ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ለሰው ፍጹም ተፈጥሯዊ ያልኾነውን የግብረ ሰዶም ኀጢአት፣ ነውርና ወንጀል ማውገዝ፣ ቤተሰብን የማዳንና ትውልድን የማስቀጠል ጉዳይ እንደኾነ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ያስረዱት የፋሚሊ ዎች ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ሻሮን ስሌተር፣ ቤተ ክርስቲያን ችግሩን የመከላከል አቋሟን በማጠናከር ሰለባዎችን ነጥቆ የማዳን ሥራም እንድትሠራ ተማፅነዋል፡፡
በቱሪዝም ሽፋን በተደራጀ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ድርጊቱን ለማስፋፋት ያቀዱ ግብረ ሰዶማውያንን ቅዱስ ሲኖዶስ ካወገዘበት ከረቡዕ ጉባኤው በኋላ ፕሬዝዳንቷ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋራ ምሽት ላይ ተገናኝተው ተወያይተዋልተወያዩት ፕሬዝዳንቷ፣ በማግሥቱ ኀሙስ ጠዋት ከሦስት የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋራ በምልአተ ጉባኤው ፊት ቀርበው፣ ለተወሰደው ጠን:: የድርጅታቸውን ድጋፍና አድናቆት በይፋ አሳውቀዋል፡፡
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የበጎ ፈቃድ ድርጅታቸው፥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በራሱ በአሜሪካ መንግሥትና በየአህጉሩ በሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ይሰራል:: ቤተሰብ ተኮር በኾኑ ጉዳዮች ወላጆች ልጆችን በመልካም የሚያሳድጉበትን፣ ልጆችም በትምህርት ተቋማት ከሞራል እና ሠናይ ምግባር ተፃራሪዎች ተጋላጭነት የሚጠበቁበትን፣ በዋናነትም በሚመለከታቸው አካላት፣ በጎ ፖሊሲዎች የሚታነፁበትን አዎንታዊ ተጽዕኖ በመፍጠር ድርጅታቸው እየሠራ እንደኾነ ሻሮን ስሌተር አስታውቀዋ::
በአንጻሩ፣ በሰብአዊ ረድኤትና ልማት ስም ወደ አፍሪቃ ከሚመጡ ድርጅቶች ጥቂት የማይባሉት፣ ለመንግሥታቱ በይፋ ከሚያቀርቡት ማኒፌስቶ በተቃራኒ፣ ግብረ ሰዶምን የመሳሰሉ ነውረኛ ተግባራትን፣ በወጣቶች ፆታዊ መብቶችና ነፃነቶች ጥበቃ ሽፋን እያስፋፉ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
በሰዶማዊ ድርጊት “ወጣት ወንዶችን ለኤች.አይ.ቪ አትጋለጡም፣ ከበሽታውም ነፃ ትኾናላችኁ በማለት፣ ወጣት ሴቶችን ደግሞ እርግዝና እና ውርጃ አያሰጋችኹም” እያሉ እየገፋፉ ለልቅነት እንደሚያበረታቷቸው የተናገሩት የፋሚሊ ዎች ኢንተርናሽናል ኃላፊ፤ “በግብረ ሰዶም የሚደረግ ግንኙነት ከተፈጥሯዊው 17 እጥፍ ለኤች.አይ.ቪ ተጋላጭ እንደሚያደርግ በጥናት ተረጋግጧል” ብለዋል::
በማደጎ ስም የወሰዷቸውን ሕፃናት፣ ተፈጥሯዊ የፆታ ማንነትና ሚና እያቃወሱ መልሰው ወደ ትውልድ
አገራቸው በማምጣት ብዙዎችን በአስተሳሰቡና በድርጊቱ እየጎዱ እንዳሉ፤ ኢትዮጵያም ከዚሁ ስጋት ነፃ እንዳልኾነች ጭምር
አስታውቀዋል፡፡