ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ በቀጣዩ አመት ወደ ውጭ የምትልከው የቡና ምርት ጭማሪ እንደሚያሳይ የአሜሪካ የግብርና መምሪያ ክፍል
መጠቆሙን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ግብርና መምሪያ ክፍል ባወጣው መረጃን መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያ ከቀጣዩ ጥቅምት እስከ መስከረም ወር ድረስ ወደ ውጭ የምትልከው የቡና ምርት ጭማሪ ሊያሳይ እንደሚችል ነው የተነገረው፡፡
240 ሺህ ቶን የቡና ምርት በቀጣዩ አመት ወደ ውጭ እንደሚላክ መረጃው ግምቱን አስቀምጧል:: ይህ ቁጥር ዘንድሮ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከላከችው የቡናምርት አንጻር የ0 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ ያሳያል:: ዜናው በተመሳሳይ ሁኔታ የሃገር ውስጥ የቡና ፍጆታም በቀጣዩ አመት በ2 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ ሊያድግ እንደሚችል ያመላከተ ሲሆን በአጠቃላይ አሁን የሃገሪቱ ከፍተኛ የቡና ምርት ጭማሪ አሳይቷል:: በቀጣዩ አመት 7 ነጥብ 35 ሚሊየን ቶን ቡና ይመረታል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።