ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር እንዲገቡ የተደረጉ መድኃኒቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡
ከ4 ሚሊየን 214 ሺህ 175 ብር በላይ ዋጋ ያወጣሉ የተባሉት መድኃኒቶች፣ በቁጥጥር ስር የዋሉት፤ በሞያሌ ከተማ በኣራት የመድኃኒት መደብሮች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑ ተነግሯል፡፡
እነዚህ በህገ ወጥ መንገድ ሞያሌ የገቡና በቀጣይም ወደሌሎች አካባቢዎች ሊሰራጩ የተዘጋጁ መድኃኒቶች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገቡ፣ ሰንሰለታቸውን ባልጠበቀ መልኩ ወደ ሀገር የገቡ፣ እንደሆነ ከባለስልጣን መ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