ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በፓሪስ በመካሄድ ላይ ባለው የፊፋ የሴቶች እግር ኳስ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተገኙ:: ፐሬዝዳንት ሣህለወርቅ በስብሰባው ላይ ይተገኙት ጂያን ፋንቲኢኖ በድጋሚ የፊፋ ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ ማግስት ነው::
ፐሬዝዳንቷ የሴቶች እግር ኳስ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻልን ያሳየ ቢሆንም፣ የወንዶችን ያህል ትልቅ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰበት አለመሆኑ ዕድገቱን ሊያቀላጥፈው እንዳልቻለ ገልጸዋል። በሴቶች ስፓርት ላይ ብዙ መስራት እንደሚገባ የተናገሩት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሴቶቸን የስፖርት ተሳትፎ ለማሳደግ የምናፈሰው መዋዕለንዋይ በአንድ መቶ እጥፍ መልሶ ቢከፍለን እንጂ ፈጽሞ እንደማያከስረን እርግጠኛ ነኝ ሲሉ ተደምጠዋል።
“ሴቶች ማድረግ ይችላሉና እነሱ ላይ ትኩረት ሰጥተን ከሰራን ውጤትም ለውጥም ማምጣት ይቻላል” ያሉት ፕሬዝዳንቷ ፊፋ በቀጣይ ለሴቶች ስፖርት የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል የሚል ዕምነት እንዳላቸው በጉባዔው ላይ መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ የ32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን እንዲመራ በካፍ ተመርጧል፡፡ ከሰኔ21 እስከ ሐምሌ 19 በግብጽ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ባምላክ በዋና ዳኝነት ሲመረጥ ሳሙኤል ተመስገን ደግሞ በረዳት ዳኝነት ጨዋታዎችን እንደሚመሩ ይፋ ሆኗል፡፡