ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በመጪው የክረምት ወራት ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ትምህርት ቤቶቿን እንደምታድስ ጊዜያዊ ከንቲባው ኢ/ር ታከሉ ኡማ ገልፀዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በዳግማዊ ምንሊክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ያካሄዱት ም/ክንቲባ ታከለ ኡማ፣ መስተዳድራቸው በክረምቱ ወራት በተለይም በትምህርቱ ዘርፍ የተለያዩ ተግባራትን ለማካሄድ ዕቅድ መያዙንጠቁመዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከሚያደርገው የት/ቤቶች ዕድሳት ባሻገር፣ በመጪው የትምህርት ዘመን ከቅድመ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችንለመመገብ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ተናግረዋል፡፡
“ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ልጆቻችሁን የምታስተምሩ ወላጆች፣ የትምህርት ቁሳቁስና ለተማሪዎች የደንብ ልብስ ወጪ ፈፅሞ ሊያስጨንቃችሁ አይገባም፤ እሱን በእኔ ጣሉት” ሲሉ የተደመጡት ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ፤ በቀጣይ ዓመት ከ1ኛ እስከ 12 ክፍል በመንግስት ት/ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና የደንብ ልብስ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚቀርብ ይፋ አድርገዋል፡፡
ይህ የከንቲባው አዲስ እቅድ ከወዲሁ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው:: አነስተኛ ገቢ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ልጆቻቸውን በመንግስት ት/ቤቶች ማስተማር መሆኑ የታወቃል:: በዚህም ምክንያት የከተማ አስተዳሩ በአዲሱ የትምህርት ዘመን የወላጆችን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ወጪ መጋራቱ በእጅጉ የሚያስመሰግነው መሆኑን ገልጸዋል:: በአንጻሩ ደግሞ ሌሎች “ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ሊኖራት ይገባል” የሚለው የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኢ/ር ታከለ ኡማን ላይ እምነት እንደሌላቸው ይገልጻሉ:: በተለይ ኢንጅነሩ ከያዙት የአዲስ አበባን ነዋሪ በተለያዩ መንገዶች የማፈናቀል ይጠቅሳሉ:: በማያያዝም በስውር እያስፈፀሙት ነው ተብለው ከሚታሙበት የኦሮሞ ተወላጆችን በብዛት በከተማዋ የማስረፅ እንቅስቃሴ ያስከተለውን ተቃውሞ በማርገብ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ታስቦ የሚገበር ስራ ነው” ሲሉ የከንቲባውን አዲስ እቅድ የሚያጣጥሉ አስተያየቶች እየተሰሙ ነው፡፡
ጊዜያዊ ከንቲባ ታከለ ኡማ ዛሬ ውሏችውን ያደረጉት ከመንገድ ስፋትና ከከተማዋ አዲስ የግንባታ ዕቅድ የተነሳ ግማሽ አካሉ እንደሚፈርስ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በተነገረለት ታሪካዊው የዳግማዊ ምንሊክ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ነው::