ዛሬ በኢትዮጵያ የአብዛኛው ክፍል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ ዋለ

ዛሬ በኢትዮጵያ የአብዛኛው ክፍል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ ዋለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በሀገሪቱ አብዛኛው ክፍል፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

በዓለም ላይ የሳይበር ደህንነትና የኢንተርኔት ስርጭትን የሚቆጣጠረው “ኔት ብሎክስ” የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትበአገሪቱ ሙሉ በሙሉ ሊያስብል በሚችል መልኩ ኢንተርኔት መቋረጡን በትዊተር ገፁ ላይ አስነብቧል፡፡

ትናንት ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የተጀመረው አገር አቀፍ ፈተና ላይ የሚያጋጥሙ ማጭበርበሮችን ለመከላከል ሆን ተብሎእንደምክንያት የተቀመጠ መሆኑን የጠቆመው ኔት ክሎክስ፣ መንግስት በዚህ ደረጃ ቁጥጥር ማደረጉ ተገቢ ቢሆንም፤ የፈተና ህትመቱ ያለፈበት ሂደት ምን ያህል ጥንቃቄን የተከተለ ነው? የሚለውን ግምት ውስጥ ከትቶታል ሲል ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ከአመት በፊት ግፈኛውን የህወሃት – ኢሃዴግ አመራር ለማስወገድ ባደረጉት ሀዝባዊ አመጽ የብሔራዊ ፈተናዎችን በአደባባይ በማህበራዊ ድረ ገጾች በመልቀቅ አገዛዙን የሚፈታተኑበት የትግል ስልት እንደነበር አይዘነጋም::

LEAVE A REPLY