የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው || መስፍን ማሞ ተሰማ

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው || መስፍን ማሞ ተሰማ

ሠላም ለናንተ ይሁን! 

ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ እስከ 1966 / መጨረሻ ድረስየመሯትና የህዝቧም እረኛ ሆነው እንደ ቀስተ ደመና ቀለማት ህብር ውበት ሁሉ የተለያየ ባህል ባለቤትና ቋንቋተናጋሪ ህዝቧን በአንድ መሶብ አሰባስበው መተሳሰብ መዋለድ ህብረትና ሀገራዊ ማንነት ተዋህደውና አምረው እንዲሰርፅና እንዲኖር ያስቻሉት እኒያ መሪዎቿ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረባቸው ነበሩ የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖት አባቶችም ለእምነቱ ህግጋት ተገዢ ፈጣሪያቸውንና አማንያንን አገልጋይ ነበሩ ፈጣሪም ከእነርሱ ጋር ነበረ 

የቀደሙት የኢትዮጵያ መሪዎች በፈሪሃ እግዚአብሄር እየተመሩ የህዝባቸው መልካም እረኛ ሆነውና  በሀይማኖቶችም አከባብረውና አስማምተው ህዝባቸውን አኖሩ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር አቆሙ ከጠላት ጠበቁ 

የኢትዮጵያ ህዝብም ልበ ቅን በራሱ ላይ ሊያደርጉበት የማይፈልገውን በጎረቤቱና በሌሎች ወገኖቹ ላይ የማያደርግ፣ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረበት ሆኖ ተባብሮና ተሰባስቦ ኖረ። ለዘመናት የተገነባው ይህ ሀገራዊ/ኢትዮጵያዊ እሴት በዘመነደርግ ፈተና ገጠመው ፈተናው ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ነበርእንጂ ዘርን ተገን አድርጎ ሀገራዊና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የዳጠ የጨፈለቀ ያዋረደና ኢትዮጵያዊነትን  ከሰውነት ተራያወረደ አልነበረም ለዚህ ብቸኛ ተጠያቂውና ሀላፊው የዘር ድርጅቶቹ ግንባር የኢህአዴግ መንግሥት ነው  

ኢህአዴግ ቤተ መንግሥት ከገባበት ቀን ጀምሮ እንደ መንግሥት የዘር ኮሌራ በመላው ኢትዮጵያ አራባ ኮተኮተአሳደገ እነሆ ፍሬው ሶስት ሚሊዮን ህዝብ ለመፈናቀል፣ አእላፍን ለህልፈትና ለመከራ ዳርጓል ኢህአዴግ መሰረቱ፣ ዕድገቱና ቀጣይ ህልውናው የዘር ኮሌራ መዋቅሩ ነው

እነሆ ቀደምት ነገሥታቱን በማያሰልስ ፀሎታቸውና በቅንነታቸው ከቤተ መንግሥት ቅጥር ሆኖ ይረዳቸው የነበረው ፈጣሪ አምላክ እግዚአብሄር 1967 /መስከረም ሁለትፈጣሪን የካዱቤተ መንግሥቱን ሲቆጣጠሩ የእግዚአብሄር መንፈስ ከቤተ መንግሥት ወጣ። አዎ! እግዚአብሄር ከቤተ መንግሥት ራቀ 

እነሆ ደግሞ በዚያው ዘመን የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አባቶች እግዚአብሄርን አሳዘኑ በእጃቸው የሾሟቸውን ቅዱስ ጳጳስአቡነ ቴዎፍሎስን አሳልፈው ሰጡ ለምድራዊው ጉልበተኛተገዙ እነሆ ደግሞ ይህንን በዘመነ ኢህአዴግ ደገሙፈጣሪም አመረረ በምድሪቱ ላይ ሀጢያት በረታ በረከተ 

እነሆ በዘር አርማታ ላይ የቆመው ኢህአዴግ ለሰማይም ለምድርም የከበደ ነውር በምድሪቱና በልጆቿ ላይ ፈፀመ። ኢትዮጵያ የኢህአዴግን ሀጢያት መሸከም አቃታት 

ለመሆኑ በነውራቸው ተፀፅተው መንበረ ሥልጣናቸውን የለቀቁ ይቅርታ ጠይቀው አንገታቸውን የደፉ ኢህአዴጎች ስንቶች ናቸው?  

ቤተ ዕምነቶችን ሲያመሳቅሉና ሲያናጉ የኖሩት የት ነው ዛሬያሉትየሀገርን ሀብት ንብረት መቀመቅ የከተቱ የት ናቸው? የኢትዮጵያን ስም መጥራት ተጠያፊዎቹሀገሪቷባዮቹ ኢህአዴጎች የት ናቸው? የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ሳይሆንክብርና ሞገስ ለታላቁ መሪባዮቹ የትናቸው? በሥልጣናቸው ሲታበዩ የኖሩ ዛሬምለድሀ አደሩ የማይፈርዱ ለመበለቲቱ እንባ ለህፃናቱም ዋይታ የሚራራልብ የሚሰማ ጆሮ የሌላቸው በምድሪቱ የሞሉ የኢህአዴግ ገዢዎች ስንትና ስንት ናቸው?

እነሆ በኢትዮጵያ ምድር የሆነውና እየሆነ ያለው ሁሉ ሰለዚህነው እግዚአብሄር ለኢትዮጵያና ለየዋሁ ህዝቧ ፊቱንይመልስ ሀዘኗንም በቃሽ ይበላት!

ሰኔ 2011 ዓ/ም (ጁን 2019)

ሲድኒ አውስትራሊያ

mmtessema@gmail.com

LEAVE A REPLY