድን ነው?  ይህ የካልጅኖ (million) ብር ጥያቄ ነው፡፡  ይህን ጥያቄ የሚያጠቃልለው የሳልጅኖ (billion) ብር ጥያቄ ደግሞ

‹‹ ያማራ ለማኙ እንኳን ከትግሬ አይለምንም›› ያለው የስብሐት ነጋ የመንፈስ ልጆች የሆኑት፣
በቀያኔ (poet) ከበደ ሚካኤል ‹‹ተረትና ምሳሌ›› ላይ ያነበበውን የካሊጎላን ታሪክ በመለወጥ ‹‹ያማራን አንገት አንድ አድርገው ቢሰጡኝ፣ አንዴ ቆርጨው እገላገል ነበር›› ያለውን ለገሰ ዜናዊን የሚያመልኩት፣
አማራን እንደ ሲጋራ ረግጠን ጥለነዋል፣ ያማራንና የኦርቶዶክስን አከርካሪ ሰብረነዋል ወዘተ.  እያሉ የሚሞካሹት            

የወያኔ ጎጠኞች ባማራ ጥላቻ ያበዱበት ምክኒያት ምንድን ነው የሚለው ነው?  አማራን አዋረድን ብለው በእስረኛ አፍ ላይ በመጸዳዳት ራሳቸውን እስከሚያዋርዱ ድረስ የገፋቸው ጥላቻ መሠረቱ ምንድን ነው?

ለመሆን የማይችሉትን ለመሆን ስለሚመኙ ካልበላሁት ጭሬ ልድፋው ባለችው እንዳቆ እሳቤ መሠረት ይሆን?  ጦቢያዊ ዮዳተንታኞች (psychoanalysts) ምን ትላላችሁ?  ለዚህ ያልሆነ ዮዳትንተና (psychonalysis) ለምን ሊሆን ነው?  ለክረምት ያልሆነ በርኖስ ይበጣጠስ፡፡

ወያኔ እኩይ ቱልቀዳ (propaganda) በፈጠረው አደገኛ ብዥታ ሳቢያ፣ በትግራይ ልሂቅ ማለት ማራ ጥላቸው የላቀ ማለት እየሆነ መጥቷል፡፡  የግለሰቡ ጥላቻ የበለጠ ሲንር፣ የልሂቅነቱ ደረጃ በዚያው ልክ ይንራል፡፡  በወያኔ የውሸት ትርክትራሳቸውን ሰማይ ያደረሱት እነዚህ ልሂቃን፣ የእውነታ መስታወት በተቃራኒው ቀላይ ሰለሚያሳያቸው፣  እውነታውን ተቀብለው የሚበጀውን ከመሻት ይልቅ የወያኔን ውሸት ሙጥኝ ብለው ዝቅጠታቸውን አማራ በሚሉት ጦቢያዊ ያሳብባሉ፡፡  ያልነበሩትን እንዲህ ነበርን ይሉና፣ አሁንስ ሲባሉ እድሜ ላማራ ይላሉ፡፡

የወያኔ ጎጠኞች ትግራዋይነታቸውን የሚገልጹት ባማራ ጥላቻቸው ስለሆነ፣ ማናቸውም ድርጊት አማራ የሚሉትን ሕዝብ ኢምንት የሚጎዳ እስከሆነ ድረስ እነሱን ጃምንትቢጎዳም ከበሮ ያነሱለታል፡፡  ማናቸውም እሳት አማራን በወላፈኑ እስከገረፈ ድረስ እነሱን በነበልባሉ የሚለበልብ፣ በፍሙ የሚያንጨረጭር ቢሆንም እሳቱን ለመለኮስ፣ ለኩሰው ለማቀጣጠል፣ አቀጣጥለው ለማንቦግቦግ አያንገራግሩም፡፡ ያማራ ደሳሳ ጎጆ እስከፈረሰ ድረስ የነሱ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ቢደረመስ፣ ያማራ ሐብት እስከተዘገነ ድረስ የነሱ ሐብት ቢታፈስ፣ ያማራ ስም እስከጠለሸ ድረስ የነሱ ሐበሻዊ ስም ቢጠቀርሽ፣ የ 50% አማራ ሐይማኖት እስከጠፋ ድረስ የ 96%  ትግሬ ሐይማኖት ቢጠፋ፣ ባጠቃላይ ደግሞ ያማራ አንድ ዓይን እስከጠፋ ድረስ የነሱ ሁለቱም ቢደረገም ዴንታ የላቸውም፡፡

የኦነጋውያን እሳት አማራን ቢበላ፣ ቀጥሎ የሚበላው እነሱን እንደሆነ በርግጠኝነት እያወቁ፣ እሳቱን ለማንቀልቀል ይንቀለቀላሉ፡፡  ጃዋር ሙሐመድና በቀለ ገርባ በመድረክ፣ ኦዴፓ ደግሞ በመግለጫ ሸገር የኦሮሞ ናት ሲሉ፣ የወያኔ ጎጠኞች ምንትሳቸው ቄጠማ ይቆርጣል፡፡

