ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ አባል በሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኩባንያ አማካይነት ለሚገነባው “ሸገር ዳቦ” ለተሰኘው የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡
ሼህ ሞሐመድ አል አሙዲ የከተማዋን የዳቦ፣ የስንዴ፣ ዱቄትና የዘይት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለው ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተረክበው ለማጠናቀቅ በመስማማታቸውና ከፍተኛ ፍላጎት በማሳየታቸው በቅድሚያ የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካው ግንባታ ጅምር ሂደት ዕውን ሊሆን እንደቻለ ነው ለማወቅ የተቻለው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መሀል አንዱ መሆኑ የተነገረለት ፋብሪካን የሚያስገነባው የሆራይዘን ፕላንቴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ የፋብሪካው የማሽን ግዥ በአንድ ወር ተጠናቆ በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ፋብሪካው ተጠናቆ ስራ እንደጀመረ በመጀመሪያው ዙር፤ በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ ሲያመርት፣ የአንድ ዳቦ ዋጋም ወደ 0.75 ሳንቲም ዝቅ ሊል እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ሸዋ ዳቦ በመባል ይሚታወቀው የረጅም እድሜ ልምድ ያለው ፋብሪካ ከመንግስት ይደረግለት የነበርው ድጎማ ከጥቂት ወራት ወዲህ በመቋረጡ ምክንያት በዳቦ ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጎ እንደነበር ይታውቃል:: አዲሱ ፋብሪካ በሸዋ ዳቦ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ ከባድ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል