አቶ ያሬድ ሀይለማርያምን እና መሰሎቻቸውን የሚሰማመንግሥት ከወዴት አለ?! ||...

አቶ ያሬድ ሀይለማርያምን እና መሰሎቻቸውን የሚሰማመንግሥት ከወዴት አለ?! || መስፍን ማሞ ተሰማ

ሠላም ለናንተ ይሁን!

በኢትዮጵያ ሥነ መንግሥትና ሥነ ህዝብ መስተጋብርና ሀላፊነት ህጋዊነትና ተጠያቂነት ላይ የአቶ ያሬድ ሀይለማርያም ምልከታና ምክረ ሀሳብ ሁሌም ያስደምመኛል። ለአብነት ጁን 13/2019 ‘ፖለቲከኞቻችን ጠዋት ጥምጥም ከሰዓት ኩፊበሚል ርዕስ በፌስ ቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ጥልቅና ውስጠትን ጠያቂ የሆነ የወቅቱን ፖለቲካዊ ዱካ የቃኙበት ፅሁፍ አንዱ ነው የኢትዮጵያ መሪዎች ወይም የመንግሥት ሀላፊ ፖለቲከኞች ግን እንዲህ ያለ ቅን መንፈስ ናቅን ሰብዕና ከሀገራዊ ራዕይ ጋር ያጣመሩ ዜጎችን አያስጠጉም አያነጋግሩም አያዳምጡም

እነርሱየሀገረ መሪዎቹበዙሪያቸውና በመንግሥታቸው መዋቅራት  ሁሉ  (አልፎ አልፎ አንዳንድ ሁለ ገብ ቅቡልነት ያላቸውን ለገፅታ መሳመሪያና ማድመቂያ ካልሆነ በስተቀር) በአብዛኛው  የሚያሰባስቡትና በሚመሩት መንግሥት መዋቅራት ሀላፊነት የሚሰጡት በዕድሜያቸውና በዘመናቸው ካሳለፉት ፖለቲካዊ ኩነት ያልተሞረዱ እንዳረጀ እባብ የውጪ ቆዳቸውን እንጂ ውስጣቸውን  ያልቀየሩ ካፖርት  ገልባጭ ቡድን/ቲፎዞ አደራጅ የከሸፉ የሴራ ፖለቲከኞችን ነው

እኒህ  ተገለባባጭ ፖለቲከኞች ደግሞ በኖሩባቸው ዘመናት ሁሉ ድርጅት ሲቀላቀሉ ድርጅት ሲያፈርሱ ድርጅት ሲመሰርቱና ወጣቱን በቱማታ ቲዎሪና በተኮፈሰ  ሁሉን አውቅ ባይ ሰብዕና በተገነባ ቲፎዙ ሲያምሱ የኖሩ ናቸው ‘ከደርግ የባሰ አይመጣም/አልመጣምበሚለው እጅግ አድርባይ መፈክራቸው ከያሉበት ብሪፍ ኬዞቻቸውን አንጠልጥለው ቤተ መንግሥት የገቡ የዘር ልክፍተኞቹን በዋናነት ህወሀትንና ኦነግን ዕውቅና የሰጡ የኢትዮጵያ ሰቆቃ አልፋና ኦሜጋ የሆነው የኢህአዴግ አርኪቴክቱን መለስዜናዊቢሳሳት እንኳን ሆን ብሎ ኢትዮጵያን ለመጉዳትሳይሆን ባለማወቅ ስለሚሆን በገንቢ ሂስ ማስተካከል ይቻላልብለው ለአያሌ ዓመታት ኢህአዴግ ስር  እንዲሰድ  የረዱትን መለስ ብለን ስናስታውስና ዛሬ ያለንበትንባለህበት እርገጥወይምአንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደሗላፖለቲካዊ ሁኔታ ስንመዝን  የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችን ዐይነተኛ ወይም ተፈጥሯዊ  በህሪያቸውን  ‘ታሪክ ራሱንደግሞያሳየናል

ኢትዮጵያ በዘረኛው የኢህአዴግ መንግሥትና በዘዋሪው መለስ ዜናዊ የገባችበትን አዘቅት ከየተኛውም ፖለቲከኛ ወይም የፖለቲካ ሳይንቲስት ነኝ ባይ ተንታኝ በፊት በገሀድ ያሳዩትና የተናገሩት ታላቁ  የሀይማኖት አባት አለቃ አያሌውታምሩ ነበሩ አለቃ አያሌው 1987 / (ምድረ ፖለቲከኛና ምሁር ከዘመኑ ባለጊዜዎች ጋር ሂስ እየተዋዋጠ ውስኪውንሲቀዳና ቁርጥ ሲያወርድ) አሳቸው በምድሪቱ  ላይ ግፍ ፈፃሚዎችንና አስፈፃሚዎችን በአደባባይ አወገዙ “ኢትዮጵያ በመንፈሳዊና ዐለማዊ ህይወቷ በሽተኛ ሆናለችአሉ  ስለ ዕውነትና ስለ ኢትዮጵያ ብቻቸውን ቆመው የአቡነ ጳውሎስንና የመለስ ዜናዊን ጣምራ በቀል ተቀብለው አረፉ። ስለ እርሳቸው  ዕውነት  ስለደረሰባቸውም ግፍ የትኛውም የኦርቶዶክስ ወይም የሌላ ሀይማኖት አባት ከጎናቸው አልቆመም የትኛውም ሂስ ሰጪም ሆነ ሂስ ተቀባይ ፖለቲከኛ ስለ አለቃ አያሌው ድምፁን ሰማም አለቃ አያሌውን መለስ ዜናዊና አቡነ ጳውሎስ የበቀል ዶፍያወረዱባቸው ከምርጫ 97 አስር አዓመት በፊት ነው ይህንሁሉ ማንሳቴ ጠቢቡ ደራሲ በዓሉ ግርማየሰው የማስታወስችሎታ አጭር ነውብሎ የፃፈው ያሳለፍነውንና የምንገኝበትን ፖለቲካዊ ዕውነታ አስታውሶኝ እንጂ

ወደ ቀደመ ጉዳያችን እንመለስ

አቶ ያሬድ ሀይለማርያም አስቀድሜ በጠቀስኩት ርዕስ ስርእንዲህ አንጥበዋልህግ ማስከበር ከተማ ማዘመንና ፅዳትበድሀ ዜጎች መቃብር ላይ መሆን የለበትም እነሱን ከፍማድረግ እንጂ

ቅዱስ መፅሀፍየግፏን አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነውእንዳለውከዚህ ጥልቅ ጉድጓድ ጫፍ ላይ ቆማችሁ ግፍ ባማረረውሕዝብ ላይ የምትዘባበቱ ባለሥልጣናት የኃይማኖት አባቶችና ፖለቲከኞች ብታስቡበት መልካም ነው የጊዜ ጉዳይነው እንጂ ጉድጓዱ የቀደሙትን ግፈኞች እንደበላው ሁሉ እናንተንም ይበላል በየስርቻው ፎቶ ተነስቶ መለጠፍየናንተን ገፅታ ይገነባ ይሆናል እንጂ ለተገፋው ደሃ ጠብየሚል ነገር የለውም ይህንን ስል የጠቅላይ ሚኒስትሩንየአንድ ዓመት ቆይታ የሚያሳየውን የፎቶ ኤግዚቢሽን ልብይለዋልበማለት ፅፈዋል እንግዲህ ጆሮ ያለው ይስማ ልብያለውም ልብ ያድርግ ያም ሆነ ይህ ግን ኢትዮጵያ ስለ እርሷየሚሰቃዩና የሚጨነቁ ልጆቿን የምታቀርባቸውና የምትሰማቸው መች ይሆን?! ብዙ እስክንድሮችንና ብዙያሬዶችን የኢትዮጵያ መንግሥትና አጋሮቹ ፖለቲከኞች የለውጥ እንቅፋቶችና የእንጀራ ልጆችአድርገው ማየትና መፈረጅ የሚያቆሙት መቼ ነው? ለማንኛውም ነገ ሌላ ቀንነው!

በያለንበት ቸር ይግጠመን!

ሰኔ 2011 ዓ/ም (ጁን 2019)

ሲድኒ አውስትራሊያ            mmtessema@gmail.com

LEAVE A REPLY