ግብረሰዶማውያኑ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጡ የቅዱስ ላሊበላ ቤተ ክርስቲያን አስጠነቀቀች

ግብረሰዶማውያኑ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጡ የቅዱስ ላሊበላ ቤተ ክርስቲያን አስጠነቀቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ግብረሰዶማውያን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የሚደርጉትን ጉብኝት በእጅጉ እንደሚቃወምና ጉብኝቱ ዕውን የሚሆንበት አጋጣሚ ከተከሰተ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱን እንደማይወስድ በሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት የቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ
አስተዳደር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በአሜሪካ የሚገኘው “ቶቶ” የተሰኘው የግብረሰዶም አስጎብኚ ድርጅት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣና የጉብኝቱ መዳረሻውን የሀገር ሐብት፣ የዓለም ቅርስ ሆኖ በክብር መዝገብ በሰፈረው በቅዱስ ላሊበላ ገዳም እንደሚያደርግ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች መግለፁን ተከትሎ፤ የቅ/ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር በቀን 26/09/2011 ዓ.ም፣ በቁጥር 1992 – 2011 ለኢ.ፌዴ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ፤ መንግስት አስጎብኚ ድርጅቱና አባላቱ ወደ አገራችን እንዳይገቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደያደርግ አሳስቧል፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ በቅዱስ ላሊበላ አካባቢ ከሚኖሩ አማኞች ባሻገር፣ መላው የአገራችን ሕዝብ እንደ ዐይኑ ብሌን የሚያየውን ቅዱስ ቦታ ግብረሰዶማውያኑ በድፍረት እንዲረግጡት ከተደረገ ግን፤ ምዕመኑ ያንን ለማየት የሚያስችል አቅም ስለማይኖረው፣ ለሚደርሰው ችግር በሙሉ ማንም ኃላፊነቱን እንደማይወስድ ለጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ለተለያዩ የመንግስትና የሀይማኖት ተቋማት በግልባጭ ከተላከው ደብዳቤ መረዳት ተችሏል፡፡

LEAVE A REPLY