ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰባት እስላማዊ ባንኮች በመቋቋም ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ እንደ አዲስ ማለዳ ዘገባ ከሆነ ዘምዘም፣ ሂጅራ፣ ነጃሺ፣ ኩሽ እና ሁዳ የተሰኙት፣ እንዲሁም ሁለት ስያሜያቸውን ያልመረጡ ባንኮች በምስረታ ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት፤ በተሰጠ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ወደ ስራ እንዳይገባ የተከለከለው ዘምዘም ባንክ፤ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁንም ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል፡፡
በአዋጅ ከወለድ ነፃ ባንክ ማቋቋም ያልተከለከለ ቢሆንም፤ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት ባንኮች ምስረታቸውን እውን ሳያደርጉ እስካሁን ቆይተዋል፡፡ ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው “የአብሮነትና የምስጋና የኢፍጣር ፕሮግራም” ላይ፤ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ እስላማዊ ባንክ እንዲቋቋም መንግስት አስፈላጊውን ትብብር
እንደሚያደርግ ቃል መግባታችው አይዘነጋም፡፡