ቅዱስ ሲኖዶስ ለ18 ቀናት ሲካሂድ የነበረውን ጉባዔ አጠናቀቀ

ቅዱስ ሲኖዶስ ለ18 ቀናት ሲካሂድ የነበረውን ጉባዔ አጠናቀቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ለ18 ቀናት ሲያካሂደው የነበረውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አጠናቋል። የጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎ በቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊና ማህበራዊ ጉዳዮች በተመለከተም ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል።

ቤተክርስቲያኗ ተወርሰውባት የነበሩት፣ ዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርት ቤት ፊትለፊት የሚገኙት ሁለት ህንፃዎች እንዲመለሱላት፣ በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ መወሰኑን ተከትሎ አስፈላጊ ሰነዶች በመሟላታቸው የርክክብ ስነስርዓት እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል:: የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ረሻድ ጀማልም የቤቶቹን ሰነዶች ለቡፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስረክበዋል።

ምልአተ ጉባኤው በተ.ቁ(22) በያዘው በዚኹ አጀንዳ፣ ዛሬ ዓርብ፣ ግንቦት 30 ቀን ባካሔደው ምርጫ፣ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማዳራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ያሬድን፣ በከፍተኛ ድምፅ መርጧል::፣ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትን በጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት እንዲመሩም መርጠዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ለአስራ ስምንት ቀናት በቆየው የሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ሽልማቶች መልካም ነገር ለሰሩ ሰዎች ተበርክቷል፡፡

ላለፉት ሦስት ዓመታት በጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት ያገለገሉት፣ የደቡብ ትግራይ – ማይጨው እና ደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና በዋና ጸሐፊነት ያገለገሉት የደቡብ ምዕራብ ሸዋ-ወሊሶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣
ትልቅ የሥራ ፍሬ ማስመዝገባቸውን ምልአተ ጉባኤው አረጋግጧል፡፡ በከፍተኛ ደረጃም አመስግኗቸዋል፡፡

መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አዋጥተው የገዙትን የብር የአንገት አይከንና የእጅ መስቀል ሽልማትም፣ በርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ አማካይነት በሽልማት ተበርክቶላቸው በድምቀት ተሸኝተዋል፡፡

LEAVE A REPLY