አስራ ሰባት ዓመት በሌት ጅብነት፣ ሃያ ሰባት ዓመት ደግሞ በዝብ ቀትርነት ልክ የሌለው ሐብት ዘረፉ፡፡  ከዚህ የዝርፊያ ሐብት ጥቂቱን በመቆንጠር ደግሞ ባንድ ቀን ባጸደቁትአፓርታዊዳዊ የሊዝ አዋጅ አማካኝነት ካማራና ከጉራጌ በነጠቁት ርስት ላይ አብዛኞቹን ያዲሳባ ሕንፃወች አቆሙ፡፡  ስለዚህም የኦነጋውያን እቅድ ቢሳካ ከማንምና ከምንም በላይ የሚጎዱት እነሱ መሆናቸውን ነጋሪ አያስፈልጋቸውም፡፡እንዲህም ሆኖ እቅዱን ለማሳካት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡  የታከለ ኡማ ዓላማ ያማራንና የጉራጌን ቆሎ ይዞ ወደ ትግሬ አሻሮ መጠጋት እንደሆነ ይበልጥና ይበልጥ ግልጽ እየሆነላቸው፣ በኦቦ ታከለ የመጣ ባይናችን መጣ ይላሉ፡፡  

እነዚህ ዓይነቶቹን ምን እንበላቸው?  አጥፍቶ ጠፊ እንዳንላቸው፣ የሚመኙት አማራን አጥፍተው ራሳቸውን ማጥፋት ሳይሆን፣ አማራን አጥፍተው በኦነግ ኢንትራሐምዌ መጥፋት ነው፡፡  አጣፍቶ ጠፊ ይገልጻቸው ይሆን?

ኦነጋውያን በማያሻማ ግልጽ ቋንቋ እንደገለጹትመሠረታዊ ዓላማቸው በማፈናቀል፣ አሰፋፈርን በመቀየርና በመሳሰሉት ዘዴወች ሐበሻ የሚሉትን ትግሬወችን የሚያካትት ሰፊ ሕዝብአብናቶቹ (አባቶቹና እናቶቹ) በደም ባጥንታቸው ባስከበሩለት በገዛ አገሩ በጦቢያ ላይ የበይ ተመልካች ማድረግ ነው፡፡  ስለዚህም የትግሬ ልሂቃን ባማራ ጥላቻ ባይታወሩ ኖሮ፣የማንነታቸው መግለጫ የሆነውን ጦቢያዊነትን እጅግ አዳክሞ እዚህ ግባ ይባል ያልነበረው ኦነግ ሊያጠፋው እስከሚዝትበት ደረጃ ያደረሰውን ወያኔን በጽኑ ባወገዙት ነበር፡፡  ቅሬታ ቢኖራቸውም ቅሬታቸውን ለጊዜው ቸል ብለው በዋናው ጠላት በኦነግ ላይ ባተኮሩ ነበር፡፡

እባብ ባለበት ጉንዳን አይፈራም፡፡  አብናቶቻችን በጣልያን ላይ፣ ቻይኖችም በጃፓኖች ላይ ያደረጉት ይህንኑ ነው፡፡ ጦቢያውያን አንድ ከሆኑ ደግሞ ፀረጦቢያውያን አንድ ቀን አያድሩም፡፡  ታከለ ኡማ ያማራንና የትግሬን ቆሎ ዘግኘ ወደ ትግሬ አሻሮ እጠጋለሁ ሲል፣ አንድ ጥሬ ሳያነሳ እጁን ይሰበስብ፣ ካልሰበሰበም ይቆረጥ ነበር፡፡

የወያኔ ጎጠኞችን በተመለከተ ሌላው መሠረታዊ ጥያቄ ራሴን ዘወትር ብጠይቅም መልስ ያላገኘሁለት፣ ነብታሚ (professor) ጥላሁን ይልማ ባንድ ወቅት ካነሱት ነጥብ ጋር የተዛመደ ጥያቄ ነው፡፡  አንዴ በዘመነ መሳፍንት፣ ቀጥሎ ከንግሊዝ ወራሪ ጋር፣ ቀጥሎ ከጣልያን ቅኝ ገዥ ጋር፣ ቀጥሎከተገንጣይ ሻቢያ ጋር፣ ቀጥሎ እነሱ ራሳቸው፣ አሁን ደግሞ ኦነግ ጋር በመተባበር ካማራ ጋር የሚያኩሉትን (equate) ጦቢያዊነትን ለማጥፋት ዝንታለም የሚጥሩትን፣ ፀረጦቢያዊነታቸው መቸም የማይድን በሽታ የሆነባቸውን ዮዳሲናዊ (psychological) ሕመምተኞች ይዞ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ መመረሽ እስከ መቸ ይቀጥላል?

