አንበሳ አውቶቢስና ሸገር ባስ ለኢድ በዓል፤ ቀኑን ሙሉ የነጻ አገልግሎት ሲሰጡ ዋሉ

አንበሳ አውቶቢስና ሸገር ባስ ለኢድ በዓል፤ ቀኑን ሙሉ የነጻ አገልግሎት ሲሰጡ ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || 1 ሺህ 440ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በዛሬው እለት በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

በተለይም በአ/አ ስታዲየም የእምነቱ ተከታዮች፣ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሶላት ሲከበር፤የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንድሪስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተገኝተዋል።

“ኢድ ማለት በየዓመቱ የሚመላለስ ደስታ ነው” ያሉት ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንድሪስ ፤ የዘንድሮው ኢድ የሙስሊሙ አንድነት እና ሰላም የተጠናከረበት በመሆኑ ደስታውን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ጠ/ሚ/ሩ እና ሌሎች አካላት “ኢፍጣር” አዘጋጅተው መጋበዛቸው፣ እንዲሁም የክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች የኢድ ሶላት መስገጃን ማፅዳታቸው፤ የዘንድሮውን ኢድ ድምቀት እንደጨመረው በቂ ማረጋገጫ መሆኑን ያመላከቱት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንድሪስ፤ ይህ አንድነት፣ መከባበር፣ ህዝባዊ፣ ሀገራዊ እና ሃይማኖታዊ እንዲሆንም ጠይቀዋል።

በተያያዘ ዜና የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በአ/አ ከተማ ውስጥ የሚሰሩ የአንበሳ አውቶቢሶችና የሸገር ባስ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ሕብረተሰቡን ከጧት እስከ ማታ ድረስ በነጻ ሲያመላልሱ ውለዋል፡፡ የጠ/ሚ/ር ዐቢይ መንግስት በዓሉን መሰረት አድርጎ መላው ሕዝብ አገልግሎት እንዲያገኝ ያደረገበት አዲስ መንገድ ብዙዎችን አስደስቷል፡፡

LEAVE A REPLY