ለሕጻናት ጤንነት አስጊ ናቸው የተባሉ 46 ምርቶች ታገዱ

ለሕጻናት ጤንነት አስጊ ናቸው የተባሉ 46 ምርቶች ታገዱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ህብረተሰቡ 46 የሚሆኑ የህጻናት ምግብ፣ የለዉዝ ቅቤ፣ ማር – የምግብ ዘይትና የምግብ ጨው ምርቶችን እንዳይጠቀም የኢትዮጲያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስጠንቅቋል፡፡

ከጤና ጎጂነት ጋር በተያያዘ ምንጫቸው ያልታወቀ፣ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸውን የምግብ ምርቶች ገበያ ላይ በስፋት እየዋሉ እንደሚገኙ በገበያ ቅኝት በመረጋገጡ የከፋ ጉዳት ከመድረሱ በፊት እርምጃ መውሰዱንና ጉዳት አድራሽ የሆኑትን ምርቶች ለህዝብ ማሳወቁ ተገቢ ሆኖ መገኘቱን ባለስልጣን መ/ቤቱ አስረድቷል፡፡

በዋና ከተማይቱ አዲስ አበባ በተለያዩ ድርጅቶች ተመርተው ወደ ገበያ በተሰራጩ ምርቶች ላይ በተደረገ የገበያ ቅኝት፤ በብሔራዊ ደረጃ የተቀመጠውን መስፈርት ያላሟሉ፣ ምንም ዓይነት ገላጭ ጽሁፍ የሌላቸውና የአምራች አድራሻ እና መለያ ቁጥር ያልሰፈረባቸው

የህጻናት ምግብ፣ የለዉዝ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ የምግብ ጨውና ማር ገበያ በብዛት ተገኝተዋል፡፡ ከዚህ በመነሳት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስተዳደራዊ እርምጃ በ46 ተቋማት ላይ ወስዷል፡፡

ጉዳዩ የሚመለከተው የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር መ/ቤት ሕብረተሰቡ ከእነዚህ ድርጅቶች ምርቶች ራሱን እንዲጠብቅ በማሳሰብ አምራች ድርጅቶቹን ዝርዝር በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል፡፡

የሕጻናት ምግብ፡-

1. ፍቅር ምጥን

2. ማስ የህጻናት ምግብ

3. ተወዳጅ ሀይል ሰጪና ገንቢ የህፃናት ምግብ

4. ስሚ የህፃናት ምጥን ገንፎ

5. ፋሚሊ ሀይል ሰጪና ገንቢ የህፃናት ምግብ

6. አባድር

7. ሂሩት ህፃናት ሂሩት ባልትና

8. አዩ ለልጆች የተዘጋጀ ምጥን ምግብ

9. ምቹ 100% ተፈጥሯዊ ይዘቱን የጠበቀ የህፃናት ምግብ

10. ፍቅር ኑሪሺ ዩር ቤቢስ ፍቅር/nourish your babies fiker

የምግብ ጨው

1. ሸዋ የገበታ ጨዉ/shoa table salt

2. Greep Iodized Salt

3. Sname Iodized table Salt

4. አባተ አዮዲን ጨው/ Abate Iodized Salt

5. Refined and iodized woef table Salt

6. ምርጥ የገበታ ጨዉ

7. አቤት የገበታ ጨዉ

የለዉዝ ቅቤ

1. ኤደን የለዉዝ ቅቤ

2. ጽጌ የለዉዝ ቅቤ

3. ፀዬየ ለዉዝ ቅቤ

4. ማቲፍ የለዉዝ ቅቤ

5. ምስራቅ የለዉዝ ቅቤ

6. ታደለ ንጹህ የለዉዝ ቅቤ

7. ምእራፍ የታሸጉ ምግቦች

8. ህብረት የለዉዝ ቅቤ

9. ደስታ የለዉዝ ቅቤ

10. ሳራ የለዉዝ ቅቤ

11. ሰን ናይት የለዉዝ ቅቤ

12. አቢሲኒያ የለዉዝ ቅቤ

የምግብ ዘይት

1. ጸደይ የምግብ ዘይት

2. ኑር

3. ኦሜጋ

4. ቅቤ ለምኔ

5. ሰብር የኑግ ዘይት

6. ያሙ የምግብ ዘይት

7. ሜራ የኑግ ዘይት

8. ፍፁም የተጣራ የኑግ ዘይት

9. ቀመር የምግብ ዘይት

10. ኔግራ የምግብ ዘይት

11. ከበለመን የምግብ ዘይት

ማር ምርት

1. ሃበሻ ንጹህ የተፈጥሮ ማር

2. ተርሴስ ማር

3. ንጹህ ማር

4. ኢትዮ ማር

5. ማስ የጫካ ማር

6. ራይት ማር

LEAVE A REPLY