የለውጡ ቀውሶች

በመጨረሻም በቅርብ የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ ባገራችን የተከሰተው ከፍተኛ ቀውስ መንስዔው ምንድን ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡  ወያኔ በትረ ስልጣን ከያዘ በኋላ ያደረገው የጦቢያን ሕዝብ ብሔር ብሔረሰብ በሚባሉ ጎላወች ውስጥ ጨምሮጎላወቹን ክልሎች በሚባሉ ምድጃወች ላይ ጥዶ፣ ዘረኝነት የሚባለውን እሳት እያደደየጎላወቹንአስመርቃኝ የገራባ ሐውዛ ማንተክተክ ነበር፡፡  ይህን ያደርግ የነበረው ደግሞ በትረ ስልጣኑን ከሚነጠቅበት ደረጃ ላይ ከደረሰ ፣ በእኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል እሳቤ መሠረት የጎላውን እፊያ በርግዶ ከፍቶ ሐውዛውን በማገንፈል ጦቢያውያንን አጨራርሶ ጦቢያንና ጦቢያዊነትን ለማጥፋት ነበር፡፡

ሰው አሳቢ እግዜር ፈጻሚ ነውና፣ ወያኔ ባልጠበቀው ሰዓትና ባላሰበው ዘዴ በትረ ስልጣኑን ተነጠቀ፡፡  በትረ ስልጣኑን የነጠቀው ቡድን ደግሞ (እሳቱን ዘረኝነት ለማጥፋት ጊዜ ቢፈጅም) እሳት ቆስቋሹን ወያኔን እጁን እንዲሰበስብ ሳያደርግ የጎላውን እፊያ በዝግታ ሲከፍተው፣ የጎላው ሐውዛበዝግታ እየገነፈለ ቀውሱን አስከተለ፡፡  ምንም እንኳን ይህ ቀውስ ከግራኝ አህመድና ግራኝን ተከትሎ ከተከሰተው የኦሮሞ መስፋፋት በኋላ ባገራችን ውስጥ በዚህ ደረጃ ተከስቶ የማያውቅ አሰቃቂ ቀውስ ቢሆንም፣ ወያኔ እንዳሰበው የጎላውን እፊያ በርግዶት ቢሆን ኖሮ ይከሰት ከነበረው እጅግ አሰቃቂ ቀውስ ጋር ሲነጻጸር ግን ኢምንት ነው፡፡  

የለውጡ ክትል የሆነውን ይህን ከፍተኛ ቀውስ በተመለከተ ሁለት አማራጮች አሉ፡፡  የመጀመርያው አማራጭ፣ እሳት ቆስቋሹን ወያኔን እጁን እንዲሰበሰብ አድርጎ የጎላውን ዋና ተንተክታኪ ኦነግን በማማሰል ምርቃናው እንዲበርድለትና እንዲሰክን ማድረግ ነው፡፡  ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ እሳት ቆስቋሹን መረን ለቆ፣ ዋናው ተንተክታኪ ኦነግ በምርቃና መገንፈሉን እንዲቀጥልና የጦቢያን አብዛኛውን ክፍል እንዲያዳርስ መፍቀድ ነው፡፡  ባለመታደል ‹‹ቲም ለማ›› የሚባለው ዐብይንና ለማን የሚያካትተው ቡድን የመረጠው ሁለተኛውን አማራጭ እንደሆነ ይበልጥና ይበልጥ እየመሰለ መጥቷል፡፡  ይህ ቡድን በእውነትም የመረጠው ሁለተኛውን አማራጭ ከሆነ ደግሞ በእጅጉ ተሳስቷል፣ ገንፍሎ አገር ያዳረሰ ማናቸውም ነገር አይቀሬ እጣው ቆሻሻ ተብሎ ተጠራርጎ መወገድ ነውና፡፡  እንኳን ግንፋይ፣ ማርም ሲበዛ ይመራል፡፡    

ጦቢያውያን በንግግር ሳይደለሉ ድርጊት ላይ ብቻ በማተኮርኦነግ በምርቃና እየገነፈለ በመፍሰስ አልኦሮሞ (non-oromo) ጦቢያውያንን በገዛ አገራቸው ላይ ባይተዋር ማድረጉን እንዲቀጥል የሚፈቀድለትና የሚመቻችለት ከሆነ፣ ግንፋዩን ጠራርገው ለማስወገድ ሽርጣቸውን ታጥቀው፣ መጥረጊያቸውን አዘጋጅተው መጠባበቅ አለባቸው፡፡  ያልጠረጠረ ተመነጠረ፡፡  

የሚቀጥለው ጦማር የሚያተኩረው የቀማኞች ዲሞክራሲ በሆነው ኦነጋውያን አለትርጉሙ ተርጉመው አላግባብ በሚኮፈሱበት ገዳ ሥርዓት ላይ ነው፡፡  እስከዚያው የጦቢያ አምላክ አብሔር ይጠብቅዋ፣ ይጠብቀን፡፡  ስላነበባችሁኝ አኮቴ (thank you)፡፡

መስፍን አረጋ ዘነገደ ኩሽ

የትብቱ ቀብር ደሴ ሳላይሽ፡፡

               mesfin.arega@gmail.com

LEAVE A REPLY