ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግሮችና ሀሰተኛ መረጃዎች ከመተላለፍ ጋር በተያያዘ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ውይይት በጠቅላይ ዓቃቤሕግ አዘጋጅነት ተጀምሯል፡፡ በጉባአኤው ምሁራን፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተሳትፈዋል::
ንጹሃን ዜጎችን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ድረስ እያስከፈለ ነው:: ርቂቅ አዋጁ የጥላቻ ንግግሮችንና የሃሰተኛ መረጃዎችን ስርጭት ለመከላከል ያስችላል ተብሏል:: የጥላቻ ንግግሮች እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ወንጀል ረቂቅ ላይ ተጋባዥ አባላቱ ሰፊ ውይይት እያካሄዱ እንደሆነ ተጠቁሟል::
ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ እንዲህ ዓይነት ህጎችን ተግባራዊ ያደረጉ ሀገራት በአንፃሩ ችግሮችን መከላከል ከመቻላቸውም ባሻገር ዜጎቻቸው ሰላማዊ ኑሮን መምራት እንደቻሉ ይታወቃል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በማህበራዊ ሚዲያው የሚናፈሱ መሰረት የሌላቸው መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮች በዘር፣ በሃይማኖትና በሌሎች ልዩነቶች ላይ የሚያደርሱትን ተጽዕኖ ለመከላከል የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል:: በአፈጻጸም ሂደት ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ላይ ሀሳብ ቀርቧል።