የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2012 ረቂቅ በጀት ላይ ተወያየ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2012 ረቂቅ በጀት ላይ ተወያየ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ በሚኒስትሮች ም/ቤት በቀረበው የ2012 ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቷል ባለፈው ቅዳሜ የሚኒስትሮች ም/ቤት የ2012 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀት 386 ቢሊየን 954 ሚሊየን 965 ሺኅ 289 ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡

በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት በገንዘብ ሚኒስቴር በቀረበው የፌደራል መንግስት በጀት ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቷል:: የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በሪፖርታቸው ባለፉት ዓመታት በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ስኬት ቢመዘገብም፣ በርካታ ችግሮች በተያያዥነት መፈጠራቸውን አስረድተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የቀረበው የ2012 ረቂቅ በጀት ማሻሻያ እየተደረገበት የሚገኘው የፊስካል ፖሊሲውንና ተዛማጅ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ተሰምቷል፡፡ ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ፣ በሀገሪቱ በተከሰቱ አለመረጋጋቶች የተነሳ የማይክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን ላይ ግልፅ የሆነ ክፍተት ተፈጥሯል ተብሏል፡፡

የ2011 በጀት ዓመት የታክስ ገቢ መጨመርና የተጀመረው ሀገራዊ የግብር ንቅናቄ ለቀጣዩ ዓመት በጀት እንደ ግብዓት መውሰዱን በውይይቱ ላይ የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በቀጣዩ በጀት ዓመትም ገቢውን ለማሳደግ የታክስ አስተዳደሩን ሂደት ዘመናዊ ማድረግ የሚያስችሉ መንገዶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY