ኢትዮጵያ ነገ ወቅታዊ አማርኛ ዜናዎች

ኢትዮጵያ ነገ ወቅታዊ አማርኛ ዜናዎች

አርቲስት እቴነሽ ግርማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

የአርቲስት እቴነሽ ግርማ የቀብር ስነ ስርዓት በለቡ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ በ1959 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ ማሊማ ወረዳ የተወለደችው አርቲስት እቴነሽ ግርማ ፣ ከ9 ዓመቷ ጀምራ በአዲስ አበባ ከተማ ነው የኖረችው።

አርቲስት እቴነሽ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ በማረሚያ ቤቶች ተቀጥራ ህይወቷ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ እስከ ሻለቃነት ማዕረግ ድረስ ስታገለግለል ቆይታለች።

በአማርኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋ የተለያዩ ተወዳጅ ዜማዎችን በማቀንቀን የምትታወቀው እቴነሽ ግርማ፣ ሁለት የሙዚቃ አልበሞችንና ከተለያዩ ታዋቂ አርቲስቶች ጋር በመሆን ለአድማጭ አበርክታለች።

በባህላዊና የሰርግ ዜማዎቹ ከፍተኛ እውቅና ያገኘው የድምጻዊ ደመረ ለገሰ ባለቤት የሆነችው አርቲስት እቴነሽ ግርማ የሁለት ወንድ ልጆችና የአንድ ሴት ልጅ እናት ነበረች።

ከዓመቱ የትምህርት ጅማሬ አንስቶ የብሔር ግጭት ለመፍጠር የተዘረጋ መረብ መኖሩ ታወቀ

በዓመቱ የትምህርት ማገባደጃ ላይ ሆን ተብሎ በተሰራ ሴራ፣ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሁከት በመፍጠር፣ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ታውቋል።

ግጭት በተፈጠረባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ለፈተና ከመዘጋጀት ይልቅ ለደህንነታቸው እንዲያስቡ የተገደዱ ነው:: ይህ ደግሞ ተማሪዎቹ ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ
ተፅዕኖ እንደፈጠረባቸው ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ድርጊቱ ጊዜው የትምህርት መገባደጃ በመሆኑ ተማሪው አመት የለፋበትን ጥረት ዋጋ ለማሳጣት እየተደረገ ያለ እንቅስቃሴ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ችግሩ በተለይ በአንድ ቦታ በሚፈጠር ሁከት ብሄርን ሽፋን በማድረግ ሌላም ቦታ እንዲስፋፋ የሚያደርግ መረብተዘርግቶለት ከአመቱ የትምህርት ጅማሬ አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ እየተሰራበት መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡

ሰሞኑን ግጭት ከታየባቸው ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በሆነው የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ እርቅ ተፈጥሯል:: ተማሪዎችም ከእርቁ በኋላ በቀጣይ ችግሩ እንዳይደገም መንግስትም ሆነ ተማሪዎች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል::

በመንግስት በኩል ሊሰሩ የሚገባቸው ስራዎች ሁሉ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመግለጽ ሰላሙን ከማስጠበቅ በተጓዳኝ ከውስጥም፣ ከውጭም ሆነው ሁከቱን የሚቀሰቅሱ አካላትን በማጣራት ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በ2012 መንግስት 59 ቢሊዮን ብር ሊያትም ይችላል

የኢትዮጲያ መንግስት በ2012 የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት ከሀገር ውስጥ 59.3 ቢሊዮን ብር በመበደር ሊሸፍን ማሰቡን የገንዘብ ሚንስትር ማስታውቁ ከወዲሁ አነጋጋሪ ዜና ሆኗል፡፡

መንግስታት የበጀት ጉድለታቸውን በሁለት መንገድ ማለትም ከውጪ በሚገኝ ብድር እና እርዳታ እንዲሁም ሌላኛው ከሀገር ውስጥ በቦንድ (በግምጃ ቤት ሰነድ) ሽያጭ ከባለሃብቶች ወይም ከድርጅቶች በመበደር ሊሸፍኑ ይችላሉ፡፡

መንግስት ቦንድ (የግምጃ ቤት ሰነድ) የተወሰነ የብር መጠን ያላቸው እና የመክፈያ ወቅት (የተለመዱት 60፤90 እና120 ቀን) የተቀመጠላቸው ሰነዶች ያዘጋጃል፤ እነሱን ሰነዶች ባለሃብቶች ወይም ድርጅቶች ከመንግስት በመግዛት በምትኩ ገንዘቡን ለመንግስት በማስረከብ ፣ወለድ ይደምራሉ (ማለትም፤ የ1 ቢሊዮን ብር ሰነድ የገዛ ባለሃብት መንግስት 7 ከመቶ ወለድ ቢጨመርበት በተቀመጠው ቀን መንግስት ለባለሃብቱ 1 ቢሊየን 70 ሚሊየን ብር አድርጎ ይከፍላል ማለት ነው)፤

ይህን መሰሉ የሀገር ውስጥ ብድር የሚካሄደው በብር: የሚከፈለውም በብር ነው፡፡ መንግስት ከተለያዩ የግብር ምንጮች ከሚያገኘው ገቢ እዳውን ይከፍላል፡፡ ነገር ግን በ2011 መንግስት ከግብር መሰብሰብ የቻለው 160 ቢሊየን ብር ብቻ ሲሆን፤ ከሀገር ውስጥ ወጪ አንጻር ሲታይ በ70 ቢሊየን ብር ያንሳል::

ስለሆነም መንግስት በቀላሉ ሲያደርግ የነበረውም ሆነ ሊያደርግ የሚችለው ብርን በማተም እዳውን መክፈል መሆኑ ታውቋል፡፡ ብድሩ ከአጠቃላይ ምርት አንጻር 1.8% ቢሆንም በገቢያው ላይ ተጨማሪ ገንዘብ ታትሞ ሲሰራጭ የዋጋ ንረትን ማባባሱ እንደማይቀር እየተነገረ ነው፡፡

በምትኩ የመንግስትን ወጪ በመቀነስ፤ ዝቅተኛ ወለድ ያላቸው የውጪ ብድሮችን በማፈላለግ፤ የውጪ እርዳታን በመጠየቅ፤ ግዙፍ የመንግስት የልማት ተቋማትን በፍጥነት ወደ ግል በማዞር፤ የግብር አሰባሰብን በማዘመን፤ ሙስናን በመከላከል፤ ከውጪ የሚላኩ ገንዘቦችን ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲገቡ በማድረግ፤ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር፤ የሀገሪቷን ሰላም በማረጋጋት ምርት እና ንግድን የማሻሻል፤ ወዘተ እርምጃዎችን በመውሰድ የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት ቢሞክር የተሻለ ነው የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም በመንግስት ደረጃ ግን የመጀመሪያው አማራጭ ቅድሚያ ተሰጥቶታል፡፡

ሕወሓትና ሻዕቢያን ለማስታረቅ የመንግስት ድጋፍ ያስፈልጋል ተባለ

“ዳስ ዕርቂ አሕዋት ውድባት” (የዕርቅ ዳስ) በሚል መርሕ በተዘጋጀው የዕርቅ መድረክ፣ ሕወሓትና ሻዕቢያን ለማስታረቅ የማዕከላዊ መንግሥት ዕገዛ እንዲያደርግና ለሚደረገው ጥረትም ዕውቅና እንዲሰጥ ሴለብሪቲ ኢቨንትስ ጠይቋል፡፡

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተፈጠረው ሰላም በሕወሓትና በሻዕቢያ መካከል አለመፈጠሩን የሚናሩት የሴሊብሪቲ ኢቨንትስ መሥራች ወንድማማቾቹ አቶ አብርሃምና አቶ ሀብቶም ገብረ ሊባኖስ፣ በሁለቱ ድርጅቶች ውስጥ የሚታየው ጥላቻና እልህ የአገርን ደኅንነት ሥጋት ላይ ጥሏል በለዋል::

በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶችም እንደሚያሳዩት፣ ሕወሓትን ያገለለው የኢትዮጵያና ኤርትራ ዕርቅ በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የነበረውን መጠራጠርና ጥላቻ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እንዲጠናከር መንገድ መክፈቱን አስረድቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአየር ትራንስፖርት መግባትና መውጣት ቢቻልም ድንበር አካባቢ ምንም የተቀየረ ነገር ባለመኖሩ፣ በድንበር አካባቢ ያለው ድባብም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሰላምም ጦርነትም የሌለበት እንደሆነ የሚያሳይ ነው ተብሏል::

በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለው እልህ ዕርቁ መሬት እንዳይወርድ እንቅፋት ስለሆነ፤ በድርጅቶቹ መካከል አለ የሚባለው የከረረ ፀብ በተለይ ድንበር ላይ ላሉ ነዋሪዎች ከባድ ፈተና ከመሆኑ አኳያ ነገሮች በፍጥነት መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ ወንድማማቾቹ ተናግረዋል፡፡

“የጦርነቱ የመጀመርያ መንስዔ የሆኑት ሕወሓትና ሻዕቢያ ወደ ዕርቁ ካልመጡ ድንበር አካባቢ ያለው ጉዳይ መፍትሔ እንደማይኖረው በጥናት ደርሰንበታል” የሚሉት አስታራቂዎች፣ ሁለቱን ድርጅቶች በማስታረቅ ረገድ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግና ለእንቅስቃሴውም ዕውቅና እንዲሰጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ ባለፈው ሳምንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ማስገባታቸውን ጠቁመው ከሕወሓትና ከሻዕቢያም በኩል ግን ጥሩ ምላሽ እንዳገኙ ተናግረዋል፡፡

አርቲስት እቴነሽ ግርማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

የአርቲስት እቴነሽ ግርማ የቀብር ስነ ስርዓት በለቡ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ በ1959 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ ማሊማ ወረዳ የተወለደችው አርቲስት እቴነሽ ግርማ ፣ ከ9 ዓመቷ ጀምራ በአዲስ አበባ ከተማ ነው የኖረችው።

አርቲስት እቴነሽ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ በማረሚያ ቤቶች ተቀጥራ ህይወቷ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ እስከ ሻለቃነት ማዕረግ ድረስ ስታገለግለል ቆይታለች።

በአማርኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋ የተለያዩ ተወዳጅ ዜማዎችን በማቀንቀን የምትታወቀው እቴነሽ ግርማ፣ ሁለት የሙዚቃ አልበሞችንና ከተለያዩ ታዋቂ አርቲስቶች ጋር በመሆን ለአድማጭ አበርክታለች።

በባህላዊና የሰርግ ዜማዎቹ ከፍተኛ እውቅና ያገኘው የድምጻዊ ደመረ ለገሰ ባለቤት የሆነችው አርቲስት እቴነሽ ግርማ የሁለት ወንድ ልጆችና የአንድ ሴት ልጅ እናት ነበረች።

LEAVE A REPLY